የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።
- 30 minutes ago
- 1 min read
ሐምሌ 20 2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።
እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመጭውን የ25 አመት የሀይል ፍላጎት ለማወቅ የሚያግዝ ጥናት ማስጠናቱን ጠቅሷል፡፡
በፍጥነት እያደገ የመጣውን የሀይል ፍላጎት ለመሸከም፣ የኔትዎርክ ችግርን ለመፍታትና የሥርጭት ሥርዓትን ወደ ዘመናዊ እና ዲጅታል አሰራር ለማሸጋገር የ25 አመታት ሀገር አቀፍ የስርጭት ስርዓት ማሻሻያና ማስፋፊያ ማስተር ፕላን ጥናት መጠናቱ ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱም በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እና ሞኔንኮ ኢራን ኢንጅነሪንግ ኮንሰልቲንግ በተሰኘ የኢራን አማካሪ ድርጅት መጠናቱን ሲነገር ሰምተናል።
ማስተር ፕላኑ የመጪዎቹን 25 አመታት የሚሸፍን መሆኑ የተነገረ ሲሆን የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የኔትወርክ ማሻሻያ፣ ማስፋፊያ፣ ዲጂታል ሽግግርና ኢንቨስትመንት ፍላጎቶችን ለይቷል ተብሏል።
ጥናቱም 1 ሺህ 100 መጋቢ መስመሮች፣ 183 ሰብስቴሽኖች እና 79 ሺህ ኪ.ሜ ነባር መካከለኛ መስመር ዳሰሳ ማደረጉን ያነሳው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ቁጥር እድገትን፣ የነፍስ ወከፍ የኢነርጂ ፍላጎትን ጨምሮ የቴክኖሎጂ እድገት የሚጠይቀውን የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው ብሎታል።
ጥናቱ ውስጥ ከተካተቱት 1 ሺህ 100 መጋቢ መስመሮች 271 ያህሉ የቮልቴጅ መጠናቸው ያልተመጣጠነ መሆኑን የሚያሳየው የጥናቱ ውጤት፣ ከእነዚህ ውስጥ 182 ያህሉ የሀይል ጭነት የበዛባቸው እንደሆኑ ጠቁሟል።
በማሰራጫ መስመሮች ላይ በተጠናው ጥናት መሰረት ደግሞ 6 ሺህ 800 ትራንስፎርመሮች፣ 15 ሺህ 800 የመካከለኛ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች፣ 6 ሺህ 833 በአየር ላይ የተዘረጉ መስመሮች እና 638 መካከለኛ መስመር መቆጣጠሪያዎች ላይ ማስተካከያ ግኝት የተገኘባቸው እንደሆነ ተናግሯል።
እነዚህም እና ሌሎች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን መለየት ኢትዮጵያ በቀጣይ 25 አመታት አስተማማኝ የስርጭት ሥርዓት እና የሀይል አቅርቦት እንዲኖራት ያደርጋል ተብሎ እንደታመነበት አገልግሎቱ ተናግሯል።
ፋሲካ ሙሉ ወርቅ
_edited.jpg)




Comments