top of page

10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቀው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ።

  • Jan 10
  • 1 min read

ጥር 2/2018


10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቀው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ።


ግንባታውን ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው፡፡


የቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።


ይኽም ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ የኢንደስትሪ ማስፋፊያ አጀንዳ እና የረጅም ዘመን የአቪየሽን ስትራቴጂ ጋር የተናበበ ነውም ሲሉም አክለዋል።


ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያጠናክራል።


በAfCFTA ማህቀፍ የአፍሪካን የማገናኘት አቅም ይጨምራል ተብሏል።


ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎሜትር አካባቢ የምትገኘውና 1910 ሜትር ከፍታ ያላት ቢሾፍቱ ለአውሮፕላኖች ሥራ የተመቸ ከባቢ ያላት ሲሆን መዳረሻቸውን ኢትዮጵያ ላደረጉም ሆነ ለትራንዚት መንገደኞች ብቁ ሁኔታ ያላት መሆኑ ተጠቅሷል።


የመጀመሪያው ምዕራፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሥራ በአመት 60 ሚሊዮን ተጓዦችን የሚያስተናግድ ሲሆን ሲጠናቀቅም አፍሪካን ከአለም ቀዳሚ የአየር ትራንስፖርት መነኻሪያዎች አንዷ የሚያደርጋትን በአመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ላይ ይደርሳል።

1 Comment


David Solano
David Solano
Feb 05

Young people congregate at Cool Games Free to play, socialize, and unwind away from screens. Let's go there and investigate how games can ignite love, happiness, and friendship while creating a welcoming, lively, and dynamic community.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page