የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
ጥር 1/2018
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡
ይህም የሚሰጡት ስልጠና ጥራት እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠቅሰዋል፡፡
ባለፈው አመት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ወጥቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ፖሊሲው ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት እራሳቸውን በፋይናንስ እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡
ለዚህም የተለያዩ አማራጮችን ያስቀመጠ ሲሆን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው በሚያሰለጥኑበት ዘርፍ የንግድ አገልግሎት እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡
በሚዛን የግብርና ኮሌጅ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ አቶ ካሳሁን አይከን ይሄ ለተቋማቱ ምን ይዞላቸው ይመጣል? ስንል ጠይቀናቸዋል።
አቶ ካሳሁን የስልጠና ጥራት እንዲኖር ፣ በፋይናንስ እራሱን የቻለ የሙያ ተቋም እንዲፈጠር ያግዛል ይላሉ፡፡
ህብረተሰቡ ስለ ቴክኒክና ሙያ ስለጠና ተቋማት ያለው አመለካከት ከዚህ ቀደም እንዲያንስ ያደረገው ባላቸው የተራራቁ ግንኙነት ነው አሁን ስራ ላይ የዋለው እስትራቴጂ ይህንን ክፍተት የሚሞላ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ይሰሩ የነበሩ ስራዎች በተቋማት አመራሮች በጎ ፈቃደኝነት ነው በተለይም ተጨማሪ ገቢን ከመፍጠርና ከህብረተሰቡ ጋር የተሻለ ቁርኝት ከመፍጠር አኳያ ሲሉም ያስረዳሉ አቶ ካሳሁን አይከን፡፡
ሌላው በዚህ ስትራቴጂ ከተጠቀሱ ጉዳዮች መካከል የክህሎት ባንክ ማቋቋምን የተመለከተ ነው፡፡
አቶ ካሳሁን እንደ ሀገር የክህሎት ባንክ መቋቋሙ በሀገሪቱ ያሉ ክህሎቶች እንዲታወቁ ፣ ወጥ ሆነ መመዘኛ ለማውጣትና እነዚህ ሙያዎች ወደ ቢዝነስ ለመቀየርና ለስራ ለማዋል ጥሩ እድል ይሰጠናል ሲሉም ነግረውናል፡፡
በሚዛን የግብርና ኮሌጅ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ አቶ ካሳሁን አይከን እነዚህ ሁለቱ ጉዳዮች በአግባቡ ወደ ስራ ከቀየርን የቴክኒክና ሙያው ዘርፍ ህብረተሰቡን በተሻለ መንገድ እንዲጠቅሙ ያደርጋል ይላሉ፡፡
የሰው ሀይልን ብቻ ሳይሆን በተሰማሩበት የትምህርት ዘርፍ አምራች የሆኑ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንድናይም ያግዘናል ብለዋል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








