top of page

በአጭር ጊዜ ለግንባታ የሚጠይቀውን በጀት አግኝተው ግንባታን ይከውኑት ይሆን?

  • May 8
  • 2 min read

የሚያዝያ 29/2018

የትምህርት ሚኒስቴር በቀሪዎቹ 4 ወራት 1,452 የቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ክልሎች ለመገንባት በቅብሩ ከክልሎች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡


እነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገነቡት ግማሹ በትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በክልሎቹ በራሳቸው ወጪ ነው፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር ለሚያስገነባቸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 40 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ከአጋር አካላት በእርዳታ ማግኘቱን ተነግሯል፡፡


ታዲያ ክልሎች በአጭር ጊዜ ለግንባታ የሚጠይቀውን በጀት አግኝተው ግንባታን ይከውኑት ይሆን? የተለያዩ ክልሎችን ጠይቀናል፡፡


የደቡብ ኢትዮጵ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በክልሉ የሚገነባው 70 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡



እነዚህ ትምህርት ቤቶች ሲገነቡ በክልሉ ውስጥ በሚኖሩ ሁሉም ወረዳዎች ቢያንስ 1 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲኖረን ያስችላል ብለዋል፡፡


እነዚህ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የበጀት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የነገሩን ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየመከርንበት ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ባለፉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት ቁጥር 34 ሺህ እንደሆነ ነግረውናል፡፡



ከዚህ ውስጥ 20,100 የሚሆኑት የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ነው ያሉ ሲሆን ይህን ያህል ቁጥር ያለው ትምህርትቤት ለመገንባት የተቻለው በክልሉ ያለው ማህበረሰብን በማስተባበርና ከባለሀብቶች ጋር በመቀራረብ ነው ብሏል፡፡


አሁን የሚገነቡትም ትምህርት የፋይናንስ ክፍተት እንዳይፈጠር ቤቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር እንሰራለን ብለዋል፡፡


የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሳ አደም (ዶ/ር) በአፋር ክልል በ560 ትምህርት ቤቶች የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት እየሰጡ ነው ይላሉ፡፡



አሁን በክልሉ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በ4 ወራት ውስጥ ሚገነቡት ትምህርትቤቶች እውን ለማድረግ ክልሉ ከባለሃብቶች ጋር እየመከረበት ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


ሶስቱም የክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት ግንባታውን በቀሪ 4 ወራት ውስጥ ገንብቶ ለማድረስ የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት መኖሩን የጠቀሱ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ማህበረሰቡን ለማስተማመር ማቀዳቸውን ነግረውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 
በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡

ሰኔ 15/2018 በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት በተለያዩ ሶስት ፋብሪካዎች ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ ከ69 ቶን በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page