የኢትዮጵያ ባንኮች አቅም እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይዋሃዱ ዘንድ ተመክረዋል።
- 2 days ago
- 1 min read
መጋቢት 9/2018
የኢትዮጵያ ባንኮች አቅም እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይዋሃዱ ዘንድ ተመክረዋል።
ግን ባንኮች እንዴት በመርጅ ኤንድ አክዩዜሽን ይዋሀዱ የሚለውን መስመር ለማሳየት ብሔራዊ ባንክ መንገድ መለየቱ ተሰምቷል።
አንዱ ባንክ እንዴት ሌላኛውን ይግዛው? የሚል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ እንደሆነ የብሔራዊ ባንክ ተናግሯል።
ይህም የሐገር ቤት ንግድ ባንኮች አቅም እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ፤ አንዱ ባንክ እንዴት ሌላኛውን መግዛት እንደሚችል የሚያግዝ የህግ ማዕቀፍ ነው።

በዚህ ጉዳይ የጠይቅናቸው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ይህ እየተዘጋጀ ያለው መንገድ ባንኮች እንዲዋሀዱ ይረዳቸዋል ብለዋል።
በተያያዘ ወሬ ፤ በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች በተለያየ አማራጭ ገብተው እንዲሰሩ ከተፈቀደ በኋላ አንዳንድ የውጭ ባንኮች የሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮችን ሼር ገዝተው ወደ ስራ ለመግባት ከባንኮች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑም ተሰምቷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments