top of page

በጥጥ ምርት ላይ የተጣለው ተጨማሪ እሴት ታክስ በሀገር ቤት የሚመረተው ጥጥ ዋጋው እንዲንር አድርጎታል ተባለ፡፡

  • Dec 31, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 22/2018 

 

በጥጥ ምርት ላይ የተጣለው ተጨማሪ እሴት ታክስ በሀገር ቤት የሚመረተው ጥጥ ዋጋው እንዲንር አድርጎታል ተባለ፡፡

 

በዚህም ምንክያት ምርቱን ገበያውን ለመምራት እየተቸገረ መሆኑን የኢትዮጵያ ጥጥ ማህበር ነግሮናል፡፡

 

ሀገር ውስጥ የሚመረተውን የጥጥ ምርት ከውጭ ከሚገባው በዋጋ በኪሎ የ30 ብር በኩንታል ደግሞ የ3,000 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ተነግሯል፡፡

 

በዚህ ምክንያት የሀገር ውስጥ ምርት ገበያው ላይ እንዲወደድና አምራቾችም የሃገር ውስጥ ምርቱን በመወደዱ ምክንያት ቀዳሚ ምርጫቸው እያደረጉት አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ጥጥ ማህበር ነግሮናል፡፡

 

የኢትዮጵያ ጥጥ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ፀጋዬ አበበ እንዳሉት ለሀገር ውስጥ የሚያስፈልግ የጥጥ ምርት በበጀት አመቱ በበቂ ሁኔታ ቢመረትም ገዥ ግን እየተገኘ አይደለም፡፡

 

ባለፈው አመት የጥጥ ምርት አቅርቦት እጥረት እንደነበር አስታውሰው በዚህ አመት ያ ችግር ቢፈታም የሀገር ውስጥ ገበያው ከአለም አቀፍ ካለው ገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር በተዳመጠ አንድ ኪሎ የጥጥ የሃገር ውስጥ ምርት የ30 ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡

 

በሀገር ውስጥና በአለም ገበያው መካከል ያለው የዋጋ ልዩነት እንዲጠብ መንግስት የጣለውን ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንዲያነሳም ጠይቀዋል፡፡

 

ይህ ካልሆነ ገበሬው ጥጥ ማምረቱን ከነአካቴው ሊተው ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ነግረውናል፡፡

 

ኢትዮጵያ በአመት ማምረት ከምትችለው የጥጥ ምርት ውስጥ አሁን ላይ የምታመርተው ከ5 ከመቶ በታች መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

 

በረከት አካሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page