top of page

ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

  • 2 hours ago
  • 2 min read

ሐምሌ 21 2018


ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡


የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡


ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡


ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሃይቁ ዓሣ እየተመረተ ወደ መሃል ሃገር እየተላከ መሆኑንን ሰምተናል፡፡


በስፍራው ዓሣ ወደ ማስገር ስራ በገቡ 12 ባለሃብቶች ከተደራጁ ወጣቶች ጋር በመሆን እንደሚሰሩ የነገሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የዓሣ ሃብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ቡሼን ቡፋ ናቸው፡፡


2018 ዓ.ምን ስንጀምር ከግድቡ እናመርታን ብለን ውጥን የያዝነው ከ9 ሺህ 600 ቶን ወይም 9.6 ኪሎ ግራም ዓሣ ያልበለጠ ነበር፤ ይሁንና እየተገባደደ ባለው ዓመት ማምረት የቻልነው 11 ሺህ 600 ቶን ወይም ከ11.6 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ነው ብለውናል፡፡


ወጣቶችን እያደራጀ ለዚህ ስራ እያሰማራ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ቡሼን ይህ የዓሣ ምርት የተገኘው ተደራጅተው ለዚህ ስራ በተሰማሩ 1 ሺህ 465 ወጣቶች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡


አሁን ያለንበት የክረምት ወቅት ለዓሣ ማስገር ስራ የተመቸ በመሆኑ ከህዳሴ ግድብ የንጋት ሃይቅ እስከ ክረምቱ ማብቂያ ከዚህም በላይ ይጠበቃል ተብሏል፡፡


ከዚህ ቀደም ምርቱ እንኳን ቢኖር የቤኒሻንጉል ክልል የሰላም ችግር ምርቱን እንደልብ ለማጓጓዝ አስቸጋሪ እንደነበር የሚያስታውሱት ግብርና ቢሮ የዓሣ ሃብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ቡሼን ቡፋ፤ አሁን ክልሉ ሰላማዊ ነው፤ምርቱን ወደ አዲስ አበባም ወደ አሶሳም እየጫንን ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡


በህዳሴው ግድብ የንጋት ሃይቅ ከፍተኛ ዓሣ የማምረት አቅም ቢኖርም ለምርቱ የሚሆኑ የማስገሪያ ማሽነሪዎችን ለማሟላት ትኩረት እንዳልተሰጠ ከዚህ ቀደምም መዘገባችን ይታወሳል፡፡


እንዲሟላላችሁ ለግብርና ሚኒስቴርና ለሌላው ስታቀርቡት የነበረው ጥያቄ መልስ አገኘ ወይ? ስንል የጠየቅናቸው አቶ ቡሼን፤ ጥያቄያቸው አሁንም መልስ እንዳላገኘ ነግረውናል፡፡


በዚህ አመት ለምርቱ መጨመር ያገዘው የማስገሪያ ማሽነሪዎችና ማቀዝቀዣ ያላቸውን የምርት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች በባለሃብቶቹ እየቀረበ በመሆን ነው ይላሉ፡፡


በመንግስት በኩል ለሚቀጥለው አመት እነዚህን የምርት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ለተደራጁ ማህበራት ለመግዛት ቃል ስለመገባቱም ጠቁመዋል፡፡


የንጋት ሃይቅ ዓመታዊ ዓሣ የማመምረት አቅም 15 ሺህ ቶን ወይም 15 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ሲሆን በመጪው ዓመት ከሃይቁ ለማምረት በእቅድ የተያዘው 12ሺህ 800 ቶን (12.8 ሚሊዮን ኪ.ግ) መሆኑንም ከሃላፊው ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....


ምንታምር ጸጋው

Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page