top of page

‘’በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል’’ ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jan 2
  • 1 min read

ታህሳስ 24/2018 

 

 ‘’በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል’’ ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

 

የድንበር ቁጥጥር መበርታት እና በሰው አዘዋዋሪ ደላሎች ላይ የሚወስደው እርምጃ ለቁጥር መቀነስ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብሏል፡፡

 

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሽ ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ በአዋሳኝ ድንበር የሚደረገውን ህገወጥ ፍልሰት በተመለከተ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመተባበር እየተደረገ ባለው ጥብቅ የቁጥጥር ስራ በርካታ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በመያዝ ተጠያቂ እየሆኑ ነው ብለዋል።

 

በዚህም ከዚህ ቀደም በአጎራባች ሀገራት በኩል ይደረጉ የነበሩ በርካታ ህገወጥ ፍልሰቶች እንዲቀንሱ አድርገዋል ይላሉ።

 

በሌላ በኩል ምያንማርን ጨምሮ ከሳውዲአረቢያ፣ ከየመን፣ ከታንዛኒያ እና ከተለያዩ የአለም ሀገራት ለመጡ ስደተኞች ጊዜያዊ መጠለያ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር ቋሚ የስራ እድል እንዲያገኙ ይደረጋል ሲሉ  አቶ ደረጄ ነግረውናል።

 

ባለፉት 6 ወራት ከተለያዩ የአለም ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ34,000 በላይ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉንም ሰምተናል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

 

ፍቅሩ አምባቸው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page