በጋሞ ዞን በየመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች አስክሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡
- 4 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 7/2018
በጋሞ ዞን ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡
የቀሪዎቹን አስከሬን ለማውጣት ሲደረግ የቆየው በቁፋሮ የታገዘ የማፈላለግ ስራም እንዲቆም መደረጉን ሰምተናል፡፡
ይህን ያለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ነው።
እንደ ቢሮው መረጃ ከሆነ አስክሬን የማፈላለግ ስራው ቆሞ የ44 ሰዎች አስከሬን አደጋው በተከሰተበት በዚያው ስፍራ የቀብር ቦታው ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል ተብሏል፡፡
እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው አስከሬኑ 7 ቀን አልፎታል በሚል ነው፡፡

በአደጋው ምክንያትም ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ ነግረውናል።
በጋሞ ዞን የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰዎችን ህይወት ከመቅጠፉ ባሻገር ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል ሲሉ ሀላፊው ነግረውናል።
በአደጋው ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ሰዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ከተለያዩ አካላት እየቀረበ መሆኑንም ተናግረዋል።
በጋሞ ዞን እና አካባቢው ተመሳሳይ አደጋ ዳግም እንዳይከሰት ስጋት የሆኑ ቦታዎችን የመለየት፣ በዝናብ ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችንም በሚመለከት የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ለማህበረሰቡ እየተላለፈ መሆኑን ኃላፊው አቶ ኃይለማርያም ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…
ፍቅሩ አምባቸው





Comments