top of page

ትንባሆ በሚጨስባቸው የግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ብርቱ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡

  • May 7
  • 1 min read

የሚያዝያ 29/2018


ትንባሆ በሚጨስባቸው የግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ብርቱ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡


በትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ትንባሆ ሲያጨሱ ተገኝተው እርምጃ የተወሰደባቸውም እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡

ይህንን ያደረግሁትም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ነው ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፡፡


ትንባሆን በማንኛውም አይነት ሁኔታ መጠቀም የበዙ የጤና ችግሮች እንዳሉት ወጣቶች እንዲያወቁት የግንዛቤ ስራ እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል፡፡



በተጨማሪም በህጉ መሰረት ሲጋራን በነጠላ መሸጥ በህግ ቢከለከልም አሁንም በነጠላ የሚሸጡ እና የሚገዙ በየቦታው እንደሚታዩም ተነስቷል፡፡


እንዲህ በሚያደርጉት ላይ የማስተማርና እርምጃ የመውሰድ ስራ እየተሰራ መሆኑን እና መልካም የሚባል መሻሻል መገኘቱን የተናገሩት ደግሞ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የናርኮቲክ፣ ሳይኮትሮፒክ እና ትንባሆ ቁጥጥር ዴስክ ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ገመዳ ናቸው፡፡


እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት የትንባሆ ቁጥጥር ስራዎችን በህግ በማስደገፍ ቢሰሩም ኢንዱስትሪዎች ደግሞ በተለይ ወጣቶችን በትንባሆ ሱስ ለማስያዝ የተለያዩ አማላይ ስልቶችን እየተጠቀሙ ስለሆነ በጊዜ ትምህርት መስጠትና መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን አስረድቷል፡፡


የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች የትምባሆ ምርቶች በህፃናትና ወጣቶች ዘንድ ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደ ቸኮሌት፣ ቫኒላ፣ ኮኮናት፣ አፕልና የሌሎች ፍራፍሬዎችን ልዩ ልዩ ጣዕም የያዙ ማጣፈጫዎችን ይጠቀማሉ ሲባልም ሰምተናል፡፡

ትንባሆ መጠቀም፤ ለልብ እና የደም ዝውውር በሽታዎች፣ ለመተንፈሻ አካላት ችግሮች፣ ለስኳር በሽታ እና የሳንባ፣ የፊኛ፣ የጉሮሮ እና የአፍ ካንሰርን ጨምሮ ከ20 በላይ ለሚሆኑ የካንሰር አይነቶች የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምር ተነግሯል።


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page