የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
- 3 hours ago
- 1 min read
ግንቦት 6/2018
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
አገልግሎቱ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ሀሰተኛ የልደት ሰርተፍኬት፣ መታወቂያ እና ፋይዳ በመያዝ ህጋዊ አገልግሎት ለማግኘት ሲሉ እንደተደረሰባቸው ተናግሯል።
በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት አገልግሎት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ብርሃኑ ከድንበር አከባቢ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ከውጪ ሃገር ከሚመጡ ዜጎች ጋር የሚመሳሰል ማንነት ስላላቸው የውጪ ዜጎች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ለመያዝ ሙከራ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል።
አቶ ሙሉጌታ ረጅም ዓመታትን በኢትዮጵያ የኖሩ ኤርትራዊያን የኢትዮጵያ ዜግነት ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታም አስረድተዋል።
በሪፈረንደሙ ወቅት ያልመረጡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት መብት ይሰጣቸዋል፣ ሪፈረንደም የመረጡ ግን ህጉን ተከትለው የዜግነት ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚነሱበትን ቅሬታዎች ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ፣ ሰዎችም ለአግልግሎት ሲመጡ የሚያጋጥማቸውን እንግልት ለመቀነስ የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ሁሉ አሟልተው እንዲመጡ አሳስበዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments