top of page

ግብርናው ዘርፍ የብድር አቅርቦት ከማያገኙ ዘርፎች መካከል ቀዳሚው ነው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 8 minutes ago
  • 1 min read

ታህሳስ 21/2018

 

ግብርናው ዘርፍ የብድር አቅርቦት ከማያገኙ ዘርፎች መካከል ቀዳሚው ነው ተባለ፡፡

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ግብርናው የብድር አቅርቦት ከፋይናንስ ተቋማት እንዳያገኝ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ዋነኛው በዝናብ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው የግብርና ኦኮኖሚ ባለሙያ፡፡

 

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚስት ምርምር ዳይሬክተር እና ተመራማሪ ታደለ ማሞ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚቀርበው ብድር ውስጥ ግብርናው የሚያገኘው 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡

 

ከ10 በመቶ ብድሩ መካከል አብዛኛው ብድር በግብርና ምርት ማቀነባበር ስራ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርብ ነው ተብሏል፡፡ ገበሬው አሁንም ብድር እያገኘ አይደለም ብለዋል፡፡

 

ግብርናው ለሺህ አመታት በስፋት የሚያውቀው ቴክኖሎጂ በሬና ሞፈር ነው ፣ ገበሬውም የለመደው ዝናብን ጠብቆ ማምረት ነው ይህ ደግሞ ለፋይናንስ ተቋማቱ ለዘርፉ ብድር ለመስጠት የሚያስችላቸው አይደለም ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

 

ree

ከተሞች አካባቢ የግብርና ምርት አንድ ሰሞን ዋጋው ሲንር ሌላ ጊዜ ደግሞ የምርቱ ዋጋ ዝቅ ሲል ይታያል ይህ የሚሆነው ገበሬው በአግባቡ የብድር አቅርቦት ስለማያገኝ ነው ብለዋል ዶክተር ታደለ ማሞ፡፡

 

እንዳመረተ ገበሬው ሕይወቱን የሚመራበትና የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችለው ፋይናንስ ይፈልጋል ይህ ደግሞ በወቅቱ ስለማያገኝ ያመረተውን ምርት ባገኘው ዋጋ ለመሸጥ ይገደዳል ይላሉ፡፡

 

ይህም የግብርና ምርቶች ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

 

ግብርናው እንዲዘምንና የገበሬው ሕይወት ለመለወጥ ምርቶች ከአመት እስከአመት ወጥ በሆነ መንገድ ለማቅረብ ከተፈለገ የመስኖ ግብርና ማስፋፋት ፣ ግብርና ለማዘመን በማሰብ ይቋቋማል የተባለው የግብርና ባንክ ማቋቋምና ወደ ስራ ማስገባት ይገባል ብለዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. 

 

በረከት አካሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page