የአካባቢ ጉዳትን የሚቀነሱ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ፈጠራዎቻቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑንን ሪች ፎር ቼንጅ ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- 58 minutes ago
- 1 min read
ታህሳስ 22/2018
የአካባቢ ጉዳትን የሚቀነሱ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ፈጠራዎቻቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑንን ሪች ፎር ቼንጅ ተናገረ፡፡
34 ስራ ፈጣሪዎችም ፈጠራቸውን ለኢንዱስትሪዎችና ለባለሀብቶች እንዲያስተዋውቁ እድል ተመቻችቶላቸዋል ተብሏል፡፡
ከመኖሪያ ቤትና ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ከፋብሪካዎች የሚወጡና አካባቢን የሚበክሉ ቁሶችን እና ፈሳሾችን በድጋሚ ጥቅም ላይ እያዋልነው ሲሉ ስራ ፈጣሪዎች ነግረውናል፡፡
አገልግሎታቸውን ጨርሰዋል ጥቅም መስጠት አቁሟል ከተባሉት መካከል እና በድጋሚ ጥቅም ላይ ከሚውሉት መካከል ፕላስቲኮች፣ ሳንቡሳ እና ቺብስ ከተጠበሰ በኋላ የሚቀረው የምግብ ዘይት እና የመኪናና የተለያዩ ሞባይል እና ላፕቶፖች ባትሪዎች ይገኙበታል፡፡
ከፕላስቲኮቹ ለመንገድ ንጣፍ የሚሆኑ ቴራሶች ከዘይቱ የጫማ ቀለም እንዲሁም ባትሮዎቹ በድጋሚ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደተደረገ ከስራ ፈጣሪዎቹ ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








