top of page


የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከ20.5 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ባለው በኮፔይ ኢ - ብር እስካሁን ከ4.8 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ተናገረ።
ጥር 6/2018 የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከ20.5 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ባለው በኮፔይ ኢ - ብር እስካሁን ከ4.8 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ተናገረ። ባንኩ ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሬ ከባንኩ በኩል ለተቀበሉ ደንበኞቹ ባዘጋጀው የውጭ ምንዛሪ የሎተሪ እድለኞችን ሸልሟል፣ ዲጂታል ሎተሪ ሽያጭ እንደሚጀምር ተናግሯል። የተላከላቸውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በመቀበላቸው እድለኛ የሆኑ ደንበኞች አንድ ዘመናዊ የቤት መኪና፣ 2 የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ፣10 ላፐቶፖች፣ 10 ቴሌቪዥኖችና 40 ስማርት ስልኮች በአጠቃላይ 63 ሸልማቶች ዕድለኞች ተበርክተዋል። የባንኩ ኦፕሬቲንግ ተጠባባቂ ቺፍ አፊሰር አቶ አብዲ ፈቀደ ባንኩ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎትና ታምሶል ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር፣ በኮፔይ ኢ-ብር
Jan 141 min read


በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት በባንክ ብድር ተገንብተው በጦርነቱ የወደሙ ፕሮጀክቶች እዳ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ብሔራዊ ባንክን በደብዳቤ ጠየቀ፡፡
ጥር 5/2018 በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት በባንክ ብድር ተገንብተው በጦርነቱ የወደሙ ፕሮጀክቶች እዳ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ብሔራዊ ባንክን በደብዳቤ ጠየቀ፡፡ የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት የክልሉ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ብድር ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ማለትም ከ2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ከነበረበት 32 ቢሊዮን ከነወለዱ አሁን ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል ብሏል፡፡ ምክርቤቱ በክልሉ ለንግድ እና ኢንቨስትመንት የተወሰዱ የባንክ እዳዎች የንግዱ ማህበረሰብ መክፍል ስለማይችል ከፕሪቶሪው የሰላም ስምምነት በኋላ የመክፈያ ጊዜ ገደብ ለ18 ወራት ተራዝሞለት እንደነበር የምክርቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ በሪሁ ሃፍቱ ተናግረዋል፡፡ ንጋዴዎቹም ሆኑ አልሚዎቹ በተሰጣቸው 18 ወራት ስራ
Jan 132 min read


በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሳምንት በኋላ በሚከበረው የጥምቀት በዓልም የተሻለ የቱሪስት ፍሰት እንደሚኖር ዝግጅት ተደርጓል፡፡
ጥር 5/2018 ከፍ ያለ የውጭ ቱሪስት ከሚገኝባቸውና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንቅስቃሴም ሞቅ ከሚልባቸው ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው፡፡ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሳምንት በኋላ በሚከበረው የጥምቀት በዓልም የተሻለ የቱሪስት ፍሰት እንደሚኖር ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ለቱሪስቶች የተሻለ የትራንስፖርት አማራጭ እንዲኖርና ለብዙዎችም ጊዜያዊ የስራ እድል እንዲፈጠር እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. በረከት አካሉ YouTube : https://url-shortener.me/2DTR Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY WhatsApp : https://url-shortener.me/2D
Jan 131 min read


ሜታ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የአውስትራሊያ አዳጊ ወጣቶችን ገፆቹን እንዳይጠቀሙ አደረጋቸው፡፡
ጥር 5/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አውስትራሊያ የእነ ፌስ ቡክ እና ኢኒስታግራም የማህበራዊ ድረ ገፆች እናት ኩባንያ (ሜታ) ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የአውስትራሊያ አዳጊ ወጣቶችን ገፆቹን እንዳይጠቀሙ አደረጋቸው፡፡ ክልከላው በአውስትራሊያ ስራ ላይ የዋለውን ህግ መሰረት ያደረገ መሆኑን ABC ፅፏል፡፡ አዲሱ የአውስትራሊያ ህግ እድሜያቸው ከ16 አመታት በታች የሆነ አዳጊ ወጣቶች በጭራሸ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዳይገለገሉ የሚከለክል ነው፡፡ አዳጊ ወጣቶች ክልከላውን ተላልፈው የማህበራዊ ትስስር ገፆቹን ሲገለገሉ ከተገኙ አገልግሎት አቅራቢያ ኩባንያዎች የገንዘብ ቅጣት እንዲቆነደዱ ያደርጋል፡፡ አዳጊ ወጣቶችን የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዳይገለገሉ በማድረግ አውስትራሊያ ቀዳሚዋ አገር ሆናለች፡፡ #ሶማሊያ የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት ከተባበ
Jan 132 min read


ሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ በጊዜው ገቢ የማያደርጉ የግል ድርጅቶች ራሳቸውን ላልተገባ ቅጣት እና ወለድ እየዳረጉ ነው ተባለ።
ጥር 5/2018 ሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ በጊዜው ገቢ የማያደርጉ የግል ድርጅቶች ራሳቸውን ላልተገባ ቅጣት እና ወለድ እየዳረጉ ነው ተባለ። ሃብት ንብረታቸውን ሸጦ የጡረታ መዋጮው ገቢ እንዲሆን እስከ ማድረግ የሚደርስ እርምጃ ሊወስድባቸው እንደሚችልም የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አሳስቧል። አንድ እና ከአንድ በላይ ሠው የቀጠረ ማንኛውም የግል ድርጅት ሠራተኛውን ወደ ጡረታ አቅድ የማስገባት ግዴታ እንዳለበት የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አሳስቧል፡፡ ሠራተኛው ወደ ጡረታ ስርአቱ መግባት ያለበት ከተቀጠረ ከአርባ አምስት ቀናት በኋላ እንደሆነ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባተ ምትኩ ተናግረዋል። አብዛኞቹ ቀጣሪ ድርጅቶች ግን ሠራተኛው ኮንትራት ነው ወይም ጊዜያዊ ነው በሚል ይህን ግዴታ ያለ ማክበር ዝንባ
Jan 131 min read


የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች በመንግስት አካላት እና በፖሊሲ አውጪዎች ላይ ጫና በማሳደር ስለ ትንባሆ አሳሳች መልክቶችን በማሰራጨት ንግዳቸውን ለማስፋፋት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።
ጥር 5/2018 የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች በመንግስት አካላት እና በፖሊሲ አውጪዎች ላይ ጫና በማሳደር ስለ ትንባሆ አሳሳች መልክቶችን በማሰራጨት ንግዳቸውን ለማስፋፋት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል። ኢንዱስትሪዎቹ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ነን በሚል፣ የበጎ አድራጎት ስራን በማስታከክ እና በሌሎች ዘዴዎች የትምባሆ ስርጭትን ለማስፋፋት እየሰሩ ነው ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በዣንጥላዎች፣ በቲሸርቶች እና በመሰል ምርቶች ላይ ማስታወቂያዎችን እየሰሩ መሆኑም ተጠቅሷል። የእነዚህን የኢንዱስትሪዎች ጫናን በመቋቋሙና ዘርፋን በመቆጣጠሩ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የተሻለ ስራ ሰርቻለሁ ብሏል። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 100 ሀገራት በተካተቱበት ጥናት፤ ኢትዮጵያ የትምባሆ ምርቶችን በመቆጣጠሩ የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግባለች ተብሏል። በዚህ ጥናት ኢትዮጵያ የትምባሆ
Jan 131 min read


10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቀው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ።
ጥር 2/2018 10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቀው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ። ግንባታውን ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው፡፡ የቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ይኽም ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ የኢንደስትሪ ማስፋፊያ አጀንዳ እና የረጅም ዘመን የአቪየሽን ስትራቴጂ ጋር የተናበበ ነውም ሲሉም አክለዋል። ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያጠናክራል። በAfCFTA ማህቀፍ የአፍሪካን የማገናኘት አቅም ይጨምራል ተብሏል። ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎሜትር አካባቢ የምትገኘውና 1910 ሜትር ከፍታ ያላት ቢሾፍቱ ለአውሮፕላኖች ሥራ የተመቸ ከባቢ ያላት ሲሆን
Jan 101 min read


በአዲስ አበባ አንዳንድ የወረዳ አመራሮች ተገልጋዩን ያመነጫጭቃሉ፣ ለጥያቄም ምላሽ አይሰጡም የሚል ቅሬታ ቀረበባቸው።
ጥር 2/2018 በአዲስ አበባ አንዳንድ የወረዳ አመራሮች ተገልጋዩን ያመነጫጭቃሉ፣ ለጥያቄም ምላሽ አይሰጡም የሚል ቅሬታ ቀረበባቸው። የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በአግባባቡ ስራቸውን መስራት ያልቻሉ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አንደሆነ አስረድቷል፡፡ ቅሬታው የቀረበባቸው የከተማው የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በስድስት ወራት የስራ ክንውን ዙሪያ ትናንት ቅዳሜ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከሚመለከታቸው የከተማው ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው። የወይይቱ ተሳታፊዎች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወረዳ ሲያቀኑ በሁሉም ባይሆንም በአንዳንድ አመራሮች ማመነጫጨቅ እና ማንገላታት እንደሚያጋጥማቸው እንዲሁም ለጥያቄያቸው ምላሽ እንደሚነፍጓቸው ተናግረዋል። ወይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አማካሪ
Jan 101 min read


የታህሳስ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 9.7 በመቶ ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናገረ።
ጥር 1/2018 የታህሳስ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 9.7 በመቶ ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናገረ። የታህሳስ 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን 9.7 በመቶ ደርሷል፤ ይህም በታህሳስ 2017 ዓ.ም ከተመዘገበው 17.0 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። የወር ከወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በታህሳስ 2018 ዓ.ም በ0.3 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር የ0.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች የዋጋ ግሽበት 9.8 በመቶ የደረሰው በዋናነት የአትክልት፣ የሥጋ፣ የስኳር እና የጣፋጭ ምግቦች፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ የፍራፍሬ፣ የዘይትና የቅባት እንዲሁም የሌሎች የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመሩ ነው። በሌላ በኩል የዳቦ እና የጥራጥ
Jan 91 min read
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡
ጥር 1/2018 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡ ይህም የሚሰጡት ስልጠና ጥራት እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠቅሰዋል፡፡ ባለፈው አመት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ወጥቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ፖሊሲው ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት እራሳቸውን በፋይናንስ እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ አማራጮችን ያስቀመጠ ሲሆን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው በሚያሰለጥኑበት ዘርፍ የንግድ አገልግሎት እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡ በሚዛን የግብርና ኮሌጅ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ አቶ ካሳሁን አይከን ይሄ ለተቋማቱ ምን ይዞላቸው ይመጣል? ስንል ጠይቀናቸዋል። አቶ ካሳሁን የስልጠና ጥራት እንዲኖር ፣ በፋይናንስ እራሱን የቻለ
Jan 91 min read


የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡
ጥር 1/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ኮሎምቢያ የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡ ጉስታቮ ፔትሮ በአሜሪካ የጦር ጣልቃ ገብነት ስጋት ገብቶኛል ያሉት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቬኔዙዌላ ላይ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ የአገሪቱን ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮን አሳግታ ወደ ኒውዮርክ ማስወሰዷ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ወዲህ በርካታ አገሮች በአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ክፉኛ ስጋት እንደገባቸው ይነገራል፡፡ በአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ስጋት ገብቶኛል የሚሉት የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የዋይት ሐውስን አስተዳደር በግላጭ በመንቀር ይታወቃሉ፡፡ ትራምፕ እንደ ቬኔዙዌላ ሁሉ በኮሎምቢያም ላይ ሲዝቱ መቆየታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሶማሊያ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ሹሞቹ
Jan 92 min read


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለተጠቃሚዎች እራሱ ስጋ ለማቅረብ ሚያስችለውን ጥናት እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡
ታህሳስ 30/2018 የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለተጠቃሚዎች እራሱ ስጋ ለማቅረብ ሚያስችለውን ጥናት እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡ ድርጅቱ ለገና በዓል 5,164 የቁም እንስሳት እርድ መፈፀሙን ነግሮናል፡፡ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል አስካሁን ድረስ ከደንበኞች ከበዓል እርድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳልቀረበ ይናገራሉ፡፡ ከበዓሉ ቀደም ባለው ጊዜ ድርጁቱ በቂ ዝግጅት አድርጎ ነበር ያሉት አቶ አታክልቲ ስጋውን ለደንበኞች ለማቅረብ የሚገለገሉባቸው መኪኖችንም እንቅስቃሴ በካሜራ እና በጂፒኤስ ሲከታተሉ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ህገወጥ የቁም እንስሳት እርድ ከተማ ውስጥ እንዲቀንስ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶች ወደ ሸገር ከተማ በመሄድ ህገወጥ
Jan 81 min read


በአዲስ አበባ በመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ስራው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ
ታህሳስ 30/2018 በአዲስ አበባ በየጊዜው የመንገድ ግንባታዎች እንዲሁም ጥገናዎች ቢደረጉም በመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ግን ስራው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ምህረት ስዩም የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1 WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O X : https://x.com/shegerfm?s=2
Jan 81 min read


ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጤና፣ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና በሌሎችም ዘርፎች ምርምር ለማድረግ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን ስትጠቀም ነበረ ተባለ፡፡
ታህሳስ 30 2018 ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጤና፣ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና በሌሎችም ዘርፎች ምርምር ለማድረግ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን ስትጠቀም ነበረ ተባለ፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ
Jan 81 min read


በዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት 32 ዓመት በተለያየ የስራ ሀላፊነት ያገለገሉት ኢትዮዽያዊው አበበ አዕምሮ ሥላሴ በጡረታ ሊገለሉ እንደሆነ ተሰማ
ታህሳስ 30/2018 በከፍተኛ ደረጃ በኢኮኖሚ ባለሞያነት፣ በዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት (IMF) 32 ዓመት በተለያየ የስራ ሀላፊነት ያገለገሉት ኢትዮዽያዊው አበበ አዕምሮ ሥላሴ፤ ከ3 ወር በኋላ በጡረታ ሊገለሉ እንደሆነ ተሰማ። አቶ አበበ በዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት IMF ከ 30 ዓመት በላይ በተለያየ ኃላፊነት ፣ የባለፉትን 10 ዓመታት ደግሞ የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ ነው። በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ቀረፃ እና ትንተና፣ በፋይናንስና በገንዘብ ነክ ፖሊሲ ጉዳዮች፣ በዕዳ ሽግሽግ፣ አጠቃላይ በገንዘብ ቁጥጥር እና ፊስካል ፖሊሲ ሰርተዋል። የ IMF ዋና ዳይሬክተር፣ ክሪስታሊና ጆርጂየቫ፣ አበበ አዕምሮ ስላሴ ከአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተርነት ከ3 ወር በኋላ ይገለላሉ ብለዋል። ከ2008 ጀምሮ በIMF አፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር ሆነው ያገ
Jan 81 min read


ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት ሹመት በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ፀደቀ።
ታህሳስ 28/2018 ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት ሹመት በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ፀደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመቱን ያጸደቀው 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን እንዲመሩ የተሾሙት ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ ያለፈውን አንድ ዓመት ያህል ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር )ይተካሉ። ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተነግሯል። ዛሬ ሹመታቸው የጸደቀላቸው ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ ከ20 ዓመታት በላይ በመገናኛ ብዙሃን እና ተያያዥ ሞያ ላይ የቆዩ መሆናቸው ተነግሯል። አዲሷ ተሿሚ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በውጪ ቋንቋ እና ስነ ፁሁፍ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያ
Jan 61 min read


በሀገር ውስጥ ላቦራቶሪዎች ጥራታቸው መፈተሽ የማይችሉ ምርቶች ከመነሻ ሀገር የጥራት ማረጋገጫ ይዘው እንደመጡ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡
ታህሳስ 27/2018 በሀገር ውስጥ ላቦራቶሪዎች ጥራታቸው መፈተሽ የማይችሉ ምርቶች ከመነሻ ሀገር የጥራት ማረጋገጫ ይዘው እንደመጡ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡ ጀነሬተሩ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና ሌላውም በዚህ የፍተሻ ሥርዓት እንዲያልፍ ተወስኗል፡፡ ይህ ደግሞ ተከልሶ የመጣ ፣ ሥርዓት ፣ ከአስመጪዎች በኩል ግን የሚነሳበት ጥያቄ አለ፡፡ ለመሆኑ አሰራሩ ተግባራዊ የሚሆነው እንዴት ነው? ያስፈለገውስ ለምን ይሆን? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….. ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Jan 51 min read


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 6 ወራት ለቀሩት ሀገራዊ ምርጫ እንዴት እየተሰናዱ ይሆን?
ታህሳስ 27/2018 ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን ለሚካሄደው ቀን ቆርጣለች፡፡ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንቢያ አንዱ መንገድ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ የምርጫ ወቅት የዜጎች ሰብአዊ መብት እንዳይታፈን ተፎካካሪዎችም ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲያስረዱ ማድረግ መቻል ሥርዓቱን ነፃ መሆን አንዱ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ሰብአዊ መብት ለማስከበር የቆምን ነን የሚሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 6 ወራት ለቀሩት ሀገራዊ ምርጫ እንዴት እየተሰናዱ ይሆን? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….. ምህረት ስዩም የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Jan 51 min read


''በገና በዓል ወቅት የሀይል መቆራረጥ እንዳይፈጠር የቅድመ ዝግጅት ስራዬን አጠናቅቄአለሁ'' የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ታህሳስ 27/2018 በገና በዓል ወቅት የሀይል መቆራረጥ እንዳይፈጠር የቅድመ ዝግጅት ስራዬን አጠናቅቄአለሁ ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ። በበዓሉ እለት እና በዋዜማው የሀይል መቆራረጥ አንዳይኖርም አስቀድሞ የጥገና ስራ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በበዓሉት ወቅት ይፈጠሩ የነበሩ የሀይል መቆራረጦች ለማስቀረት እየሰራ መሆኑን የተናገረው አገልግሎቱ ረቡዕ ታህሳስ 29 ቀን በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሚከበረው የገና በዓልም ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር አስቀድሜ ስራዎችን ሰርቻለሁ ብሏል። አገልግሎቱ ይህንን ያለው የገና እና የጥምቀት በዓላትን በማስመልከት በተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። የገና በዓል ከሌሎች በዓላት በበለጠ በደንበኞች ዘንድ የሀይል አጠቃቀሙ ክፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ
Jan 52 min read
በኢትዮጵያ አብዛኛው የፋይናንስ ተቋም አሰራሩ አንድ ዓይነት ነው።
ታህሳስ 27/2018 በኢትዮጵያ አብዛኛው የፋይናንስ ተቋም አሰራሩ አንድ ዓይነት ነው። በተለይ በዓል በመጣ ግዜ ፤ በዓሉን ታሳቢ በማድረግ የብድር አገልግሎት የሚሰጡ የፋይናንስ ተቋም ቁጥራቸው ቢጨምር ፤ አንዛኛውን ሰው በፋይናንስ ለማካተት አንደኛው መንገድ ይሆናል ይባላል። በበዓል ወቅት እና የማህበራዊ አገልግሎት ጊዜ ለአንድ ቀንም ቢሆን አስቸኳይ የፋይናንስ አቅርቦት ለማግኘት አብዛኛው የፋይናንስ ተቋም ብድር ሲሰጥ አይታይም፡፡ ይሁንና የማህበራዊ እና የበዓል ሰሞን ወጭዎችን ለመሸፈን የሚያስፈልግ የፋይናንስ አስቸኳይ ብድር አገልግሎት ስራ መጀመሩን ሰምተናል፡፡ ይህ የፋይናንሰ አቀባይ ምንዳ የገንዘብ ቁጠባና ህብረት ስራ ማህበር ይባላል። ደንበኞች ይህን አገልግሎት በአጭሩ እንዴት ያገኙታል? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ተህቦ ንጉ
Jan 51 min read


የይዞታ ማረጋገጫ ሳይኖር፤ የንብረት ታክስ እንዲከፈል የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ
ታህሳስ 27/2018 መንግስት የባለቤትነት መብት የሌላቸው ሰዎች የይዞታ ማረጋገጫ ባይኖራቸውም የንብረት ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ እያሰናዳ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ለመሆኑ የባለቤትነት መብት በሌለበት ሁኔታ ለይዞታ የንብረት ታክስ እንዲከፈል ማድረግ ምን ያክል ትክክለኛ አካሄድ ይሆናል? የንብረት ታክስ የሚከፍለው ግለሰብስ በሂደት መብት እንዲፈጠርለት አያደርግም ወይ? የሚል ጥያቄም ይነሳል፡፡ የህግ ባለሞያ አነጋግረናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw Telegram : https://t.me/S
Jan 51 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








