''የኢራኑን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀላፊ ዓሊ ላርጃኒን ገድለነዋል'' እስራኤል
- 2 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 8/2018
የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የኢራኑን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀላፊ ዓሊ ላርጃኒን ገድለነዋል አሉ፡፡
ካትዝ እንደተናገሩት ላርጃኒ የተገደሉት እስራኤል ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ኢራን ውስጥ በፈፀመችው ድብደባ ነው፡፡

ዓሊ ላርጃኒ ከሁለት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ እና በእስራኤል ጣምራ ጥቃት የተገደሉትን የቀድሞውን ጠቅላይ መሪ አያቶላ ዓሊ ሐሚኒን ለመተካት በእጩነት ከቀረቡት አንዱ ነበሩ፡፡
አባታቸውን በመወከል በጠቅላይ መሪነት የተመረጡት ሞጅታባ ሐሚኒ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ዓሊ ላርጃኒ በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል ስለመባሉ እስካሁን ከኢራን በኩል ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ እንዳልተሰጠ ሬውተርስ ፅፏል፡፡





Comments