top of page

የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች በመንግስት አካላት እና በፖሊሲ አውጪዎች ላይ ጫና በማሳደር ስለ ትንባሆ አሳሳች መልክቶችን በማሰራጨት ንግዳቸውን ለማስፋፋት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።

  • sheger1021fm
  • Jan 13
  • 1 min read

ጥር 5/2018


የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች በመንግስት አካላት እና በፖሊሲ አውጪዎች ላይ ጫና በማሳደር ስለ ትንባሆ አሳሳች መልክቶችን በማሰራጨት ንግዳቸውን ለማስፋፋት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።


ኢንዱስትሪዎቹ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ነን በሚል፣ የበጎ አድራጎት ስራን በማስታከክ እና በሌሎች ዘዴዎች የትምባሆ ስርጭትን ለማስፋፋት እየሰሩ ነው ተብሏል።


ከዚህ በተጨማሪም በዣንጥላዎች፣ በቲሸርቶች እና በመሰል ምርቶች ላይ ማስታወቂያዎችን እየሰሩ መሆኑም ተጠቅሷል።

የእነዚህን የኢንዱስትሪዎች ጫናን በመቋቋሙና ዘርፋን በመቆጣጠሩ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የተሻለ ስራ ሰርቻለሁ ብሏል።


በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 100 ሀገራት በተካተቱበት ጥናት፤ ኢትዮጵያ የትምባሆ ምርቶችን በመቆጣጠሩ የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግባለች ተብሏል።


በዚህ ጥናት ኢትዮጵያ የትምባሆ ምርቶችን በመቆጣጠር ከአፍሪካ 2 ከዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ሲል ተናግሯል።


ለዚህም ከአለም ጤና ድርጅት እውቅና ማግኘቱንም የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው ማብራሪያ ተናግሯል።


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page