top of page

የሚያዝያ ወር የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ከ11 በመቶ መሻገሩን መንግስት ተናገረ።

  • May 8
  • 1 min read

ሚያዝያ 30/2018


የሚያዝያ ወር የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ከ11 በመቶ መሻገሩን መንግስት ተናገረ።


አምና በዚህ ወቅት የዋጋ ግሽበቱ 14.4 በመቶ እንደነበር ያስታወሰው የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ሲሆን ዘንድሮ በመጠኑ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል።


የዘንድሮ የሚያዝያ ወር የግሽበት ምጣኔ 11.7 በመቶ ነው።


ከባለፈው ወር ደግሞ 2.2 በመቶ ያህል ጨምሯል።



በተለይ ምግብ ነክ የሆኑና አልኮል የሌላቸው መጠጦች ደግሞ ከፍተኛ ሆኖ የዋጋ ግሽበት ምጣኔአቸው 13.5 በመቶ ደርሷል።


ለአብነትም አትክልት፣ ስጋ፣ የወተት ተዋፅዖዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይት እና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል ብሏል አገልግሎቱ ባወጣው መረጃ።


ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 9.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን የትራንስፖርት ዋጋ በ13 በመቶ ከፍ ብሏል።


በምግብ ቤቶች እና ሆቴሎች 10.5 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።


እንዲሁም ሌሎች በሚል አገልግሎቱ በጠቀሳቸው እቃዎች እና አገልገሎቶች የ15.9 በመቶ መመዝገቡ ተጠቅሷል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page