top of page

የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ብድር ጭማሪ ማሳየቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ።

  • May 7
  • 2 min read

ሚያዝያ 29/2018


የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ብድር ጭማሪ ማሳየቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ።


የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል።


ኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የምታገኝበትን ስምምነት ሁለቱ አገራት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለፓርላማ ተናግሯል።


የገንዘብ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ከሰሞኑ የዘጠኝ ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።


የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ክንውን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል።



ከዚህ ውስጥ 33.5 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ብድር እዳ እንደሆነ እና ቀሪው 18.3 ቢሊዮን ዶላሩ ደግሞ የሀገር ውስጥ እዳ መሆኑን አቶ አህመድ አብራርተዋል።


ከ33.5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ ውስጥ ደግሞ 22.1 ቢሊዮን ዶላሩ የፌደራል መንግስት እዳ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ቀሪው 11.5 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እዳ እንደሆነም አክለዋል።


ከሀገር ውስጥ ብድሩ ማለትም ከ18.3ቢሊዮን ዲላር ውስጥ ደግሞ 17.5 የፌደራል መንግስት እዳ እንደሆነ እና 0.8 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ነው ብለዋል አቶ አህመድ ።


የመንግስት የልማት ድርጅቶች እዳ ዝቅ ያለበትን ምክንያት አቶ አህመድ ሲያስረዱ በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መሰረት አብዛኛው ከንግድ ባንክ ተበድረው የነበረው ብድር ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር በመዞሩ በበጀት መከፍል በመጀመሩ እንደሆነ አሳውቀዋል።


አጠቃላይ የኢትዮጵያ እዳ ሁኔታ በእሳቸው አገላለጽ "በጣም በጣም "ጤናማ እንደሆነ ለቋሚ ኮሚቴው ያስረዱት ሚኒስትሩ የውጪ እዳ የመክፈል አቅማችንም "ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየጨመረ ነው ብለዋል።


የሀገር ውስጥ ብድር ደግሞ ጭማሪ አሳይቷል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡


ይህ ደግሞ ለማስተካከል በዘላቂ (sustainable) የፋይናንስ መርህን በመከተል የሚሰራ ስራ ይኖራል ነው ያሉት ሚኒስትር አህመድ።


በእዳ ክፍያን ክንውን ሪፖርታቸው ደገሞ በበጀት ዓመቱ ለሀገር ውስጥ እና የውጪ እዳ ክፍያ 463.4 ቢሊዮን ብር ተመድቦ የነበረ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የአግልግሎት ክፍያን ጨምሮ 226.5 ቢሊዮን ብር ተከፍሏል።


እንዲሁም የውጭ ሃብት አሰባሰብን በተመለከተ በዓመቱ ከተለያዪ ተቋማት 4 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ማታቀዱን እንዲሁም በዘጠኝ ወሩ ደግሞ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታቅዶ ከዛ ውስጥ 2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከእቅዱ በ1.1 ዶላር ያነሰ ተግኝቷል ተብሏል።


ይህም የእቅዱን 65.1 በመቶ ሲሆን ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ 914.2 ሚሊዮን ዶላሩ ከአለም ባንክ መገኘቱን አቶ አህመድ ተናግረዋል።


የውጪ ሃብት ግኝቱ በቀጣይ ሁለት ወራት ከፍ ይላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያስረዱት ሚኒስትሩ ባለፈው አሜሪካ ተደርጎ በነበረው የአልም ባንክ እና የገንዘብ ድርጅት ስብሰባ ላይ ለበጀት ድጋፍ ለአደጋ ምላሽና ለነዳጅ ማሻሻያ ማስኬጃ የሚያስችሉ ምላሾች መገኘታቸውን የገንዘብ ሚኒስትሩ ሪፖርት ያክላል።


የአሜሪካ የተራድዖ ድርጅት እርዳታ መቋረጥ የጤና፣ ትምህርት፣ ግብርና የእቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ጫና መፍጠሩን ያስታወሱት ሚኒስትሩ በቅርቡ ድርድር በማድረግ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በዓመቱ በመንግስት በኩል ፈሰስ እንዲደረግ ከአሜሪካ መንግስት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል ብለዋል።


ይህም ስምምነት በቅርቡ በካቢኔ እንደሚጸድቅ አቶ አህመድ ጠቁመዋል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…



ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 
በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡

ሰኔ 15/2018 በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት በተለያዩ ሶስት ፋብሪካዎች ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ ከ69 ቶን በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page