በመካከለኛው መስራቅ ጦርነት ምክንያት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የቅባት እህሎች የማጓጓዣ ዋጋ ከሶስት እጥፍ በላይ መጨመሩ ተነገረ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ግንቦት 5/2018
በመካከለኛው መስራቅ ጦርነት ምክንያት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የቅባት እህሎች የማጓጓዣ ዋጋ ከሶስት እጥፍ በላይ መጨመሩ ተነገረ፡፡
ይህን የተናገረው የኢትዮጵያ የጥራጥሬ እና የቅባት እህል ላኪዎች ማህበር ነው፡፡
ማህበሩ በጦርነቱ ምክንያት የጥራጥሬ እና የቅባት እህል ላኪዎች ምርቶቻቸውን በሚፈለገው ደረጃ ወደ ውጭ መላክ እንዳልቻሉ እና በዚህም ምክንያት ትልልቅ ላኪ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ከዝነው መያዛቸውን ተናግሯል፡፡

የኢራኑ ጦርነት አሁንም መፍትሔ ባለማግኘቱ ኢትዮጵያ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ የምትልካቸው የቅባት እህሎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መቀጠሉን የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ኤዳኦ አብዲ ነግረውናል፡፡
አቶ ኤዳኦ ኢትዮጵያ ነጭ ቦሎቄን፣ ሰሊጥ እና መሰል ምርቶች በሆሩሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ እንደምትልክ አስታውሰዋል፡፡
አሁን ወሽመጡ በጦርቱ ምክንያት ስለተዘጋ የኢትዮጵያ ምርቶች በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ቨርድ በኩል ወደ ውጪ እንደሚላኩ ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡
ይህም ረዥም ጊዜ እንደሚፈጅ እና ለማጓጓዣ የሚከፈለው ዋጋንም "በሶስት እና አራት እጥፍ" እንዲንር ማድረጉን የኢትዮጵያ የጥራጥሬ እና የቅባት እህል ላኪዎች ማህበር አሰረድቷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

