top of page

የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመክፈል አቅም የሌላቸው ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ሊስፋፋ ይገባል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jan 2
  • 1 min read

ታህሳስ 24/2018


የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመክፈል አቅም የሌላቸው ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ሊስፋፋ ይገባል ተባለ፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ የፌደራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በተለያዩ አካባቢዎች ስራ አስጀምሯል፡፡


በአዳሪ ትምህርትቤቶቹ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ያመጡና የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የቻሉት ብቻ ናቸው፡፡


ይህ ስራ በባለሙያዎች እንዴት ይታያል? በምንስ መንገድ መመራት አለበት? የዘርፉን ባለሙያ ጠይቀናል፡፡


የትምህርት ባለሙያ እና በደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ መምህር ሆኑት ዳምጠው ወልዴ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም በግልና በምንግስት ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶችን ለማስፋፋት መሞከሩን ያስታውሳሉ፡፡


እንዲህ አይነት ትምህርትቤቶች መስፋፋታቸው ክህሎት ያለው ተማሪ ለማፍራት ሁነኛ ስፍራ ናቸው ይላሉ፡፡


ምክንያታቸው ደግሞ ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶች ሲመሰረቱ የበቁ መምህራንና በትምህርት አቀባበላቸው ጥሩ አቅም ያላቸው ተማሪዎች ነው ሚገናኙት፡፡


ለመማር ማስተማር የሚያስፈልገው ግብአትም ከሌሎች ትምህርትቤቶች በተሻለ መንገድ በነዚህ ተቋማት የተሟላ የመሆን እድል አላቸው ብለዋል፡፡


አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ብቃትን መሰረት ያደረገ ነው ይሄ ደግሞ ተማሪዎቹ በተግባር ተኮር በተደገፈ የትምህርት አሰጣጥ ሲማሩ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡


አሁን ትምህርት ሚኒስቴር የተቀበላቸው ተማሪዎች ከሀገሪቱ የተሻለ አቅም ያላቸው ተማሪዎች ናቸው፡፡ ይሄ ደግሞ ነገ ክህሎቱ የዳበረ የሰው ሀይል እንድናገኝ ያስችለናል ሲሉም ተስፋቸውን ተናግረዋል፡፡


ትምህርት ሚኒስቴር ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶችን ሲያስፋፋ አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል በማለት ይመክራሉ፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር በ2ተኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ትምህርትቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን የቀጠረው በማወዳደር መሆኑ ትክክለኛ አካሄድ ነው ብለዋል ዳምጠው ወልዴ (ዶ/ር)፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page