top of page

የህክምና አገልግሎትን ያሻሽላሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን የሚያቀርቡ 8 ሀገራት ተቋሞቻቸውን የሚያሳትፉበት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው።

  • 3 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 9/2018

የህክምናውን ዘርፍ ያሳድጋሉ፣ የህክምና አገልግሎትን ያሻሽላሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን እና መፍትሄዎችን የሚያቀርቡ ከተለያዩ 8 ሀገራት ተቋሞቻቸውን የሚያሳትፉበት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው።


ከ10ኛው ኢትዮ ኸልዝ ጉባኤ ጎን ለጎን 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ፈጠራዎች ኤግዚቢሽን ከመጋቢት 24 እስከ 26/2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል ተብሏል።


ኤግዚቢሽኑ የሀገር ውስጥ የህክምና መሣሪያዎች፣ የመድኃኒት አምራቾች እና የጤና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማበረታታትና ለገበያ ለማቅረብ የሚረዳ መሆኑም ተነግሯል።


በተጨማሪም የሀገር ውስጥ አምራቾች ከዓለም አቀፍ አምራቾች ጋር እንዲተሳሰሩ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ እና በዘርፉ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የንግድ ተስስር እንዲፈጠር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎለታል።


ኤግዚቢሽኑን ጤና ሚኒስቴር፣ አርማወር ሀንሰን የምርምር ኢኒስቲትዩት እና ፕራና ኢቨንትስ በጋራ እንደሚያዘጋጁትም ሰምተናል።


ከ8 የአለም ሀገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉም ተነግሯል።


ሁነቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አቅራቢዎችን በማስተዋወቅ፣ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግርን በማምጣት ለዘርፉ ልማት በሚደረገው ጥረት ቁልፍ ሚና እንደሚኖረውም ታምኖበታል።


በተጨማሪም ከ40 በላይ የሞያ ማጎልበቻ (CPD) ስልጠናዎች፣ 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ እና ሳይንሳዊ ፎረሞች የኹነቱ አካል ናቸው ተብሏል።


ባንግላዲሽ፡ ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ አሜሪካ እና አዘጋጇ ኢትዮጵያን ጨምሮ የጉባኤው ተሳታፊዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page