top of page

የካቲት 9/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • Feb 16
  • 1 min read

የካቲት 9/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች



የእስራኤል መንግስት የሀገሪቱ ዜጎች በቀላሉ በዌስት ባንክ መሬት እንዲገዙ የሚያስችል ህግ አፀደቀ።


ህጉ እስራኤላውያን ግለሰቦች በዌስት ባንክ መሬት እንዲገዙ የሚፈቅድ ሲሆን ከገዙት መሬትም የተወሰነውን ለሀገሪቱ የመንግስት አስተዳደር ማስተላለፍ እንደሚችሉ ይደነግጋል።


ህጉ እስራኤል በዌስት ባንክ የምታካሂደውን የአይሁዶች የሰፈራ ፕሮግራም ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ ነው በሚል ከተለያዩ ወገኖች ትችት እየቀረበበት ይገኛል።


የአውሮፓ ህብረት አባላት እና የአረብ ሀገራት ትችቱን ከሰነዘሩት መካከል እንደሆኑ DPA international ዘግቧል።


የእስራኤል መንግስት ግን ህጉ የዜጎችን ሃብት የማፍራት መብት ታሳቢ አድርጎ ብቻ የተዘጋጀ ነው ብሏል።



የሡዳን ጦር በምዕራብ ኮርዶፋን የነበረን የፈጥኖ ደራሹ ሃይልን የአየር ሃይል ማዘዣ ሰፈር አወደምኩ አለ።


በጦር ሰፈሩ በነበሩ የፈጥኖ ደራሹ ሃይል ተዋጊዎች እና የጦር መሳሪያ ክምችት ላይ ከበድ ያለ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሷል።


ከዚህ በላይ ግን የሰጠው ዝርዝር መረጃ እንደሌለ አናዱሉ ፅፏል።


የሡዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል በጄኔራል አልቡርሃን በሚመራው የሀገሪቱ ጦር ደርሶበታል ስለ ተባለው ጥቃት ያለው ነገር የለም።


በጀኔራል አልቡርሃን የሚታዘዘው የሡዳን ጦር እና ጀኔራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ሃይል አሁን ላይ በዳርፉር እንዲሁም ሰሜን ፤ ደቡብ እና ምዕራብ ኮርዶፋን ከባድ ውጊያ እያካሄዱ እንደሚገኙ ተነግሯል።


ሶስት ዓመት ባስቆጠረው የሁለቱ ሃይሎች ውጊያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሡዳን ዜጎች መገደላቸው የተነገረ ሲሆን 13 ሚሊየን ያህሉ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ተብሏል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page