top of page


ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት በቀሩትና በመንግስት ወጥቶ ላለፉት 2 ዓመት ሲተገበር ከቆየው የኪራይ ውል ወጪ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ከፍትኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡
ግንቦት 7/2018 ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት በቀሩትና በመንግስት ወጥቶ ላለፉት 2 ዓመት ሲተገበር ከቆየው የኪራይ ውል ወጪ በአዲስ አበባ በቤቶች ላይ ከፍትኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት በህብረተሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫናና በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ በየቀኑ ሰማይ እየነካ የሄደው የዋጋ ንረት የሸማቹን የመግዛት አቅም በእጅጉ አዳክሞታል፤ ለዚህም መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል። በተለይም ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች እየተደረገ ነው ይህንንም አረጋግጫለሁ ብሏል ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፡፡ የሸማቹ የመግዛት አቅም መዳከም ደግሞ አጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮ
May 152 min read


የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
ግንቦት 6/2018 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል። አገልግሎቱ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ሀሰተኛ የልደት ሰርተፍኬት፣ መታወቂያ እና ፋይዳ በመያዝ ህጋዊ አገልግሎት ለማግኘት ሲሉ እንደተደረሰባቸው ተናግሯል። በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት አገልግሎት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ብርሃኑ ከድንበር አከባቢ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ከውጪ ሃገር ከሚመጡ ዜጎች ጋር የሚመሳሰል ማንነት ስላላቸው የውጪ ዜጎች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ለመያዝ ሙከራ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል። አቶ ሙሉጌታ ረጅም ዓመታትን በኢትዮጵያ የኖሩ ኤርትራዊያን የኢትዮጵያ ዜግነት ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታም አስረድተዋል። በሪፈረንደሙ ወቅት ያልመረ
May 141 min read


ከእፅ መጠቀም፣ ከቁማር የተነሳ ለአእምሮ ህመም ተጋላጭ የሚሆኑ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡
ግንቦት 6/2018 ከእፅ መጠቀም፣ ከቁማር የተነሳ ለአእምሮ ህመም ተጋላጭ የሚሆኑ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በኢትዮጵያም በተቀረው ዓለምም ከጭንቀት፣ ድብርትና ሌሎችም ጉዳዮች ጋር በተገናኘ የሚከሰቱት የአእምሮ መታወኮች አሁንም ከአጠቃላዩ ችግር ድርሻው ከፍተኛ ነው። በሌላ በኩል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በኢትዮጵያ ለአዕምሮ ጤና መታወክ ምክንያት የሆኑ አዳዲስ ልማዶች እየታዩ ነው ይላሉ በየካ ኮተቤና በዶክተር ዳዊት ኦፊስ ፕራክቲስ ውስጥ የአዕምሮ ሀኪም የሆኑት ዳዊት አሰፋ(ዶ/ር)። እነዚህ በፊት የምዕራባዊያን ይባሉ የነበሩ አሁን አሁን በኢትዮጵያም መታየት ከጀመሩ ችግሮች ውስጥ አንዱ ከሰውነት አቋምና አመጋገብ ጋር የተገናኘ ነው ብለዋል። ብዙ ሰዎች ሰውነቴ ጨምሯል መክሳት አለብኝ፤ ምግብ አብዝቻለው መቀነስ ይኖርብኛል በሚል ጭንቀትና ስለራሳቸው ባ
May 141 min read


ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁሉም ወገን ለኢትዮጵውያን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲፈጸም የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳሰበ፡፡
ግንቦት 6/2018 ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁሉም ወገን ለኢትዮጵውያን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲፈጸም የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳሰበ፡፡ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ውስጥ በምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ከመንግስት ጋር በመነጋገር እንዲፈቱ፣ ሕዝቡን እንዲያጽናኑ፣ ሀገረ ስብከቱንም በሊቀ ጵጵስና በቋሚነት እንዲመሩ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበዋል፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ንጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡ ላለፉት ቀናት ምክክር እያደረገ የነበረው ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስ በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ ካሳለፈባቸው
May 142 min read


በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ታድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና የልብስ ቁራጮች እንዲሁም የወርቅ አምባር ቅርሶች ከ158 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡
ግንቦት 6/2018 በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ታድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና የልብስ ቁራጮች እንዲሁም የወርቅ አምባር ቅርሶች ከ158 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ቅርሶቹ የተመለሱት ከእንግልዝ ሀገር ሲሆን ቅርሶቹን ያመጡት ሮቢን ጃክሴን (ዶ/ር) የእንግልዝ የንግስቲቱ ቤተሰብ ሙዚየም ኃላፊና አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር ) የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አባልና ተመራማሪ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ለቅርሶቹ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ታሪካዊ የሆኑ ቅርሶች በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የወጡትን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ስራ በትልቅ ትኩረት እየተሰራ
May 141 min read


‘’በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩና በመንግስት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ በድጋሜ በህገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ሰዎች አሉ‘’
ግንቦት 6/2018 በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ በድጋሜ በህገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ሰዎች መኖራቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። ይህንን ችግርም ለመፍታት ህገወጥ ደላሎች ላይ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል። ከስደት ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው ሲመጡ በማቋቋሚያ ሂደቱ ላይ የሚጠብቁትን ያህል ባለማግኘታቸው እና የነበሩበት ቦታ የተሻለ ገቢ ስለሚኖራቸው ተመልሰው ወደ መጡበት ሀገር በህገወጥ መንገድ መሄድን ይመርጣሉ ተብሏል። ብዙ የሚባሉ ሰዎች ባይሆኑም ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላ ግን በድጋሜ በህገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ መኖራቸውን ያነሳው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ለማስተካከልም ህገወጥ ደላሎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብሏል። በሌላ በኩል በተያዘው
May 141 min read


''የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ’’ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ወቅት ታይተዋል ያላቸውን ህጸፆች ይፋ አደረገ።
ግንቦት 5/2018 በሰባተኛው ምርጫ ዙሪያ እየሰሩ ካሉ ጥምረቶች አንዱ የሆነው፤ ‘’የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ’’ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ወቅት ታይተዋል ያላቸውን ህጸፆች ይፋ አደረገ። ማንነትን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ሳያሟሉ በመራጭነት መመዝገብና በተከለከሉ ቦታዎች የምርጫ ጣቢያዎችን ማቋቋም ጥምረቱ ታይተዋል ካላቸው እንከኖች መካከል ናቸው። በጥቂት የምዝገባ ጣቢያዎች ውስጥ እና አካባቢ በታጠቁ ኃይሎች በተመዝጋቢዎች፣ በአስፈጻሚዎችና በታዛቢዎች ላይ ጥቃት፣ ማስፈራራትና ወከባ እንተፈጸመም ጠቅሷል። በምርጫ እና ምርጫ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ፤ 2011 ላይ ነው የተመሰረተው። ከ180 በላይ አባሉት እንዳሉትም ከጥምረቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሃይለማሪያም ሠምተናል። ከቀና
May 132 min read


በመካከለኛው መስራቅ ጦርነት ምክንያት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የቅባት እህሎች የማጓጓዣ ዋጋ ከሶስት እጥፍ በላይ መጨመሩ ተነገረ፡፡
ግንቦት 5/2018 በመካከለኛው መስራቅ ጦርነት ምክንያት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የቅባት እህሎች የማጓጓዣ ዋጋ ከሶስት እጥፍ በላይ መጨመሩ ተነገረ፡፡ ይህን የተናገረው የኢትዮጵያ የጥራጥሬ እና የቅባት እህል ላኪዎች ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ በጦርነቱ ምክንያት የጥራጥሬ እና የቅባት እህል ላኪዎች ምርቶቻቸውን በሚፈለገው ደረጃ ወደ ውጭ መላክ እንዳልቻሉ እና በዚህም ምክንያት ትልልቅ ላኪ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ከዝነው መያዛቸውን ተናግሯል፡፡ የኢራኑ ጦርነት አሁንም መፍትሔ ባለማግኘቱ ኢትዮጵያ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ የምትልካቸው የቅባት እህሎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መቀጠሉን የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ኤዳኦ አብዲ ነግረውናል፡፡ አቶ ኤዳኦ ኢትዮጵያ ነጭ ቦሎቄን፣ ሰሊጥ እና መሰል ምርቶች በሆሩሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ አሜሪ
May 131 min read


ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብል ምርት ከሚያስፈልገው ግብአት ውስጥ ገበሬው የሚቀርብለት ከ35 በመቶ እንደማይበልጥ ተነገረ፡፡
ግንቦት 4/2018 ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብል ምርት ከሚያስፈልገው ግብአት ውስጥ ገበሬው የሚቀርብለት ከ35 በመቶ እንደማይበልጥ ተነገረ፡፡ ይህ የተባለው በሰብል የግብርና ግብአት ላይ ትኩረት ያደረገ ሀገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበርያ ኤግዚቢሽን ከግንቦት 14 እስከ 16 እንደሚካሄድ ይፋ በተደረገበት መግለጫ ነው፡፡ ለግብርናው ምርታማነት የሚያሰፈልጉ ግብአቶችን በበቂ ሁኔታ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ይሁንና በተለያየ ምክንያት ገበሬው ግብአት እየደረሰው እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ ለዚህ አንደኛው ምክንያት የገበያ ትስስር ችግር ነው የተባለ ሲሆን የሚሰናዳው ኤግዚቢሽንም ለተጠቀሰው ችግር መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎበታል፡፡ በኤግዚቢሽኑ ለሰብል ልማት የሚያገለግሉ የአፈር ማዳበርያ ፣ ፀረ ነፍሳት ፣ ፈንገስ ማጥፊያዎች ፣ አረም ማጥፊያ ፣ የግብርና ስራን ለ
May 132 min read


የአዲስ አበባ ስነ ስሪት (የተዋቀረችበት መንገድ) ለከተማ ልማትና ዕድገት አስቸጋሪ አድርጓታል ተብሏል።
ግንቦት 4/2018 የአዲስ አበባ ስነ ስሪት (የተዋቀረችበት መንገድ) ለከተማ ልማትና ዕድገት አስቸጋሪ አድርጓታል ተብሏል። አመሰራረቷም በተጠና የከተማ ፕላን ሳይሆን በልማዳዊ ሰፈራ መሆኑ ከነገስታቱ ጀምሮ ባለው ስርዓት ውስጥ አዲስ አበባን ለማዘመን ፈተና ሆኖ መቀጠሉም ተነግሯል። ይህ የተነገረው ናሽናል ሚዲያ አክስዮን ማህበር "አዲሲቱ አዲስ" በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ከተማን የማደስና የልማት ሥራዎች፣ በጎ ዕድሎችና ፈተናዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በተካሄደበት መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ላይ የዳሰሳ ፅሁፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ዳዊት በንቲ (ዶ/ር)፤ አዲስ አበባ ከሌሎች የዓለም ከተሞች በዕድሜ ትንሿ መሆኗን አንስተዋል። ከተማዋ የተቆራረጠች እና ለዋና ከተማነት የማትመች ቦታ ላይ ነች ያሉት ዳዊት(ዶ/ር)፤ ይህም በየጊዜው ከተማዋ
May 122 min read


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 1,139 የአገልግሎቱ ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰዱን ተናገረ፡፡
ግንቦት 4/2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 1,139 የአገልግሎቱ ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰዱን ተናገረ፡፡ እርምጃ ከተወሰደባቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች መካከል 16ቱ ከስራቸው ሲሰናበቱ፤ 721ዱ የደመወዝ ቅጣት እንዲሁም 402 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው ተብሏል፡፡ አገልግሎቱ በሠራተኞች ላይ ከወሰዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች መካከል 103 ሠራተኞች ላይ በደንበኞች የቀረበን ጥቆማ በመመርመር የወሰደው መሆኑንና ቀሪ 1,036ቱ ተቋሙ በራሱ ግኝት አጣርቶ የወሰዳቸው እርምጃዎች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ ባለፉት 9 ወራት አገልግሎቱ በሙስና መጠቆሚያ ዘመናዊ መተግበሪያ እና በሌሎች አማራጮች ከደንበኞቹ የደረሱትን 427 ጥቆማዎችን መርምሮ በ103 ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የ
May 121 min read


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ግንቦት 4/2018 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አቶ ዘገየ የግብርና ሚኒስቴርን ከ1968–1970 ዓ.ም እና ከ1983 - 1984 ዓ.ም በሚኒስትርነት ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ አቶ ዘገየ አስፋው መሬት ለአራሹ አዋጅ እንዲታወጅ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው፡፡ አቶ ዘገየ አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም ተለይተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እየሰሩ ነበር፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1
May 121 min read


ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለህዳሴ ግድብ 1.2 ቢሊዮን ብር ተሰብሰቧል ተባለ።
ግንቦት 3/2018 ባለፉት 9 ወራት ለህዳሴ ግድብ 1.2 ቢሊዮን ብር ተሰብሰቧል ተባለ። ይሀም ለመሰብሰብ ከታቀደው ውስጥ ከ50 በመቶ በታች ወይም 1.2 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ባለፉት 9 ወራት ሀገሪቱ ከኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ ወደ 366 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ታውቋል፡፡ ይህ የተነገረው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለፉት 9 ወራት የሰራቸውን ስራዎች ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባለፈው ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡ ጷጉሜ 4/2017 ዓ.ም የግንባታ ስራው ተጠናቅቆ ለተመረቀው ታላቁ ህዳሴ ግድብ 9 ወራት ውስጥ በህዝብ ተሳትፎ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተሳትፎ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 2.58 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር ለምክር ቤቱ የቀረበው ሰነድ ያሳያል፡፡ ይሁንና የእቅዱን 50 በመቶ ገደማ
May 112 min read
በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ500,000 እና 400,000 ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ።
ግንቦት 3/2018 በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ500,000 እና 400,000 ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ። መንሱር ጀማል የተባለው ተከሳሽ ግን አቃቢ ህግ መቃወሚያ ስላቀረበበት ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ በ1.9 ቢሊዮን ብር የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፈቅዷል። ባለፈው ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከ5 ተከሳሽ መንሱር ጀማል ውጭ ባሉ ተጠርጣሪዎች ከሀገር እንዳይወጡ እና ከፍ ያለ ዋስትና አስይዘው የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከውጭ ሆነው ጉዳያቸውን ቢከታተሉ እንደማይቃ
May 111 min read


በአዲስ አበባ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጉቦ እና የእጅ መንሻ፤ አካውንት ቁጥር እስከ መስጠት መድረሱ ተነገረ፡፡
ሚያዝያ 30/2018 በአዲስ አበባ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጉቦ እና የእጅ መንሻ፤ አካውንት ቁጥር እስከ መስጠት መድረሱ ተነገረ፡፡ በአዲስ አበባ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ለአገልግሎት የሚመጡ ሰዎችን ጉቦ የሚጠይቁ እንዳሉ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ነው የተናገሩት፡፡ ጉቦ እና እጅ መንሻ መጠየቅ፤ አገልግሎት መስጠት ላይ እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉም ከምክር ቤት አባል ተነስቷል፡፡ #ጉቦ ጠይቀው የተገኙት ላይም የሚወሰድባቸው እርምጃ እና የሚወሰኑ ውሳኔዎች ቀለል ያሉ ናቸው ተብሏል፡፡ ይህ መሆኑ ጉቦ ጠያቂዎቹ የበለጠ እየተደፋፈሩ እንደሆነና ቅጣቱ ሌሎችን ሊያስተምር እንዳልቻለ ተጠቅሷል፡፡ ይህ የተነገረው ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ ይህንን ተግባር ለማስቆም ምን እየተሰራ እንደሆነም ጥያቄ ቀ
May 81 min read


የሚያዝያ ወር የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ከ11 በመቶ መሻገሩን መንግስት ተናገረ።
ሚያዝያ 30/2018 የሚያዝያ ወር የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ከ11 በመቶ መሻገሩን መንግስት ተናገረ። አምና በዚህ ወቅት የዋጋ ግሽበቱ 14.4 በመቶ እንደነበር ያስታወሰው የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ሲሆን ዘንድሮ በመጠኑ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል። የዘንድሮ የሚያዝያ ወር የግሽበት ምጣኔ 11.7 በመቶ ነው። ከባለፈው ወር ደግሞ 2.2 በመቶ ያህል ጨምሯል። በተለይ ምግብ ነክ የሆኑና አልኮል የሌላቸው መጠጦች ደግሞ ከፍተኛ ሆኖ የዋጋ ግሽበት ምጣኔአቸው 13.5 በመቶ ደርሷል። ለአብነትም አትክልት፣ ስጋ፣ የወተት ተዋፅዖዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይት እና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል ብሏል አገልግሎቱ ባወጣው መረጃ። ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 9.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን የትራንስፖርት ዋጋ በ13 በመቶ ከፍ ብሏል። በምግብ ቤቶች እና ሆ
May 81 min read


በአጭር ጊዜ ለግንባታ የሚጠይቀውን በጀት አግኝተው ግንባታን ይከውኑት ይሆን?
የሚያዝያ 29/2018 የትምህርት ሚኒስቴር በቀሪዎቹ 4 ወራት 1,452 የቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ክልሎች ለመገንባት በቅብሩ ከክልሎች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገነቡት ግማሹ በትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በክልሎቹ በራሳቸው ወጪ ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ለሚያስገነባቸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 40 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ከአጋር አካላት በእርዳታ ማግኘቱን ተነግሯል፡፡ ታዲያ ክልሎች በአጭር ጊዜ ለግንባታ የሚጠይቀውን በጀት አግኝተው ግንባታን ይከውኑት ይሆን? የተለያዩ ክልሎችን ጠይቀናል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በክልሉ የሚገነባው 70 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ሲገነቡ በክልሉ ውስጥ
May 82 min read


ትንባሆ በሚጨስባቸው የግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ብርቱ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡
የሚያዝያ 29/2018 ትንባሆ በሚጨስባቸው የግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ብርቱ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡ በትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ትንባሆ ሲያጨሱ ተገኝተው እርምጃ የተወሰደባቸውም እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡ ይህንን ያደረግሁትም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ነው ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፡፡ ትንባሆን በማንኛውም አይነት ሁኔታ መጠቀም የበዙ የጤና ችግሮች እንዳሉት ወጣቶች እንዲያወቁት የግንዛቤ ስራ እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም በህጉ መሰረት ሲጋራን በነጠላ መሸጥ በህግ ቢከለከልም አሁንም በነጠላ የሚሸጡ እና የሚገዙ በየቦታው እንደሚታዩም ተነስቷል፡፡ እንዲህ በሚያደርጉት ላይ የማስተማርና እርምጃ የመውሰድ ስራ እየተሰራ መሆኑን እና መልካም የሚባል መሻሻል መገኘቱን የተናገሩት ደግሞ በኢትዮ
May 71 min read


‘’በአዲስ አበባ በ9 ወራት ከ37,000 በላይ እግረኞች ተቀጥተዋል’’
የሚያዝያ 29/2018 ማዳመጫ ጆሯቸው ላይ አድርገው የአስፋልት መንገድ የተሸገሩ እና ሌሎች የመንገድ አጠቃቀም የደንብ መተላለፍ የፈፀሙ ከ37,000 በላይ እግረኞች ተቀጥዋል ተባለ፡፡ ባለፉት 9 ወራት ቅጣቱ ከተላለፉባቸው ከነዚህ እግረኞች መካከል የገንዘብ ቅጣቱን መክፈል ያልቻሉት 16,000 ያህሉ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :-..
May 71 min read


የመክፈል አቅም ለሌላቸው፤ ጠበቆች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡
የሚያዝያ 29/2018 ፍትህ ለሁሉም ተደራሽ ይሆን ዘንድ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ነፃ የህግ ድጋፍ እንዲያገኙ መንግስት ህግ ቢያወጣም አሁንም ግን ብዙ ሰዎች ተጠቃሚ እየሆኑ አይደለም፡፡ የፍትህ ሚኒስቴርም ይህንን ያምናል፡፡ ከህጉ ባሻገር ጠበቆችም በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ምንታምር ፀጋው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s
May 71 min read


የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ብድር ጭማሪ ማሳየቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ።
ሚያዝያ 29/2018 የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ብድር ጭማሪ ማሳየቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ። የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል። ኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የምታገኝበትን ስምምነት ሁለቱ አገራት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለፓርላማ ተናግሯል። የገንዘብ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ከሰሞኑ የዘጠኝ ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ክንውን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ 33.5 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ብድር እዳ እን
May 72 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

