ኢቲኬር የስፓይሩሊና ምግብ አጋዥ እና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን እንዲያመርት ፍቃድ ተሰጠው።
- sheger1021fm
- 12 minutes ago
- 1 min read
ጥር 22/2018
ኢቲኬር የስፓይሩሊና ምግብ አጋዥ እና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን እንዲያመርት ፍቃድ ተሰጠው።
ስፓይሩሊና በያዘው ከፍተኛ ፕሮቲን እንደ አጋዥ ምግብ ወይንም ሰፕልመንት የሚመርጥ እንዲሁም ለውበት መጠበቂያነት የሚያገለግለውና በውሃ አካላት ላይ የሚገኘውን አልጌ ነው።
ኢቲ ኬራ ስፓይሩሊና አልጌን ለአጋዥ ምግብነትም ፣ ለውበት መጠበቂያም አድርጎ እንዲያመርት የመጠቀሚያ ፈቃድ የሰጠው የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ነው፡፡
ይህን ስምምነትም በዛሬው እለት በኢቲኬር ፕሮዳክት መስራችና ባለቤት አቶ ማቲዮስ መባ እና የብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ (ዶ/ር) መካከል ተፈርሟል።

ስፓይሮሊና አልጌን የመሳሰሉ የብዝሃ ሕይወቶችን ለመጠቀም ፣ ለማምረት ፍቃድ ያስፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩትም ይህንን ፈቃድ የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ ኢቲኬር ይህንኑ የመጠቀም ፈቃድ የተሰጠው ከአስገዳጅ ስምምነቶች ጋር ነው ብለዋል፡፡
ኢቲኬር ስፓይሮሊና አልጌን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ጪቱ ሀይቅ ላይ ዘሩን ወስዶ ቡልቡላ በሚገኘው አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በሰራው ኩሬ ውስጥ አባዝቶ ምርት እንደሚጀምር ሰምተናል፡፡
ግማሽ ኪሎ ግራም የሚሆን ስፓይሮሊና አልጌ አጋዥ ምግብ ወይምም ሰፕሊመንት ከውጪ ሀገር እየመጣ ኢትዮጵያ ውስጥ 14 ሺ ፣ 15 ሺህ እንደሚሰጥ የነገሩን የኢቲኬር ባለቤት አቶ ማቲዮስ መባ ምርቱ ወደ ገበያ ሲወጣ ከዚህ ባነሰ ዋጋ እንደሚሆነ አስረድተዋል፡፡
ኢቲ ኬር ስፓይሮሊና አልጌን በተለይ በታብሌት መልክ አምርቶ ከሶስት ወር በኋላ ለገበያ እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ንጋቱ ሙሉ












Comments