top of page


በሆንግ ኮንግ ከ83 ያላነሱ ሰዎችን የገደለው የመኖሪያ ሕንፃዎች ቃጠሎ መጥፋቱ ተሰማ፡፡
ህዳር 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ሆንግ_ኮንግ በሆንግ ኮንግ ከ83 ያላነሱ ሰዎችን የገደለው የመኖሪያ ሕንፃዎች ቃጠሎ ከበርካታ ሰዓታት በኋላ መጥፋቱ ተሰማ፡፡ ቃጠሎው በአካባቢው ከነበሩ 8 የመኖሪያ ሕንፃዎች 7ቱን እንዳልነበሩ መደረጉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በአደጋው መሞታቸው ከተረጋገጠው ሌላ ሌሎች ሰለባዎች ካሉ ፍለጋው መቀጠሉ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ከገደላቸው ሌላ 76 ሰዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ 270 ሰዎች ደግሞ ገና እጣ ፈንታቸው እንዳልለየ ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ምክንያት የአደጋው ሟቾች ብዛት ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የመኖሪያ ሕንፃዎቹ ቃጠሎ በግዛቲቱ እጅግ ከባድ ነው ተብሏል፡፡ የአደጋው መንስኤ ገና አልተነገረም፡፡ ለጥገና አገልግሎት የተተከሉ ቀርክሃ ስሪት የህንፃ መወጣጫዎች ቃጠሎውን ማባባሳቸው
Nov 282 min read


ህዳር 1 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ስሎቫኪያ በአውሮፓ አገሮች ታግዶ የሚገኘው የሩሲያ ገንዘብ ለዩክሬይን በብድር የመሰጠቱ ሀሳብ ከስሎቫኪያ በኩል ጠንካራ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ በአውሮፓ ህብረት ዘንድ ታግዶ ከሚገኘው የሩሲያ ገንዘብ 140 ቢሊዮን ዩሮው ለዩክሬይን የጦር መደገፊያ በብድር እንዲሰጣት ምክር ከተያዘ መቆየቱን አናዶሉ አስታውሷል፡፡ የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ ግን እኛ የዚህ ውጥን አካል አይደለንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ይልቅ ለዩክሬይኑ ጦርነት ማብቃት ጥረቱ ቢበረታ ይሻላል ብለዋል ፊኮ፡፡ የታገደው የሩሲያ ገንዘብ ለዩክሬይን የጦር መደገፊያነት በብድር በሚሰጥበት መላ በአውሮፓ ህብረት መድረክ በመጪው ወር በታላቁ እንደሚመከርበት ታውቋል፡፡ ገንዘቡ ለዩክሬይን በብድር እንዲፈቀድላት የሁሉንም የህብረቱ አባል አገሮች ሙሉ ስምምነት እንደሚሻ ተ
Nov 102 min read


ጥቅምት 28 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ካሜሮን የካሜሮኑ አረጋዊ ፕሬዘዳንት ፖል ቢያ ለ8ኛ ጊዜ ቃለ መሐላ በመፈፀም አዲሱን ሀላፊነታቸውን ተረከቡ፡፡ ፖል ቢያ ለ8ኛ ጊዜ ቃለ መሐላ በመፈፀም ሀላፊነታቸው የተረከቡት በቅርብ ጊዜው የካሜሩን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሸንፈዋል ከተባለ በኋላ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የ92 አመቱ አረጋዊ ፖል ቢያ እስካሁን ካሜሮንን ከ40 አመታት በላይ መርተዋታል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ከአገር መሪዎቹ መካከል በእድሜ አንጋፋው እሳቸው ናቸው፡፡ ፖል ቢያ በምርጫው አሸንፈዋል የተባለው ሁነኛ ተፎካካሪዎች ከምርጫ በታገዱበት አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡ ተቃዋሚዎች ፖል ቢያ አሸናፊ የተደረጉበትን ምርጫ ህገ መንግስታዊ ጠለፋ ነው ሲሉ እየጠሩት መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሩሲያ ሩሲያ የአሜሪካ የወረራ ስጋት ተጋርጦብኛል ለትምትለው የደቡብ አሜሪካዋ አገ
Nov 72 min read


ጥቅምት 26 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#እስራኤል የእስራኤሉ የኢነርጂ እና የመሰረተ ልማት ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን ወደ ጋዛው ጦርነት መመለሳችን አይቀርም አሉ፡፡ ዔሊ ኮኸን በጋዛ ወደ ጠንካራው ድብደባችን ለመመለስ የምንጠብቀው የሟች ታጋቾችን አስከሬን በሙሉ መረከብ ብቻ ነው ሲሉ ለአገራቸው ቻናል 7 ቴሌቪዥን መናገራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ባቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ በጋዛ አልፎ አልፎ ቢጣስም የተኩስ አቁም ስራ ላይ ውሏል፡፡ እቅዱ የተኩስ አቁሙን መዝለቅ የሚከታተል አለም አቀፍ አረጋጊ ሀይል በጋዛ እንዲሰፍር ይጠይቃል፡፡ ዔሊ ኮኸን ግን አለም አቀፍ ሀይል ቢሰፍር እንኳ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታቱ አይሆንለትም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የአገራቸው ጦር ግን ወደ ጋዛው ዘመቻ ተመልሶ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታቱን በብቃት ማሳካት ይችላ
Nov 52 min read


ጥቅምት 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቱርክ በቱርክ PKK የተሰኘው የኩርዶች የቀድሞ አማጺ ቡድን ታጣቂዎቹን ከቱርክ ወደ ኢራቅ ማስወጣት ጀመረ፡፡ PKK ታጣቂዎቹን ወደ ኢራቅ ማስወጣት የጀመረው ከቱርክ መንግስት ጋር በጀመረው የሰላም ሒደት መሰረት እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ የኩርዶቹ ታጣቂ ቡድን ከእንግዲህ የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ በትጥቅ መፍታት ሒደት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ PKK ታጣቂነቱን ትቶ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ብቻ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡ ቡድኑ ለወሰደው እርምጃ አስተማማኝነት የቱርክ መንግስት PKK ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ማህበርነት የሚለወጥበትን ሁኔታ እንዲያመቻችለት መጠየቁ ተሰምቷል፡፡ PKK የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ከ40 አመታት በኋላ እንደሆነ መረጃው አስታውሷ
Oct 272 min read


ጥቅምት 13 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሱዳን በሱዳን የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከአገሪቱ ኤርፖርቶች የሚነሱ እና በኤርፖቶቹ የሚያርፉ አውሮፕላኖችን በሙሉ አወድማለሁ ሲል ዛተ፡፡ ዛቻውን ያሰሙ የፈጥኖ ደራሹ ሀይሉ አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ እንደሆኑ ሱዳንስ ፖስት ፅፏል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ትናንት ወደ አገልግሎት ተመልሷል በተባለው የካርቱም ኤርፖርት ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ሰንዝሯል ተብሏል፡፡ የካርቱም ኤርፖርት ትናንት ከ2 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ በረራ አውሮፕላን ማስተናገዱ ታውቋል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር ሲዋጋ ከ2 ዓመታት ከመንፈቅ በላይ ሆኖታል፡፡ ጦርነቱን ማቆሚያ አንዳችም ፍንጭ አይታይም፡፡ #አሜሪካ በአሜሪካ በሁለት የሩሲያ ታላላቅ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ማዕቀብ ጣለች፡፡ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ሮስ
Oct 232 min read


ጥቅምት 11 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፈረንሳይ የፈረንሳይ ሹሞች እጅግ ውድ የአገራችንን ቅርሶች ማስጠበቅ ተስኖናል ሲሉ በፀፀት ተናገሩ፡፡ የሹሞቹ አስተያየት የተሰማው በርዕሰ ከተማዋ ፓሪስ ከሚገኘው የሉቨር ቤተ መዘክር ውድ ጌጣ ጌጦች ከተሰረቁ በኋላ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ጌጣ ጌጦቹ የአገሪቱ ቅርሶችም በመሆናቸው በዋጋ እንደማይታመኑ እየተነገረ ነው፡፡ ከተዘረፉት ቅርሶች መካከል የፈረንሳዩ ንጉሰ ነገስት ናፖሊዮን በናፖርት ለባለቤቱ አበርክቶለት የነበረ በአልማዝ የተንቆጠቆጠ ሐብልም ይገኝበታል ተብሏል፡፡ ዘራፊዎቹ ላይ በፍጥነት ካልተደረሰባቸው ቅርሶቹን በማወላለቅ በትንሽ በትንሹ ወደ ውጭ አገራት ሊያሸሿቸው ይችላሉ የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ የፓሪሱ ዘረፋ በመሰል ቤተ መዘክሮች የደህንነት ጥበቃው በእጅጉ እንዲጠናከር የማንቂያ ደወል ሆኗል ተብሏል፡፡ የቤተ መዘክሩ የቅርሶች ዘረፋ በአገሪቱ
Oct 212 min read


ጥቅምት 6 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#የአፍሪካ_ህብረት የአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ የተደረገባትን ማዳጋስካርን ከአባልነት አግጃለሁ ማለቱ ተሰማ፡፡ በዚያ ካፕሳት የተሰኘው ልዩ የጦር ክፍል መኮንኖች የፕሬዘዳንት አንድሬይ ራጆሊናን መንግስት ማስወገዳቸውን እወቁልን ያሉት መሰንበቻው እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የጦር መኮንኖቹ መንግስታዊ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት አገሪቱ ከ2 ሳምንታት በላይ በተቃውሞ ስትናጥ ከሰነበተች በኋላ ነው፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የገልባጮቹ አለቃ ኮሎኔል ሚካኤል ራንድ ኒሪያናን ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት እንዲሆኑ ፈቅዶላቸዋል፡፡ የገልባጮቹ አለቃ በነገው እለት ቃለ መሐላ በመፈፀም ሀላፊነታቸው ይረከባሉ ተብሏል፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ግን የአፍሪካ ህብረት ማዳጋስካርን ከአፍሪካ ህብረት አባልነትዋ አግጃለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ #ቬኒዙዌላ የቬኒዙዌላው ፕሬ
Oct 163 min read


መስከረም 23 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ደቡብ_አፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሣ ለጋዛ ፍልስጤማውያን ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ በጀልባ ሲያመሩ በእስራኤል ጦር ተይዘው የታሰሩት በጎ ፈቃደኞች እንዲለቀቁ ጠየቁ፡፡ ከታሰሩት የብዙ አገሮች ዜጎች...
Oct 32 min read


መስከረም 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሱዳን የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ የአለም ማህበረሰብ RSFን በአሸባሪነት ይፈረጅልን አሉ፡፡ በሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው RSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር ሲዋጋ ከ2...
Sep 292 min read


መስከረም 14 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ጀርመን ጀርመን የወታደሮቿን ብዛት እና የመከላከያ ወጪዋን በእጅጉ ልትጨምር ነው ተባለ፡፡ አገሪቱ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ለመመልመል መሰናዳቷን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀርመን የጦር...
Sep 241 min read


ሐምሌ 28 2017 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#የአለም_አቀፍ_የፍሰተኞች_ድርጅት በየመን የባህር ዳርቻ ባጋጠመ የጀልባ ተገልብጦ መስጠም አደጋ ከ60 በላይ ስደተኞች ሕይወት አለፈ ተባለ፡፡ አደጋው የደረሰው በየመን አቢያን ግዛት አቅራቢያ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡...
Aug 42 min read


ሐምሌ 18 2017 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፈረንሳይ ፈረንሳይ ለፍልስጤም ነፃ አገርነት ይፋዊ እውቅና ልትሰጥ ነው፡፡ ፈረንሳይ ለፍልስጤም ነፃ አገርነት እውቅና ለመስጠት መሰናዳቷን ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባኖሩት መልዕክት...
Jul 252 min read


ሰኔ 20 2017 - የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኢራን የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ሐሚኒ አሜሪካ ዳግም ጥቃት ካደረሰችብን በቀጠናው የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿን እንመታለን አሉ፡፡ የኢራኑ የበላይ መሪ በመንግስታዊው መገናኛ ብዙሃን በተላለፈ መልዕክታቸው በቀጠናው...
Jun 272 min read


ሰኔ 7 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ኢራን ኢራንም በእስራኤል ላይ የብቀላ አፀፋ እየሰነዘረች ነው፡፡ እስራኤል ቀደም ሲል በኢራን የኒኩሊየር ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ያለችውን ከባድ ድብደባ መፈፀሟን አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ የኢራን ሹሞች በእስራኤል ድብደባ...
Jun 142 min read


ግንቦት 27 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሱዳን ሱዳን ውስጥ የተባበሩት መንግስታትን የእርዳታ ምግብ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት አምስት የረድኤት ሰራተኞች ተገደሉ፡፡ በጥቃቱ አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው እንዳሉ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እርዳታ በጫኑት...
Jun 42 min read


ግንቦት 25 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሱዳን አዲሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ ቃለ መሐላ በመፈፀም ሀላፊነታቸውን ተረከቡ፡፡ ካሚል ኢድሪስ የቃለ መሐላ ስነ ስርዓትን ያከናወኑት የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት የተሰኘው አካል የበላይ የሆኑት ጄኔራል...
Jun 21 min read


ግንቦት 20 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ጋዛ በጋዛ ሰርጥ የምግብ እርዳታ ማከፋፈያ ማዕከል ከፍተኛ ረብሻ እና ውጥንቅጥ ተፈጠረ፡፡ ለ3 ወራት ምናምኒት ሰብአዊ እርዳታ ያላገኙ ፍልስጤማውያን ወደ እርዳታ ማከፋፈያው መጉረፋቸው ቀድሞ ለመግባት በተፈጠረ...
May 282 min read


ግንቦት 18 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአውሮፓ ህብረት ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች እና ምርቶች ላይ ያሰቡትን የቀረጥ ታሪፍ ጭማሪ በ1 ወር አራዘሙት፡፡ ትራምፕ በህብረቱ ሸቀጦች እና ምርቶች ላይ የ50 በመቶ...
May 262 min read


ግንቦት 13 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ብሪታንያ ብሪታንያ ከእስራኤል ጋር ጀምራ የነበረውን የነፃ ንግድ ንግግር አቋረጠች ተባለ፡፡ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪየር ስታርመር መንግስት ከእስራኤል ጋር ሲደረግ የነበረውን ንግድ ነክ ንግግር ያቋረጠው...
May 212 min read


ግንቦት 12 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ፈረንሳይ ፈረንሳይ በደቡብ አሜሪካ አማዞን ጫካ ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የማይለየው እስር ቤት ልትገነባ ነው ተባለ፡፡ የፈረንሳዩ የፍትህ ሚኒስትር ጌራልድ ድራማኒን ፍሬንች ጉያና በተባለው የፈረንሳይ የባህር ማዶ...
May 202 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








