top of page

በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ500,000 እና 400,000 ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ።

  • 1 day ago
  • 1 min read

ግንቦት 3/2018


በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ500,000 እና 400,000 ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ።


መንሱር ጀማል የተባለው ተከሳሽ ግን አቃቢ ህግ መቃወሚያ ስላቀረበበት ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ በ1.9 ቢሊዮን ብር የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፈቅዷል።


ባለፈው ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከ5 ተከሳሽ መንሱር ጀማል ውጭ ባሉ ተጠርጣሪዎች ከሀገር እንዳይወጡ እና ከፍ ያለ ዋስትና አስይዘው የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከውጭ ሆነው ጉዳያቸውን ቢከታተሉ እንደማይቃወም አስረድቶ እንደነበር ይታወሳል።


ዛሬ በዋለው ዝግ ችሎት ተርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮላቸው፣ ከእስር ተፈትተው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።


በዚህ መሠረት ከአንድ እስከ አራት ያሉ ተከሳሾች ማለትም ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሰለሞን ቦጋለ፣ ይገረም ደጀኔና ዳንኤል ተገኝ በ500 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ሲፈቀድላቸው።


ስድስተኛና ሰባተኛ ተከሳሽ አብርሀም ግዛውና ካሊድ ናስር በ400 ሺህ ብር እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ጠበቃ አበባው አበበ ነግረውናል።


አምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል በተመለከተ አቃቢ ህግ ባቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ 8 ሰዓት ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃ አበባው አበበ ተናግረዋል፡፡


ሁሉም ተከሳሾች ከሃገር እንዳይወጡ እገዳም ተጥሎባቸዋል ተብሏል።


ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page