top of page

በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለአነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ መሆኑን ተነገረ፡፡

  • 2 days ago
  • 1 min read

መጋቢት 9/2018

በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለአነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ መሆኑን ተነገረ፡፡


ይህ የሰማነው የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና ለእርሻ ድርጅት ባደረጉት አብሮ የመስራት ስምምነት ላይ ነው፡፡


ለእርሻ ደርጅት በሚቀጥሉት 4 ዓመታት አነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ብድር ለማመቻቸት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ከዚህ በፊት በሙከራ ደረጃ በሰራው ስራ ገበሬዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡


የለእርሻ ድርጅት ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም እንድርያስ በዚህ ዓመት ብቻ ለ65 ሺህ ገበሬዎች ብድር ለማቅረብ እቅድ መያዛቸውን የሚናገሩ ሲሆን ለስራውም ከተለያዩ ባንኮች ጋር እንደሚሰሩም አስረድተዋል፡፡


በሙከራ የስራ ወቅት ገበሬው በትክክል የሚፈልገው ብድር ከተሰጠው ያለምንም ችግር ብድሩን መክፈል እንደሚችል ተመልክተናል ያሉ ሲሆን ይህን ስራ ለማስፋት ነው አሁን ስምምነት ከግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የተዋዋልነው ብለዋል፡፡



ለገበሬው ብድር ብቻ ማመቻቸት በቂ አይደለም ጥራት ያለው የግብርና ግብዓትና ዘመናዊ መሳሪያ ማቅረብ ያስፈልጋል የኢትዮጵያ ስራዎች ኮርፖሬሽን በዚህ ዘርፍ የተሰማራ በመሆኑ በትክክል ከተሰራ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ሲሉም አስረድተዋል፡፡


የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ የስንዴ ምርትና የበቆሎ ምርትን አሁን ካለበት በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ መያዙን ጠቅሰዋል፡፡


የምርጥ ዘር አጠቃቀም ማሳደግ፣ የአፈር ማዳበሪያ በሄክታር ከ44 ኪሎ ግራም ወደ 400 ኪሎ ግራም ለማሳደግ አቅደን እየሰራን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡


ለግብርና የሚያስፈልጉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለገበሬው ማቅረብ በሚቀጥሉት ጊዜያት ዋነኛ እቅዳችን ነው ያሉ ሲሆን ይህንን ለማሳካት ከእርሻ ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚቀርበው ድብር ውስጥ ግብርናው ለግብርናው የሚመደበው 2 በመቶ ሲሆን በዓመት ግብርናውን ለማዘመን እስከ 2 ትሪሊን ብር ብድር እንደሚያስፈልግም ይነገራል፡፡


በ2030 ለማሳካት በወጣው የግብርና ፍኖተ ካርታ በወቅቱ ለግብርናው ዘርፍ የሚመደበው ብድር ወደ 880 ቢሊዮን ብር ለማድረስም ታቅዷል፡፡


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page