ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከካርበን ሽያጭ 4.8 ሚሊየን ዶላር ገቢ አገኘች፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ሐምሌ 22 2018
ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከካርበን ሽያጭ 4.8 ሚሊየን ዶላር ገቢ አገኘች፡፡

በአራት ዓመታት ውስጥ ከ140 ሺህ ቶን በላይ የካርበን ጋዝ ልቀት መቀነሱ ተሰምቷል፡፡
ይህ ገቢ የተገኘውም ከ2013-2017 ዓ.ም በተተገበረ የታዳሽ ሀይል ፕሮጀክቶች መሆኑም ተነግሯል።
ይህንን የነገሩን በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ አማካሪና የካርበን ገበያ አስተባባሪ አቶ መንሱር ደሴ ናቸው።
ኢትዮጵያ ላለፉት አራት አመታት በተገበረቻቸው የባዮጋዝና የፀሐይ ሃይል ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ገቢ እንድታገኝበት ከማድረግ ባሻገር የሀይል አቅርቦት የማያገኘው ህብረተሰብም ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
ወደ አየር ሊለቀቅ የነበረውን የሙቀት አማቂ ጋዝ እንዲቀንስ ማድረጉም ሌላኛው ውጤት ነው ይላሉ።
በባዮጋዝ እና በፀሐይ ሃይል ላይ የተሰሩ ፕሮጀክቶች ከጤና አኳያም የራሱን አውንታዊ ሚና እንዳበረከተም አቶ መንሱር ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ፍቅሩ አምባቸው
_edited.jpg)


Comments