የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከ20.5 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ባለው በኮፔይ ኢ - ብር እስካሁን ከ4.8 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ተናገረ።
- sheger1021fm
- 9 minutes ago
- 1 min read
ጥር 6/2018
የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከ20.5 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ባለው በኮፔይ ኢ - ብር እስካሁን ከ4.8 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ተናገረ።
ባንኩ ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሬ ከባንኩ በኩል ለተቀበሉ ደንበኞቹ ባዘጋጀው የውጭ ምንዛሪ የሎተሪ እድለኞችን ሸልሟል፣ ዲጂታል ሎተሪ ሽያጭ እንደሚጀምር ተናግሯል።
የተላከላቸውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በመቀበላቸው እድለኛ የሆኑ ደንበኞች አንድ ዘመናዊ የቤት መኪና፣ 2 የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ፣10 ላፐቶፖች፣ 10 ቴሌቪዥኖችና 40 ስማርት ስልኮች በአጠቃላይ 63 ሸልማቶች ዕድለኞች ተበርክተዋል።

የባንኩ ኦፕሬቲንግ ተጠባባቂ ቺፍ አፊሰር አቶ አብዲ ፈቀደ ባንኩ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎትና ታምሶል ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር፣ በኮፔይ ኢ-ብር ሞባይል ዋሌቱ፣ የዲጂታል ሎተሪ ሽያጭ እንደሚጀምር ተናግረዋል።
ከ20.5 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ባለው በኮፔይ ኢ-ብር እስካሁን ከ4.8 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ግብይት መፈጸሙን አስረድተዋል።
ባንኩ እንደ ሀገር በተያዘው 2030 ወደ ዲጂታል ሽግግር ሂደት ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን በመጠቆም፣ በኮፔይ ኢ-ብር ዲጂታል ሎተሪ ሽያጭ የመጀመሩ እንቅስቃሴም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
X : https://x.com/shegerfm?s=2
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD








