top of page

በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ

  • 10 hours ago
  • 2 min read

መጋቢት 10/2018


በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ እና የህገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት የሚገታ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ።


በስራና ክህሎት ሚንስቴር እየተዘጋጀ ያለው ይህ ደንብ፣ በቤት ሰራተኞች ላይ የሚደርሱ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶችን ለመከላከል እንዲሁም የአሰሪዎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተነግረሯል።


ብዙ ጊዜ የቤት ሰራተኛ ሲባል ሰዉ የሚገነዘበዉ 70 በመቶ የሚሆኑትን ሴት የቤት ሰራተኞችን ብቻ ቢሆንም በዚህ ደንብ ግን አትክልተኛ፣ ሹፌሮችና ሌሎችም በመኖሪያ ቤት ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሰራተኛችን ጭምር እንደሚያካትት ተጠቁሟል።


በሚኒስቴሩ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የስራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ አዲሱ ደንብ በቀጣሪም በተቀጣሪም በኩል የሚነሱ ችግሮችና ፈተናዎችን የሚፈታ በተለያየ ጊዜ በሁለቱ መካከል ተደረጉ የሚባሉ አሰቃቂ ወንጀሎችንም ሚቀንስ እንደሆነ አስረድተዋል።


ደንቡ አለማቀፍ ስምምነቶችንና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችን በመዉሰድ የስራ ስዓት፣ የእረፍት ጊዜና ሌሎች መብቶች እንዲካተቱበት ሆኖ እየተዘጋጅ ነው ያሉት ሀላፊዉ ነገር ግን የቤት ሰራተኛነት ከቤት ዉስጥ ሆኖ የሚሰራ ስራ እንደመሆኑ መጠን ከሌሎች የስረ ዘርፎች ስለሚለይ የቀጣሪንና የሰራተኛን ጥብቅ ተግባቦት እንደሚጠይቅ አመላክተዋል።



ደንቡ ብዙ ጥናት ተደርጎበታል፣ ብዙ የሚመለከታቸዉ ተቋማትም ተሳትፈዉበታል የተባለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎንም በቴከኖሎጅ የታገዘ ሆኖ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከአሰራሩ በማስወጣት አሰሪና ተቀጣሪን በቀጥታ የሚያገናኝ እንዲሆን ታሰቦ እየተዘጋጀ እንደ ሆነም አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ ጠቁመዋል።


አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ ሰራተኛውም ሆነ አሰሪው በአቅራቢያቸው በሚገኝ ወረዳ በመቅረብ "የሰራተኛ መታወቂያ" ወይም Labor ID በማዉጣት ቀጣሪዉም እንዲሁ የአሰሪ መታወቂያ እንዲያወጡ በማድረግቀጥታ ሰራተኛ ከተቀጣሪ ጋር ያለምንም አማላጅ ተገናኝተው በዋጋና በስራ ሁኔታዎች ላይ ተስማምተዉ ውላቸውን በየወረዳው በሚገኘው የስራና ክህሎት ተወካይ አማካኝነት በህጋዊ መንገድ እንዲመዘገቡ የሚያግዝ ዘዴ እየተበጀ ነዉ ብለዋል ።

ለመጀመሪያ ጊዜ እየተዘጋጀ ነዉ በተባለዉ የቤት ሰራተኞች ደንብ ሁለቱም ወገን ተጠቃሚ ይሆኑበታል ተብሏል።


በፍትሐቤር ህግ ተጠቅሶ የሚገኘዉ አሽክርና ገረድ የሚለዉ ስያሜም ተገቢና ተስማሚ አይደል በሚል በዚህ ደንብ የግል አገልግሎት ቅጥር በሚል እንዲተካ ስለመደረጉም ሰምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..


ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page