ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት ሹመት በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ፀደቀ።
- sheger1021fm
- 2 days ago
- 1 min read
ታህሳስ 28/2018
ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት ሹመት በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ፀደቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመቱን ያጸደቀው 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው።

ዛሬ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን እንዲመሩ የተሾሙት ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ ያለፈውን አንድ ዓመት ያህል ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር )ይተካሉ።
ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተነግሯል።

ዛሬ ሹመታቸው የጸደቀላቸው ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ ከ20 ዓመታት በላይ በመገናኛ ብዙሃን እና ተያያዥ ሞያ ላይ የቆዩ መሆናቸው ተነግሯል።
አዲሷ ተሿሚ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በውጪ ቋንቋ እና ስነ ፁሁፍ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከህንድ በሶሾዮሎጂ ተመርቀዋል ተብሏል።
ዛሬ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን እንዲመሩ የተሾሙት ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ፤ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር እና ኤዲተር በመሆን፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮፖሬሽን በተለያዩ የስራ ዘርፎች አገልግለዋል ሲባል ሰምተናል።
የዛሬው ሹመታቸው እሰኪጸድቅ ድረስ ደግሞ የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ቢሮ በምክትል ኃላፊ መዕረግ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር ተብሏል።
ያሬድ እንዳሻው








