ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብል ምርት ከሚያስፈልገው ግብአት ውስጥ ገበሬው የሚቀርብለት ከ35 በመቶ እንደማይበልጥ ተነገረ፡፡
- 2 days ago
- 2 min read
ግንቦት 4/2018
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብል ምርት ከሚያስፈልገው ግብአት ውስጥ ገበሬው የሚቀርብለት ከ35 በመቶ እንደማይበልጥ ተነገረ፡፡
ይህ የተባለው በሰብል የግብርና ግብአት ላይ ትኩረት ያደረገ ሀገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበርያ ኤግዚቢሽን ከግንቦት 14 እስከ 16 እንደሚካሄድ ይፋ በተደረገበት መግለጫ ነው፡፡
ለግብርናው ምርታማነት የሚያሰፈልጉ ግብአቶችን በበቂ ሁኔታ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ይሁንና በተለያየ ምክንያት ገበሬው ግብአት እየደረሰው እንዳልሆነ ይነገራል፡፡
ለዚህ አንደኛው ምክንያት የገበያ ትስስር ችግር ነው የተባለ ሲሆን የሚሰናዳው ኤግዚቢሽንም ለተጠቀሰው ችግር መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎበታል፡፡
በኤግዚቢሽኑ ለሰብል ልማት የሚያገለግሉ የአፈር ማዳበርያ ፣ ፀረ ነፍሳት ፣ ፈንገስ ማጥፊያዎች ፣ አረም ማጥፊያ ፣ የግብርና ስራን ለማቀላጠፍ ወደ ስራ የገቡ የድሮን ቴክኖሎጂዎች ና ሌሎችም ግብአቶች ይቀርባሉ ተብሏል።
ኤግዚቢሽኑን ያዘጋጀው ዊ-ሊንክ የተባለ ድርጅት ሲሆን አምራቾች ፣ አከፋፋዮች ፣ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንደሚሳተፉ ተጠቅሷል።
ግብርናውን ለማሳደግ በተለይም የሰብል ልማት ላይ ዋንኛው ጉዳይ የአፈር ማዳበርያ እና ሌሎች ግብአቶች ናቸው ያሉት የዊ-ሊንክ ድርጅት ማናጀር እንዳለ ገብሬ (ዶ/ር) በዚህ ዘርፍ የገበያ ትስስር ክፍተት አለ ብለዋል።
ዊሊክ ይህንን ክፍተት ለመፍታትና ከውጪ የሚገባው የግብርና ግብአት በሀገር ውስጥ ለመተካት እንዲያስችል ለማድረግ በውጪ ያሉ ግዙፍ የዚህ ዘርፍ ተዋናዮችን ለማምጣት እየሰራ ነውም ይላሉ።
የድርጅቱ የማርኬቲን ዳይሬክተር አቶ በሀይሉ ካሳሁን ለግብርና ስራ የሚያስፈልጉ የሰብል ግብአቶች አጠቃቀም ኢትዮጵ ውስጥ ሲታይ እጅግ ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡
ገበሬው ከሌሎች ጋር ሲወዳደር መጠቀም ከነበረበት ግብአት ውስጥ አጠቃላይ የሚጠቀመው 35 ከመቶ እንደማይበልጥ ይህም የሆነው በበቂ ሁኔታ አስፈላጊው ግብአት ስለማይቀርብለት ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ገበሬ አሁን ላይ የአፈር ማዳበርያ አጠቃቀሙ ከ50 እስከ 60 በመቶ ብቻ እንደሆነ ጥናት ሳያል ያሉ ሲሆን ገበሬው አሁንም ድረስ የግብርና ዘርፍን የተመለከቱ ቴክኖሎጂዎችና መረጃዎች በተገቢው መንገድ ተደራጅቶ እየደረሰው አይደለም ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የድርጅቱ ምክትል ማናጀር አቶ ዳንኤል ካሳሁን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአመት ልግብርናው ዘርፍ ከምታወጣው ወጪ ትልቁን ቦታ የሚይዘው ይሄ የግብአት ዘርፍ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
ከግዙፍ እርሻ ጀምሮ አነስተኛ ማሳ ድረስ እንደየ አቅሙ ገበሬው ያገኘውን ግብአት እየተጠቀመ ነው ነገር ግን የበለጠ ዘርፉን ለማሳደግና ተወዳዳሪ ለመሆን ተቀራርቦ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
አሁን የሚደረገው የመጀመርያው ሀገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበርያ ኤግዚቢሽን ሲካሆድ የገብያ ትስስር ከመፍጠር ባለፈ ውይይቶች መዘጋጀቱንም ተጠቅሷል።
አውደ ርእዕዩ በኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ሰምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments