top of page

አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ሰጥተው የሚጣሉ ስስ ፌስታሎችን መጠቀም ከአንድ ወር በኋላ ይከላከላል፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ታህሳስ 22/2018 

 

አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ሰጥተው የሚጣሉ ስስ ፌስታሎችን መጠቀም ከአንድ ወር በኋላ ይከላከላል፡፡

 

አምራቾች በበኩላቸው አሁንም በቂ የሽግግር ጊዜ አላገኝም፣ ስስ ፌስታሎቹንም ቢሆን ልክ እንደ የውሃ መጠጫ ኮዳዎች አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ተሰብስበው መልሶ ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግ ይቻላል ይላሉ፡፡

 

በጉዳዩ ላይ የአካባቢው ጥበቃ ባለስልጣንን ጠይቀናል፡፡

 

ree

ድጋሚ ጥቅም ላይ መዋል ቢችሉም ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ናቸው በቀላሉ በተለያየ ምክንያትም በየቦታው ተበታትነው አካባቢ ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር ያስከትላል ተብሏል፡፡

 

ከዚህ ቀደም በዚህ ፕላስቲክ ምርት ላይ የተሰማሩ አምራቾች የሚያስከትለውን ጉዳት በመረዳት ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት መስጠት ወደሚችሉ የስራ ዘርፎች ፊታቸውን ቢያዞሩ የተሻለ ነው ሲል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መክሯል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ

 

ማርታ በቀለ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page