የሐምሌ 21 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
- 1 day ago
- 2 min read
የጃፓን ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል በርዕደ መሬት ተመታ፡፡
ርዕደ መሬቱ የደረሰው ኩማማቶ የተባለው የአገሪቱ ክፍል እንደሆነ ኒኪ እስያ ፅፏል፡፡
የመሬት ነውጡ የተቀሰቀሰው ከምድር በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት መሆኑ ታውቋል፡፡
ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል፡፡
ቀደም ሲል የባህር ማዕበል /ሱናሚ/ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ወዲያው መታጠፉ ተጠቅሷል፡፡
ያም ሆኖ ሰዎች ራሳቸውን ከባህር ዳርቻዎች እንዲያርቁ ተመክረዋል፡፡
በኩማማቶው ርዕደ መሬት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡
በዚሁ ስፍራ ከ10 አመታት በፊት ደርሶ የነበረ ርዕደ መሬት 300 ያህል ሰዎችን እንደገደለ መረጃው አስታውሷል፡፡
ጋና ተጨማሪ 1 ሺህ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ አስወጣች፡፡
በደቡብ አፍሪካ በቀጠለው የስደተኛ ጠል ወገኖች ጥቃት ምክንያት ጋና ቀደም ሲል 900 ዜጎቿን መመለሷን አፍሪካ ኒውስ አስታውሷል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ስደተኛ ጠሎቹ ወገኖች ሰነድ አልባዎቹ የውጭ ተወላጅ አፍሪካውያን ተጠራርገው ይውጡልን ከማለት አልፈው ግድያ ፣ ደብደባ እና ዘረፋ እየፈፀሙባቸው መሆኑ ይነገራል፡፡
ሕጋዊ የስራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ተወላጅ አፍሪካውያንም የጥቃቱ ሰለባዎች ናቸው ይባላል፡፡
ጋና በደቡብ አፍሪካው የጥላቻ ጥቃት ሽሽት ዜጎቿ በዚያ ለተውት ሐብት እና ንብረት ካሣ መጠየቄን አልተወውም ማለቷ ተሰምቷል፡፡፡
አፍሪካውያን ጠሉ ጥቃት በአህጉር ደረጃ የደቡብ አፍሪካን ገፅታ እያጠለሸው መምጣቱ ይነገራል፡፡
ጋና እና ናይጀሪያ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አንዱ መነጋገሪያ አጀንዳ እንዲሆን ቀደም ሲል ጥያቄ ማቅረባቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡
የሊቢያ ተቀናቃኝ አስተዳደሮች አገሪቱ ወደ ብሔራዊ አንድነቷ እንድትመለስ ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ሊያደርጓቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሊቢያ ከ15 አመታት ገደማ በፊት የቀድሞው የአገሪቱ መሪ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ አስተዳደር በትጥቅ አመጽ ከተወገደ ወዲህ በምስራቅ እና በምዕራብ እንደተከፋፈለች ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ሰሜን አፍሪካዊቱ አገር ወደ ብሔራዊ አንድነቷ እንድትመለስ ዲፕሎማሲዊ ጥረት እያደረገች መሆኑን አሽራቅ አል አውሷት ፅፏል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳት የአፍሪካ እና የአረብ አገሮች ጉዳይ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ የሊቢያ ተቀናቃኞች ንግግር እርምጃ እየታየበት መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ያም ሆኖ ሁለቱ ተቀናቃኝ አስተዳደሮች ልዩነት የበዛ እንደሆነ አማካሪው አልሸሸጉም፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሊቢያ የብሄራዊ አንድነት ጉዳይ ጎልቶ እየተሰማ ነው፡፡
ሆኖም አገሪቱን ወደ ብሔራዊ አንድነቷ የመመለሱ ጉዳይ ቀላል እንዳልሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
አሜሪካ ጦርነቱን ብትጀምረውም መቼ እና በምን ሁኔታ እንደሚያበቃ የምትወስነው ኢራን ብቻ እንደሆነች የፋርሳዊቱ አገር የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኢስማየል በካይ ተናገሩ፡፡
በካይ በጦርነቱ ማብቂያ ጉዳይ አሜሪካ በአድራጊ ፈጣሪነት እንድትወስን አንፈቅድም ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡
አሜሪካ አገርሽቶ የነበረውን በጦር መጠቃቃት ማቆማቸው ታውቋል፡፡
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አስተያየት የተሰማውም መጠቃቃቱ ከተገታ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
አክሲዮስ እንደዘገበው የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸውን ጦር በኢራን ላይ የሚፈፅመውን ድብደባ እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
በቀዳሚዎቹ 2 ሳምንታት ገደማ አሜሪካ በኢራን ላይ ከባድ ድብደባ ስትፈፅም ቆይታለች፡፡
ኢራንም በአፀፋ በአቅራቢያው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ተቋሞች ላይ ያነጣጠረ ነው ያለችውን የአፀፋ ጥቃት ስታደርስ እንደነበረ መረጃው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
_edited.jpg)

Comments