የሶማሊላንድ አስተዳደር በግዛቷ የእስራኤል የጦር ሰፈር እንዲገነባ ተስማምቷል መባሉን ሐሰት ነው አለ፡፡
- Jan 2
- 2 min read
ታህሳስ 24/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
የሶማሊላንድ አስተዳደር በግዛቷ የእስራኤል የጦር ሰፈር እንዲገነባ ተስማምቷል መባሉን ሐሰት ነው አለ፡፡
እስራኤል ባለፈው ሳምንት አርብ ለሶማሌላንድ የነጻ አገርነት እውቅና ሰጥታለች፡፡
የእስራኤል እርምጃ በሶማሌያ እና በምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር አጋሮች ዘንድ ውግዘት አስከትሏል፡፡
የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሶማሌላንድ ከእስራኤል እውቅና ለማግኘት የጦር ሰፈር እንድትገነባ መፍቀዷን ተናግረዋል፡፡

ይሄም በደህንነት መረጃዎች የተደረሰበት ነው ማለታቸው አልጀዚራ ፅፏል፡፡
ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በተጨማሪም በእስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚነቀፉ ፍልስጤማውያን በሶማሌላንድ ለማስፈር ስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡
የሶማሌላንድ አስተዳደር ግን ይሄ በፍፁም ሐሰት ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡
እስራኤልም ለሶማሌላንድ የነፃ አገርነት እውቅና መስጠቴ ለዲፕሎማሲያዊ ዓላማ ብቻ ነው ብላለች፡፡
ሶማሌላንድ ከተቀረችው ሶማሌያ ከተነጠለች 34 አመት ሆኗል፡፡
በኢራን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ያስከተለው ግጭት የሰዎችን ሕይወት መንጠቅ ጀመረ ተባለ፡፡
በአገሪቱ ከልክ በላይ የሆነው የኑሮ ውድነት ካለፈው እሁድ አንስቶ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እና ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞ ማስከተሉን ገልፍ ኒውስ ፅፏል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉ ግጭት ጭምር እያስከተለ ነው ተብሏል፡፡
በአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል በሰልፈኞች እና በፀጥታ ሀይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰልፈኞች እና አንድ የፀጥታ ባልደረባ መገደላቸው ተሰምቷል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉ ሀይል ጭምር እየተቀላቀለው ነው ተብሏል፡፡
ኢራን በኒኩሊየር መርሐ ግብሯ የተነሳ ዳግም ለአለም አቀፍ ምጣኔ ሐብታዊ ማእቀብ ተዳርጋለች፡፡
ከዚያም በፊት በአሜሪካ የተናጠል ማዕቀብ ስትደቆስ ቆይታለች፡፡
ይሄ ሁሉ ጫና አሁን በአገሪቱ የኑሮ ውድነቱ ከልክ በላይ እንዲሆን ማድረጉ ይነገራል፡፡
በየመን ደቡባዊ ክፍል የመገንጠል ዓላማ አለው የሚባለው STC ከያዛቸው አካባቢዎች ለቅቆ እንዲወጣ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገው፡፡
ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግስት STC በቅርቡ በውጊያ ከያዛቸው ሐድራማውት እና አል ማሐራ ግዛቶች ለቅቆ እንዲወጣ ቀደም ሲል ጠይቆ እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡
ሳውዲ አረቢያም ለSTC ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ ነበር፡፡
በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ይደገፋል የሚባለው STC ግን ጥሪውን አልቀበለውም ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የየመኑ አጋጣሚ በሳውዲ መራሹ የጦር ጥምረት ላይ ስንጥቃት ፈጥሯል፡፡
ኢሚሬትስ ከጥምረቱ ወጥቻለሁ ያለችው ሰሞኑን ነው፡፡
አለም አቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግስት መቀመጫው በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ነው፡፡
ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ አብዛኛውን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት የሁቲ ታጣቂዎች እንደሆኑ መረጃው አስታውሷል፡፡
በስዊዘርላንድ ደቡባዊ ክፍል በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ የ40 ያህል ሰዎች ህይወት የቀጠፈበት የእሳት አደጋ እየተመረመረ ነው ተባለ፡፡
በቃጠሎው መሞታቸው ከተረጋገጠገው ሌላ 115 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል መባሉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
ብዙዎቹ ብርቱ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ተብሏል፡፡
በአደጋው የሞቱትን ሰዎች ማንነት የመለየት ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የቃጠሎ አደጋው የደረሰው ሰዎቹ በአዲስ አመት መቀበያ ፈንጠዝያ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡
በአደጋው ከሞቱት እና የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የበርካታ አገሮች ዜጎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
አካባቢው በበረዶ ሸርተቴ መዝናኛነቱ የሚታወቅ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1





Nice read! Your explanation about branding and consistency really stood out. It’s interesting how successful platforms focus on clarity and trust-building. Sites like Juan365 app seem to follow similar approaches. Thanks for the helpful article.