top of page

በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት በባንክ ብድር ተገንብተው በጦርነቱ የወደሙ ፕሮጀክቶች እዳ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ብሔራዊ ባንክን በደብዳቤ ጠየቀ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 minutes ago
  • 2 min read

ጥር  5/2018

 

በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት በባንክ ብድር ተገንብተው በጦርነቱ የወደሙ ፕሮጀክቶች እዳ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ብሔራዊ ባንክን በደብዳቤ ጠየቀ፡፡

 

የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት የክልሉ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ብድር ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ማለትም ከ2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ከነበረበት 32 ቢሊዮን ከነወለዱ አሁን ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል ብሏል፡፡

 

ምክርቤቱ በክልሉ ለንግድ እና ኢንቨስትመንት የተወሰዱ የባንክ እዳዎች የንግዱ ማህበረሰብ መክፍል ስለማይችል ከፕሪቶሪው የሰላም ስምምነት በኋላ የመክፈያ ጊዜ ገደብ ለ18 ወራት ተራዝሞለት እንደነበር የምክርቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ በሪሁ ሃፍቱ ተናግረዋል፡፡

 

ንጋዴዎቹም ሆኑ አልሚዎቹ በተሰጣቸው 18 ወራት ስራ ሰርተው እዳቸውን የመክልፍ አቅም ይኖራቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም በወቅቱ ሳይከፍሉ በመቅረታቸው እና ጋዴው ያስያዘውን ቋሚ ንብረት ባንኮች በሃራጅ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ በድርድር በድጋሚ ታህሳስ 2017 ዓ.ም ላይ የአንድ ዓመት ተጨምሪ ጊዜ ተሰጧቸው እንደነበር ያስታወሱት አቶ በሪሁ ምንም አዲስ ነገር ሳይፈጠር ወለዱም እየጨመረ የአንድ ዓመት ጊዜ ገደብም በላፈው ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡

 

የተሰጣቸው ያማራዘሚያ ጊዜ ደግሞ ውጤት ያላመጡት ተፈቅደው የነበሩ ማበረታቻዎች ባለመሰጠታቸው  እንደሆነ ምክርቤቱ ጥቁሟል፡፡

 

የሁለተኛ ዙር ጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ባንኮች ለማሲያዣ ያዋሉት ቋሚ ንብረቶችን በድጋሚ ለሶስተኛ ጊዜ ለሃራጅ የማቅረብ እንቅስቃሴ በመጀመራቸው በቅርቡ ከብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ውይይት ማካሄዳቸውን የምክርቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ በሪሁ ሃፍቱ አብራርተዋል፡፡

 

በውይይቱ ከዚህ ቀደም ተሰጥተው የነበሩት 30 የብድር ማራዘሚያ ወራት ምን አዲስ ነገር እንዳመጣ እንዲፈተሸ፤ ካላመጣ ደግሞ ሌላ አማራጭ እንዲታይ እና ምክርቤቱም በአጠቃላይ ያለውን ጥያቄ በጸሁፍ እንዲያቀርብ ከገዢው ጋር በነበራቸው ወይይት መነሳቱን ፕሬዚዳንቱ ነግረውናል፡፡

 

በዚህም መሰረት የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በባንክ እዳ ተገንብተው በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ለወደሙ፣ በከፊል ለወደሙ እና ስራ ጀምረው በጦርነቱ ለከሰሩ የንግድ ወይም እንቨስትመንት ተቋማት እና ፐሮጀክቶች ምን መደረግ እንዳለባት ዝርዝር የያዘ ሰንድ ለባንኩ አስገብቷል ተብሏል፡፡

 

በሰነዱ መሰረት አንደኛ በባንክ እዳ ተገንብተው በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ለወደሙ ፕሮጀክቶች ማራዘሚያ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ እዳው ከነወለዱ እንዲሰረዝላቸው፣ መልሰው ወደ ስራ እንዲገቡ ወቅቱን የማከለ የገንበዝ ድጋፍ እንዲሁም ብድር እንዲመቻችላቸው እና ማበረታቻ እንዲሰጣቸው እንደሚጠይቅ አቶ በሪሁ ነግረውናል፡፡

 

ሁለተኛ በከፊል ጉዳት ለደረሰባቸው አልያም ለተሰረቀበት ደግሞ የወድመቱን መጠን በጥናት ተለይቶ ብድሩ እንዲቀርለት ፣ከጉዳት የተረፈውን ጠግኖ የሚሰራበት ብድር እንዲመቻች እና ወለዱ ሙሉ በሙሉ እንዲቀርለት፡፡

 

ሶስተኛ ድገሞ ከባንክ እዳ ወስደው ንግድም ሆነ ስራ ጀምረው የነበሩ ስርቆትም ውድመትም ያልደረሰባቸው ነገር ግን በጦርነቱ ምክንያት ስራ አቁመው የከሰሩትን የተመለከተ ሲሆን በዚህም ተቋማቱ ባለመስራታቸው ለከፍተኛ ወለድ ክምችት ተዳርገዋል ተብሏል፡፡

 

እንዚህ ተቋማት ስራ እንዲጀምሩ እና ብድራቸውን መክፍል እንዲችሉ የገንዘብ አቅርቦት እንዲመቻቻላቸው ሰነዱ የሚጠይቅ መሆኑን የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ፕሬዚዳንት አቶ በሪሁ ሃፍቱ ተናግረዋል፡፡

 

ምክር ቤቱ አሁን የክልሉ አልሚ ሆነ ነጋዴ ካለበት የብድር ጫና ወጥቶ ለሃገርም ሆነ ለክልሉ ግብር እንዲከፍል በልማት ስራም እንዲሳተፍ እንዚህ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው ብሏል፡፡

 

አቶ በሪሁ በሃፍቱ በእዳ ጫና ምክንያት ለህመም የተዳረጉ ተበዳሪዎች መኖራቸውን ጠቁመው ብሔራዊ ባንክ ምን ምላሽ ሰጣችሁ የሚለውን ሲመልሱ ባንኩ የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ እንጂ ወለዱን የመግዛት አልያም መፍትሄ መስጠት የባንኩ ሃላፊነት ሳይሆን የሚኒስትሮች ምክርቤት እንደሆነ መናገሩን አስረድተዋል፡፡

 

ምክርቤቱ ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ማረዘሚያ ጊዜ እንማይፈልግ የተናገረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የባንኮች የወለድ መጠን 20 በመቶ ስለሆነ አሁን ከተራዘመ ደግሞ ያለውን ካፒታል መልሶ የሚውስድ ነው የሚሆነው ሲሉ አክሏል፡፡

 

ስለዚህም ተቋሙ በክልሉ ያለው የተከማቸ እዳ እና ብድር እንዲሰረዝለት ጠይቋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

  

ያሬድ እንዳሻው


X : https://x.com/shegerfm?s=2                 

Website፡ https://www.shegerfm.com/                          

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page