top of page

ወደ ህክምና ተቋማት የአጥንት ህክምና ፈልገው ከሚመጡ ተገልጋዮች አብዛኛዎቹ በትራፊክ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 24 hours ago
  • 1 min read

ታህሳስ 20/2018  

 

ወደ ህክምና ተቋማት የአጥንት ህክምና ፈልገው ከሚመጡ ተገልጋዮች አብዛኛዎቹ በትራፊክ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ተባለ፡፡

 

የትራፊክ አደጋ አሁንም ከሌሎች ጉዳቶች ይልቅ ለአጥንትና መገጣጠሚያ ችግሮች ቀዳሚ መንስኤ መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

በሌላ በኩል ጉዳቱ ከባድ ቢሆንም የህክምና ወጪው ከፍተኛ መሆንና ህክምናው በሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማት አለመገኘቱም ተጨማሪ ጫና መፍጠሩንም የኢትዮጵያ የአጥንት ቀዶ ህክምና ማህበር ተናግሯል፡፡

 

የማህበሩ ፕሬዝዳንትና የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ኤፍሬም ገብረ ሐና እንደሚናገሩት ከአጥንት ጉዳት ጋር በተያያዘ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው የትራፊክ አደጋ ነው ብለዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ እስካሁን የጉዳት መረጃ መመዝገቢያ ቋት የሌላት በመሆኑም በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ አድርጎታል የሚሉት ዶ/ር ኤፍሬም የኢትዮጵያ የአጥንት ቀዶ ህክምና ማህበር በራሱ ይህንን ለመስራት የጀመራቸው ስራዎች አሉ ብለዋል፡፡

ree

አደጋዎች እንዴት ነው የሚከሰቱት? የት ነው በብዛት ያሉት? የሚለውን ለመለየት የአደጋ መመዝገቢያ የለም ያሉት ዶ/ር ኤፍሬም እዚህም ላይ ለመስራት  እንደማህበር የያዘው አንድ ትልቅ እቅድ አለ አዋሣ ላይ በሙከራ ደረጃ የአደጋ መረጃ መመዝገቢያ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

 

ከአጥንት ጋር የተያያዙ ህክምናዎች በተለይም በአደጋ ምክንያት የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ውጪ የሚጠይቅ ለህክምና የሚሆኑ ግብዓቶችም ውድ መሆናቸው ህክምናው ላይ ተጽእኖ አለው የሚሉት ዶክተር ኤፍሬም የህክምና ውጪው ጥቂትም ቢሆን በጤና ኢንሹራንስ ውስጥ ተካቶ እንዲሰራበት ማህበሩ ግፊት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በአዲስ አበባ ብቻ የድንገተኛ አደጋ ህክምና በሚሰጡ ተቋማት ለመታከም ከሚመጡት ውስጥ ከ36 በመቶ በላይ የሚሆኑት በትራፊክ አደጋ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የሚመጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

 

ምህረት ስዩም

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page