የአፍሪካን የሠላም እና ደህንነት ጉዳይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት የሎጀስቲክስ እና ኮሚዩኒኬሽን አለመቀላጠፍ እስከዛሬም ያልተፈታ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ተባለ።
- 2 hours ago
- 2 min read
ሐምሌ 20 2018
የአፍሪካን የሠላም እና ደህንነት ጉዳይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት የሎጀስቲክስ እና ኮሚዩኒኬሽን አለመቀላጠፍ እስከዛሬም ያልተፈታ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ተባለ።
አፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ፣ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በየጊዜው የሚፈትኗት አህጉር ብትሆንም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት መሰረታዊ ለሆነው የሎጅስቲክስ ዘርፍ ትኩረት እንዳልተሰጠው ተነግሯል።

ይህ የተነገረው ኢትዮጵያ እና አሜርካ በጋራ ባዘጋጁት የ2026 የአፍሪካ ሎጅስቲክስና ኮሚውኒኬሽን ሲምፖዚየም ላይ ነው።
በሲፖዚየሙ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ ኮማንድ ተወካይ ጀነራል "ዳግቪን አንዴርሰን" ዓለም የተራቀቀ የቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ ቢሆንም፣ የሎጅስቲክስ አለመቀላጠፍ ለውትድርናው ዘርፍ አሁንም ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
ሽብርተኝነትን፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና ሌሎች ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን የምንዋጋው ሎጅስቲክስ ሲኖር ብቻ ነው ሲሉ ጀነራል አንደርሰን አስረድተዋል።
ሎጅስቲክስና ኮሚውኒኬሽን ከሌለ ደህንነትን የሚያረጋግጥ ኦፕሬሽን አይኖርም ያሉት ጀነራሉ፣ እንዳለመታደል ሆኖ ግን በዘርፉ ላይ ኢንቨስት መደረግ ባለበት አግባብ ኢንቨስት አልተደረገም ብለዋል።
የደህንነት ችግር ሲፈጠር የአደጋ ጊዜ የህክምና መድሃኒቶችን፣ የውትድርና ግብአቶችን ፣የአስቸኳይ ጊዜ ቁሳቁሶችን ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ ማጓጓዝ ያለ ሎጅስቲክስ እና ኮሚውኒኬሽን የሚታሰብ አይደለም፣ እስከዛሬም ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው በማለት አስረድተዋል።
ለኢትዮጵያ አየር አየር መንገድ ምስረታ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን አሜሪካዊውን ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰንን ያነሱት ጀነራል አንደርሰን ኢትዮጵያ ገና ያኔ ስለ ሎጅስቲክስ ጥቅም ገብቷት ኢንቨስት በማድረጓ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ የአህጉሪቱ ትልቁ አየር መንገድ መሆን ችሏል ብለዋል።
ይህ ለሎጅስቲክሱ ዘርፍ እድገት እንዴት እና ምን መስራት እንዳለብን ማሳያ ነው በማለት አስረድተዋል።
የመከላከያ ሚንስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው አፍሪካ ነገ ለሚጠብቃት የደህንነት ሥራ ዛሬ ሎጅስቲክስ ላይ በትብብር መስራት አለባት ብለዋል።
ሲፖዝየሙ ከአሜርካ ጋር በጋራ መካሄዱ የኢትዮጵያ እና አሜርካ ግንኙነት ወደ ውትድርና ስትራቴጂ ትብብር ማደጉን ማሳያ መሆኑንም ኢንጂነር አይሻ ተናግረዋል።
በሲፖዚየሙ በኢትዮጵያ የአሜርካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ጨምሮ ከ40 በላይ የአፍሪካ ሃገራት ሎጅስቲክ ተወካዮች፣ ከ20 በላይ የሎጅስቲክስ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሲፖዝየሙ ኢንዳስትሪ እና የሎጅስቲክስ ዘርፉ በጋር በመሆን አሁን ያለውን ችግሩን ለመፍታት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
ንጋት መኮንን
_edited.jpg)



Comments