በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቀድላቸው ባንኮች የውጪ ምንዛሪ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ተነገረ።
- 1 hour ago
- 1 min read
መጋቢት 9/2018
በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቀድላቸው ባንኮች የውጪ ምንዛሪ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ተነገረ።
የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል።
አዋጁ ከደነገጋቸው ግዴታዎች አንዱ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ በሚቋቋም የአንድ መስኮት አገልግሎት ባንኮችም ገብተው አገልግሎት መስጠት አለባቸው የሚለው እንደሆነ ተጠቅሷል።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ 32 ባንኮች እንዳሉ ያመለከተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከእነዚህ መካከል ከ15 እስከ 20 የሚሆኑት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው ለመስራት የሚያስችላቸውን ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።
የዉጪ ባንኮችም ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠቅ ተናግሯል።

ከአዋጁ መወጣት በፊት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በዋናነት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው ለመስራት ፍቃድ የሚወስዱ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ተነግሯል።
የባንክ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ግን በዚያው በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ላሉ የማህበረሰብ አባላት ብቻ ነው ተብሏል።
በአንድ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚሰሩ ባንኮችን ቁጥር ብሄራዊ ባንክ ሊወስን እንደሚችልም ተጠቅሷል።
ባንኮቹ ቅርንጫፍ መክፈት ይችላሉ የተባለ ሲሆን ንዑስ ቅርንጫፍ ግን መክፈት እንደማይፈቀድላቸው ተመልክቷል፡፡
ብሄራዊ ባንክ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ለሚሰሩ የፋይናንስ ተቋማት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ በስካይ ላይት ሆቴል ውይይት እየተካሄደ ነው።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments