top of page


ጥቅምት 6 2018 - ''ተገልጋዮችን የሚያንገላቱ፣ ጉቦ የሚቀበሉ ሰራተኞቼን እያባረርሁ በህግ እንዲጠየቁም እያደረግሁ ነው'' ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
ተገልጋዮችን የሚያንገላቱ፣ ጉቦ የሚቀበሉ እና መሰል ጥፋቶችን የሚሰሩ ሰራተኞቼን እያባረርሁ በህግ እንዲጠየቁም እያደረግሁ ነው ሲል የከተማዋ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡   የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባና ያላገባ ሰነዶችን ማግኘትና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት ተገልጋዩን የሚያመላልሱ ሰራተኞች መኖራቸው ተነግሯል።   እነዚህን ሰራተኞች በስልጠና አግዛለው፤ አጥፍተው የሚገኙትንም መቅጣት እጀምራለሁ ብሏል ተቋሙ።   ይህንን ያሉን የኤጀንሲው ምክትል ዳሬክተር ጥጋቡ ሹመይ ናቸው።   ነዋሪዎች ከተቋሙ አገልግሎት ፈልገው በሚመጡበት ወቅት፤ ጉዳይ የሚያንዛዙ የተቋሙ ሰራተኞች እንዳሉ ደርሼበታለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡   በተለይም እንዲህ ዓይነቱ ችግር በወረዳዎች ላይ እንደሚታይ ነግረውናል፡፡   በተያያዘም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12
Oct 161 min read


ጥቅምት 6 2018 - የኢትዮጵያ የሚዲያ የልህቀት ማዕከል ስራ ጀመረ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ስራ የጀመረው ማዕከሉ የሚዲያ ተቋማትንና  የባለሞያዎችን አቅም የመገንባት ስራን ይሰራል ተብሏል። ማዕከሉ የተመሰረተው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን መሆኑን በዝግጅቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡ በልህቀት ማዕከሉ መክፈቻ ዝግጅት ላይ የሕዝብ እንደራሴዎች  ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡ በልህቀት ማዕከሉ በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተነግሯል። የማዕከሉ መቋቋም ዋና ዓላማ የጋዜጠኞችን የሙያ እውቀት እና ክህሎትን ማሳደግ ላይ በትኩረት መስራት ነው ተብሏል። በአለም አቀፍ የሚዲያ አሰራር መሰረት ባለሙያው ከጋዜጠኝነት ትምህር
Oct 161 min read


ጥቅምት 6 2018 - “የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ስርዓት ውስጥ”
የግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሰጠት በዚህ ዓመት ተጀምሯል፡፡ ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ወጥቶታል፡፡ አንዳንዶች እስይ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አስፈላጊ አይደለም ልጆቻችንም አይማሩም ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ በቋንቋ አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ ባያነሱም ከስንተኛ ከፍል ጀምሮ ነው ቋንቋው ለተማሪዎች መሰጠት ያለበት በሚለው ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ “የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ስርዓት ውስጥ” በሚል ርዕስ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም  በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አዘጋጅነት በርካታ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተሳታፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄዷል፡፡ በስነ ልሳን መምህሩ እና ተመራማሪው ዘላለም ልየው(ፕ/ሮ) አወያይነት፤ በበድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር) እና በይኩኖአምላክ መዝገቡ መካከል ውይይ
Oct 165 min read


ጥቅምት 5 2018 በኮሪደር ልማት ላይ ሸንቶ ያመለጠ ግለሰብ ተይዞ 2,000 ብር ተቀጣ፡፡
በኮሪደር ልማት ላይ ሸንቶ ያመለጠ ግለሰብ ተይዞ 2,000 ብር ተቀጣ፡፡ መኪና በማቆም በኮሪደር ልማት ላይ የምትሸኑ ከድርጊታችሁ ተጠንቀቁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሳስቧል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ከዋናው አየር መንገድ ልዩ ስሙ ወሎ ሰፈር አካባቢ መኪና በማቆም በኮሪደር ልማት ላይ ሽንት በመሽናት ያመለጠ ግለሰብ ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋሉን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ግለሰቡ በፈፀመው የደንብ መተላለፍ ም  2,000 ብር መቅጣቱ ተነግሯል፡፡ መሰል ደንብ ተላለፊዎች  ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣ ደንብ ተላላፊዎችም ከድርጊታቸው ተቆጠቡ ሲል  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  አሳስቧል። ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲ
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል?
የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ትናንት በተጀመረው እና እስከ ነገ በሚቀጥለው ጉባኤ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች፣ ባህርተኞች እና ቀጣሪ ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው፡፡ ለመሆኑ ይህ ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል ስንል #የኢትዮጰያ_ማሪታይም_ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋን ጠይቀናቸዋል፡፡ ጉባኤው በዘርፉ ለሚሰለጥኑ ባለሞያዎች የገበያ ትስስር፣ ለማሰልጠኛ  ተቋማት ደግሞ ዘርፉ የሚፈልገውን አለም አቀፍ ክህሎት ምን መሳይ ነው የሚለው እንዲያውቁት እንዲሁም ከትልልቅ የዘርፉ ድርጅቶች ልምድ ለመውሰድ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል ሀላፊው፡፡  ኢትዮጵያ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢኒስትቲዩት እና በቢሾፍቱ የሚገኘው የባቦጋ
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ለመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ እንዲሆን ተወስኗል
ኢትዮጵያ ከመድሀኒት ፍላጎቷ ከ40 በመቶ በላዩን በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን መቻሏ ይነገራል፡፡ መንግስት ለመድሀኒት ግዥ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በሂደት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ሙሉ በሙሉ የማስቀረት ፍላጎት አለው፡፡ ኢትዮጵያ ካሏት 10 የኢኮኖሚ ዞኖች የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ለመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በኢንዱስትሪ መንደሩ ግን የሚፈለገውን ያህል ባለሀብቶች እየገቡ አይደለም፡፡ ታዲያ የታሰበውን ግብ እንዴት ማሳካት ይቻላል? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRa
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - የመንግስት ሰራተኞች ከፈቃዳቸው ውጪ፣ ከደመወዛቸው ገንዘብ እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ
ይህም ህገ ወጥም አሳሳቢም ነው ተብሏል። ይህንን ያለው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው። ተቋሙ ከህግ ውጪ የመንግስት ሰራተኞች ከደመወዛቸው የሚቆረጥባቸው ገንዘብ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ተደጋጋሚ ቅሬታ እየቀረበልኝ ነው ብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ያሉ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ ከደመወዛቸው ላይ ገንዘብ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነግረውኛል ብሏል። በተመሳሳይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞንም በተለያዩ ወረዳዎች የሚሰሩ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተነግሯል። ይህም የችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳያል ብሏል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ መግለጫ። ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ስምምነቱን በፅሁፍ ሲገልፅ፣
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት 13.2 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ፡፡
ያለፈው ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት መጠን 13.2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናግሯል። ከአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች (Food Items) የዋጋ ግሽበት 12.1 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) የዋጋ ግሽበት ደግሞ 14.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ነሐሴ ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በነሐሴ ወር አጠቃላይ የግሽበት ምጣኔው  13.6 በመቶ ነበር፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Faceb
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - በታዋቂ ሰዎች የተዋወቁ ምርትና አገልግሎቶች ''የሀሰት ሆነው አገኘናቸው እነሱን አምነን ተታለልን'' የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ፡፡
በገበያው የሚሸጥ የሚለወጠው ብዙ ነው፡፡ ቤት፣ መኪና፣ አክሲዮን፣ የፋብሪካ ምርት፣ አገልግሎት፣ በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚተዋወቀው ብዙ ነው፡፡  ገዥና ሻጭም በዚሁ የማስተዋወቂያ መንገድ በቀላሉ ይገናኛል፡፡ ውል ይታሰራል ግብይት ይፈፀማል፡፡ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ #ታዋቂ_ግለሰቦችን መጠቀም አምባሳደር አድርገው ማሰራታቸውም የተለመደ ነው፡፡ አንዳንዴ ግን በእነዚህ ታዋቂ ሰዎች የተዋወቁ ምርትና አገልግሎቶች ''የሀሰት ሆነው አገኘናቸው እነሱን አምነን ተታለልን'' የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ፡፡ ለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ህጉ ምን ይላል? ተጠያቂውስ ማነው? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ገዛ ጌታሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube...
Oct 151 min read


ጥቅምት 4 2018 - ህንድ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የባህላዊ መድሀኒት ሀብት በሳይንስ የተደገፈ እንዲሆን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገረች።
ህንድ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የባህላዊ መድሀኒት ሀብት በሳይንስ የተደገፈ እንዲሆን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገረች። በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የህክምና ግብዓት፣ የመድሃኒት አቅርቦት እና የህክምና እሴት ለማሳደግ ይርዳል የተባለለት ጉባኤ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በህንድ ኤምባሲ ተካሄዷል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ከህንድ ሀገር የመጡ የህክምና ባለሞያዎች፣ የጤና ተቋማት ሃላፊዎች እና መድሃኒት አስመጪዎች ተገኝተዋል። በመድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር፤ አፍሪካ ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ቀዳሚ ተጎጂ አህጉር መሆኑን አስረድተዋል። የሳምባ፣ ቲቢ፣ የወባ፣ ኤችአይቪ፣ የአዕምሮ ህመም፣ ካንሰር፣ ስኳር፣ ኩላሊት እና በመሰል ህመሞች አፍሪካ እንደምትሰቃይ ተና
Oct 143 min read


ጥቅምት 4 2018 - ኢትዮጵያ ታሪኳን ሙሉ ከዓለም ፊት ሲያሳንሳት የቆየው አንዱና ዋና ጉዳይ የምግብ ማጣት
የሀገሬው ህዝብ  ከገበታው ብዙ ጊዜ የሚያገኘው እንጀራ፣ ጤፍን እንኳን የጠገቡት ሀገሮች ረሃብተኞች የሚመገቡት እህል ነው የሚል ተቀጽላ  እስከመስጠት የደረሱበት ነው፡፡ "አንደ ኢትዮጵያዊ፣ አንደ ሀገር ስናስበው የፖለቲካ ታሪካችን ያበላሸብን፣ ውጪ ሀገር ስንሄድ አንገታችንን የምንደፋበት፣ የምናዝንበት ጉዳይ ረሃብ በሚባለው ነው፡፡ ጤፍ ምንድነው ሲባል የረሃብተኞች ምግብ ነው ይባላል፡፡ እናንተ እኮ አልተገዛችሁም ግን ረሃብተኛ ናችሁ ይሉናል" ይላሉ የግብርና ተመራማሪው እና መምህሩ ፍሬው መክብብ(ፕ/ር)፡፡ #የምግብ ጉዳይ መልስ ለመስጠት ሀገራት አንዳላቸው አቅም መንገዳቸውም ይለያያል፡፡ ገንዘብ ካለ ምግቡ የትም ይመረት ገዝተው የሚበሉ፣ ዜጎቻቸውን የሚመግቡ ሀገራት ብዙ ናቸው፡፡ የገበሬ ሀገር ባይሆኑም ህዝባቸው የሚመገበው አያጣም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 
Oct 141 min read


ጥቅምት 4 2018 - ''መጪው ምርጫ የሚደረገው ከዚህ በፊት በነበረው የምርጫ ሥርዓት፣ ወይስ?'' ኢዜማ
መጪው ምርጫ የሚደረገው ከዚህ በፊት በነበረው የምርጫ ሥርዓት፣ ወይስ ሀገራዊ ምክክሩ በሥምምነት የሚቀይራቸውን ከፖለቲካና ከምርጫ ሥርዓቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ባካተተ ሁኔታ በአዲስ መልክ  ነው ሲል ኢዜማ ጠየቀ፡፡ በአዲስ መልክ ምርጫ ለማካሔድስ ምርጫው በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ ይቻላል ወይ ሲልም ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አንስቷል? ፓርቲው ይህንነ ጥያቄ ያነሳው ምረጫ ቦርድ የምርጫ ህጉ አንዳልተቀየረ ከተናገረ ብኋላ በመሆኑ ጥያቄው የረፈደበት አይሆንም ወይ? ፓርቲውን ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….  የኔነህ ሲሳይ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/Sheger
Oct 141 min read


ጥቅምት 4 2018 - የቀድሞ ተዋጊዎች እና ሌሎች አካላት በትግራይ ክልል ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ውስን በሆነ የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ውስጥ መግባታቸውን ጥናት አሳየ
የቀድሞ ተዋጊዎች እና ሌሎች አካላት በትግራይ ክልል ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ውስን በሆነ የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ውስጥ መግባታቸውን ጥናት አሳየ። ሰላም፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ እድገት ተጋላጭ ለሆኑ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በሚል ሃሳብ የቀድሞውን መተማመን እና ችግር አፈታት ወደ ቀድሞው ለመመለስ ያለመ ጉባዔ ዛሬ እየተካሄደ ነው። በጉባዔው ላይ ''በክልሉ መተማመን ለመፍጠር እና የቀድሞ ችግር አፈታትን መመለስ'' በሚል ርዕስ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ተጠንቶ ቀርቧል። በጥናቱ መሰረት የሰሜኑ ጦርነት በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሃብት መቀራመትን አባብሷል፣ የመንግስት መዋቅር ደካማ እንዲሆን እና ማህበራዊ ቀውስ የተባባሰ እንዲሆን አድርጓል ተብሏል። የአካባቢ አስተዳደሮች ሙሰኞች ተደርገው በማህበረሰቡ እንዲሳሉ እና መንግስት እንዳይታመን የሰሜኑ ጦርነት ማድረጉን
Oct 141 min read


ጥቅምት 4 2018 - የንጋት ሃይቅ ሳይበከልና በደለል ሳይጎዳ እንዲቀጥል የማድረግ ሰራ መሰራት አለበት ተባለ።
የንጋት ሃይቅን ከአደጋ የሚጠብቅ በዙሪያው የሚሰራው ስራም በጥናት የተደገፈና የተናበበ እንዲሆን ያደርጋል የተባለለት ፍኖተ ካርታ እየተሰናዳለት ነው። ኢትዮጵያ ከ #ንጋት_ሀይቅ በሚገባት ልክ መጠቀም ያለባት እንዴት ነው ለሚለው ጥያቄ ፍኖተ ካርታው መልስ ይሰጣል ብለዋል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል፣ የንጋት ሃይቅም ይመራበታል የተባለ የንጋት ሃይቅና አካባቢው የተቀናጀ ፍኖተ ካርታ ተሰናድቶ ምክክር እየተደረገበት ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤት ሆኖ ያሰራው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን መሰራቱ ተነግሯል። የንጋት ሃይቅ ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ይፋ ሲሆን ከዚህ በኋላ በውሃ ሀብቱ ዙሪያ ምን ይሰራ ለሚለው መልስ ይሰጣል ተብሏል። የህዳሴውን ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን ተከትሎ ከውሃው
Oct 142 min read


ጥቅምት 4 2018የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን እንድታቋቁም የሚያስችላትን ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አጸደቀ፡፡
ሀገሪቱ  የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤና አገልግሎት፣ በሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ላይ ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት የመምራትና የማስተባበር ሃላፊነት እንዲኖረው ተደርጎ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል ተብሏል፡፡ ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ ከተወያየበት በኋላ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትረ ጽ/ቤጽ ተናግሯል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት  ሌለው የተወያየበት ጉዳይ በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በወጣ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ የሚሰጣቸውን የምርምር፣ የቴክኖሎጂ 
Oct 141 min read


ጥቅምት 4 2018ኢትዮጵያ በባህር ላይ የተለያዩ ስራዎችን የሚከውኑ 2,600 የማሪታይም መሀንዲሶችን አሰልጥና ለውጭ ገበያ አቅርባለች ተባለ።
የባህር ባለሞያዎቹን እያሰለጠነ የሚገኘው የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሰልጥነው በውጭ ሀገራት በተለያዩ የስራ እርከን ተቀጥረው እየሰሩ መሆኑ ተነግሯል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ(ዶ/ር) ሰልጥነው በውጪ ሀገራት ከተቀጠሩት መካከልም 26ቱ በአለም ትልልቅ የዘርፉ ተቋማት በከፍተኛ ሀላፊነት፣ አማካሪነት እና ባለሞያነት እየሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል። ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በሜካኒካል እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና የተመረቁ ምሩቃንን መልምሎ ለ6 እና ለ9 ወራት በማሰልጠን ነው የማሪታይም ዘርፍ ባለሞያዎችን እያበቃ ያለው ተብሏል። የማሪታይም መሀንዲሶቹ የሚያሰለጥኗቸ፤ የውጪ ሀገራት ዜጎች መሆናቸውንና ስልጠናውም አለም አቀፍ ስታንዳርድ ያሟላ ነው ሲሉ መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ባህርዳር ዩኒቨ
Oct 141 min read


ጥቅምት 3 2018 - የመምህርነት ሞያ ያላቸው ታራሚዎች እና የፖሊስ አባላት ተመልምለው፤ እዚያው ባሉ ት/ቤቶች እንዲያስተምሩ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
በማረሚያ ቤት የሚገኙ የመምህርነት ሞያ ያላቸው ታራሚዎች እና የፖሊስ አባላት ተመልምለው፤ እዚያው ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲያስተምሩ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡ ባለሞያዎቹ ያገለገሉበት ሰዓትና ቀን ተቆጥሮ ክፍያ...
Oct 131 min read


ጥቅምት 3 2018 - ለ2 ወር በከፊል ዝግ ሆነዉ የቆዩት ፍ/ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ የችሎት አገልግሎት ይመለሳሉ ተባለ
መደበኛ የችሎት አገልግሎቱም በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ፈጣንና ጥራት ያለዉ የዳኝነት ስራ የሚሰራበት እንዲሆን ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል። ይህ የተነገረው የ2018 ዓ/ም የመደበኛ የችሎት አገልግሎት ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት...
Oct 131 min read


ጥቅምት 1 2018 ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ መሆኑን ተናገረ።
የአንድ አክሲዮን ትርፍ ወደ 68.3 በመቶ ማደጉንም አስረድቷል። ዘመን ባንክ በ2017 በጀት ዓመት  14.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን በዛሬው እለት ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ባወጣው  ሪፖርት ተናግሯል።...
Oct 111 min read


መስከረም 30 2018 - የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ተናገረ፡፡
ተቋሙ እስካሁን የሰበሰብኩት አጠቃላይ የአረቦን ገንዘብ 15.93 ቢሊዮን ብር ደርሷልም ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በባንክና ማይክሮፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ያስቀመጡ ግለሰቦች ለሚገጥማቸው ችግር...
Oct 101 min read


መስከረም 30 2018 - በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ስር ያሉ ታራሚ ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማሳለፍ ምጣኔ ከሀገራዊ የማሳለፍ ምጣኔ ከእጥፍ በላይ መሆኑ ተነገረ፡፡
በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን  ስር በአባ ሳሙኤል ማረሚያ ማዕከል የሚገኘው የታራሚዎች ትምህርት ቤት፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ያስፈተናቸው ተማሪዎች በቀጥታ እና በረመዲያል መቶ በመቶ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን...
Oct 102 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








