top of page

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለተጠቃሚዎች እራሱ ስጋ ለማቅረብ ሚያስችለውን ጥናት እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

ታህሳስ 30/2018


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለተጠቃሚዎች እራሱ ስጋ ለማቅረብ ሚያስችለውን ጥናት እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡


ድርጅቱ ለገና በዓል 5,164 የቁም እንስሳት እርድ መፈፀሙን ነግሮናል፡፡


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል አስካሁን ድረስ ከደንበኞች ከበዓል እርድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳልቀረበ ይናገራሉ፡፡


ከበዓሉ ቀደም ባለው ጊዜ ድርጁቱ በቂ ዝግጅት አድርጎ ነበር ያሉት አቶ አታክልቲ ስጋውን ለደንበኞች ለማቅረብ የሚገለገሉባቸው መኪኖችንም እንቅስቃሴ በካሜራ እና በጂፒኤስ ሲከታተሉ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ህገወጥ የቁም እንስሳት እርድ ከተማ ውስጥ እንዲቀንስ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶች ወደ ሸገር ከተማ በመሄድ ህገወጥ የእንስሳት እርድ ይፈፅማሉ ብለዋል አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል፡፡


ችግሩን ለመፍታት ከዚህ ቀደም ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር ክፍተቶች ነበር አሁን ግን አብረን መስራት ጀምረናል ይላሉ፡፡


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አሁን እየሰራ ካለው ስራ በተጨማሪ ስጋን ለተጠቃሚዎች እራሱ ለማቅረብ የሚያስችለው አሰራር ለመዘርጋት ጥናት እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ተናግረዋል፡፡


ጥናቱ ተጠናቆ በሚቀመጠው መፍትሄ በመነሳት ቄራዎች ድርጅት ሉካንዳቤቶት አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አሁን ላይ የቁም እንስሳት እርድን  አገልግሎት እየሰጠሁ ነው  ያለ ሲሆን የስጋ ተረፈምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገብያዎች እያቀረበ መሆኑን አቶ አታክልቲ ጠቅሰዋል፡፡


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Recent Posts

See All
 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ  እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡

ጥር 1/2018   የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ  እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡   ይህም የሚሰጡት ስልጠና ጥራት እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠቅሰዋል፡፡   ባለፈው አመት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ወጥቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡   ፖሊሲው ው

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page