top of page

የታህሳስ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 9.7 በመቶ ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • 9 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 1/2018


የታህሳስ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 9.7 በመቶ ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናገረ።


የታህሳስ 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን 9.7 በመቶ ደርሷል፤ ይህም በታህሳስ 2017 ዓ.ም ከተመዘገበው 17.0 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።


የወር ከወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በታህሳስ 2018 ዓ.ም በ0.3 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር የ0.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።


የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች የዋጋ ግሽበት 9.8 በመቶ የደረሰው በዋናነት የአትክልት፣ የሥጋ፣ የስኳር እና የጣፋጭ ምግቦች፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ የፍራፍሬ፣ የዘይትና የቅባት እንዲሁም የሌሎች የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመሩ ነው።

በሌላ በኩል የዳቦ እና የጥራጥሬዎች የዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር በነበረበት ደረጃ ቀጥሏል ሲል አስረድቷል።


ምግብ ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት 9.6 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ ለዚህም አስተዋፅዖ ያደረጉት ትራንስፖርት (17.6 በመቶ)፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ (10.4 በመቶ)፣ ኮሚኒኬሸን (13.9 በመቶ)፣ የቤት እቃዎች (12.5 በመቶ)፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች (13.8 በመቶ) እንዲሁም ልዩ ልዩ እቃዎችና አገልግሎቶች (21.5 በመቶ) ሆነው ተመዝግበዋል።


ከዓመት ዓመት እና ከወር እስከ ወር ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ዓመት ጋርሲነጻጸር ቀንሷል ሲል መግለጫው አስረድቷል።


ከታህሳስ 2017 ዓ.ም ጀምሮ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ እየቀነሰ መምጣቱ፣ የዋጋ መረጋጋት ትርጉም ባለው መልኩ እየተሻሻለ መሆኑን የሚያሳይ ጠቃሚ ምልክት ነው ሲል የስታትስቲክስ አገልገሎት ጠቅሷል::


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ  እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡

ጥር 1/2018   የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ  እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡   ይህም የሚሰጡት ስልጠና ጥራት እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠቅሰዋል፡፡   ባለፈው አመት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ወጥቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡   ፖሊሲው ው

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page