top of page

በአዲስ አበባ አንዳንድ የወረዳ  አመራሮች  ተገልጋዩን ያመነጫጭቃሉ፣ ለጥያቄም ምላሽ አይሰጡም የሚል ቅሬታ ቀረበባቸው።

  • Jan 10
  • 1 min read

ጥር 2/2018

 

በአዲስ አበባ አንዳንድ የወረዳ  አመራሮች  ተገልጋዩን ያመነጫጭቃሉ፣ ለጥያቄም ምላሽ አይሰጡም የሚል ቅሬታ ቀረበባቸው።

 

የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በአግባባቡ ስራቸውን መስራት ያልቻሉ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አንደሆነ አስረድቷል፡፡

 

ቅሬታው የቀረበባቸው የከተማው የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በስድስት ወራት የስራ ክንውን ዙሪያ ትናንት ቅዳሜ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከሚመለከታቸው የከተማው ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።

የወይይቱ ተሳታፊዎች አገልግሎት ለማግኘት ወደ  ወረዳ ሲያቀኑ በሁሉም ባይሆንም በአንዳንድ አመራሮች ማመነጫጨቅ እና  ማንገላታት እንደሚያጋጥማቸው እንዲሁም ለጥያቄያቸው ምላሽ እንደሚነፍጓቸው ተናግረዋል።

 

ወይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ በበኩላቸው ሁሉም አመራሮች ሃላፊነት የተሰጣቸው ህዝቡን ወይንም ተገልጋይውን  በቅንንት አንዲገለግሉ መሆኑንን ተናግረው በአግባባቡ ስራቸውን መስራት ያልቻሉ ሃላፊዎች ላይ በቁጥር በይጠቅሱም እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስረድተዋል።

 

በሌላ በኩል የከተማው ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን  የከተማውን ሰላም ለማረጋጋጥ  ተቋማት የደህንነት ካሜራ በህጻዎች ላይ  እንዲገጥሙ "የውዴታ ግዴታ"ተሰጥቶታል ፣በየመንደሩ  ደግሞ የተሻለ አቅም ያለው ገለሰብ ተለይቶ አማካኝ ቦታ ላይ የደህንነት ካሜራ የመግጠም ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page