የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 1,139 የአገልግሎቱ ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰዱን ተናገረ፡፡
- 10 hours ago
- 1 min read
ግንቦት 4/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 1,139 የአገልግሎቱ ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰዱን ተናገረ፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች መካከል 16ቱ ከስራቸው ሲሰናበቱ፤ 721ዱ የደመወዝ ቅጣት እንዲሁም 402 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው ተብሏል፡፡
አገልግሎቱ በሠራተኞች ላይ ከወሰዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች መካከል 103 ሠራተኞች ላይ በደንበኞች የቀረበን ጥቆማ በመመርመር የወሰደው መሆኑንና ቀሪ 1,036ቱ ተቋሙ በራሱ ግኝት አጣርቶ የወሰዳቸው እርምጃዎች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡

ባለፉት 9 ወራት አገልግሎቱ በሙስና መጠቆሚያ ዘመናዊ መተግበሪያ እና በሌሎች አማራጮች ከደንበኞቹ የደረሱትን 427 ጥቆማዎችን መርምሮ በ103 ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል ተብሏል፡፡
በደንበኞቹ በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት 14 የፅሁፍ፣ 80 የደሞዝ ቅጣት፣ 2 ከቦታ የማንሳትና 7 ስንብት በድምሩ 103 እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቅሷል፡፡
የሙስና ጥቆማ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል የአዲስ ቆጣሪ ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥና አስቸኳይ ጥገና፣ የቆጣሪ ንባብና የቢል ስብሰባ እንዲሁም ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ይገኙበታል፡ እንደሚገኙበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በላከን መግለጫ ተናግሯል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments