top of page

በኢትዮጵያ የኦዲት ስራ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከወን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ በገበያው ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል።

  • 7 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 7/2018

በሀገር የፋይናንስ ሥርዓት ከሚረበሹበት፤ ከሚታመሙበት ጉዳዮች መካከል አንደኛው የተዝረከረ የሂሳብ አያያዝና ጥራት የሌለው ጥንቅቅ ያላለ የኦዲት ሪፖርት ነው ።


የኦዲት ሪፖርት ጥራቱ የደረጃውን ጠብቆ ካልተሰራ ዞሮ ዞሮ የሕዝብ ጥቅም ያለባቸውን ተቋሞች መነካካቱ አይቀርም።


በፋይናንስ ሥርዓት በባንክ ፤ ማይክሮ ፋይናንስ ፤ኢንሹራንስና ሌላውም የሚደረገው የኦዲት ስራ የህዝብ ጥቅም የሀገርን ኢኮኖሚ በአንድም ሆነ በሌላ ስለሚነካ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመከራሉ።


በኢትዮጵያ የኦዲት ስራ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከወን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ በገበያው ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል።


በዚህም ምክንያት ምክንያታዊ የኦዲት ክፍያ ስራ ላይ እንዲውል ያግዛል የተባለ አዲስ መመሪያ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡

የኦዲት ስራ ደረጃው ዝቅ እንዲል ካደረጉበት ምክንያቶች አንደኛውም በገበያ ውስጥ የሚቀርበው በጨረታ ሰብሮ የሚገባው ዝቅተኛ የኦዲት ዋጋ አንዱ ነው ተብሏል ።


ለዚህም ኦዲተሮች ስራቸውን በጥራት እንዲያከናውኑ ምክንያታዊ የኦዲት ዋጋ ክፍያ መመሪያ ወደ ስራ ገብቷል።


ነገር ግን የማህበሩ አባል ያልሆኑና ሌሎች ግድ የለሽ ኦዲተሮች ፤ ይህን መመርያ ከመተግበር ይልቅ ፤ እኛ በዝቅተኛ ዋጋ እንሰራለን እያሉ ፤ ተቋሞችንና የህዝብን ጥቅም እየረበሹ ነው ተብሏል ።


ለመሆኑ ምክንያታዊ የኦዲት ዋጋ ክፍያ ሲባስ ምን ማለት ነው?


አቶ ዳንኤል ጌታነህ የኢትዮጵያ የውጭ ኦዲተሮች ማህበር ፕሬዝዳንት ናቸው።


እሳቸውን ስለዚሁ ጉዳይ ዝርዝር እንዲነግሩን ጠይቀናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ተህቦ ንጉሴ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page