የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለምርት ከሚጠቀሙባቸው ግብአቶች 95 በመቶውን ከውጪ እንደሚያስገቡ ተነገረ።
- sheger1021fm
- Jan 1
- 1 min read
ታህሳስ 23/2018
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለምርት ከሚጠቀሙባቸው ግብአቶች 95 በመቶውን ከውጪ እንደሚያስገቡ ተነገረ።
የምርት ማሸጊያዎችን ጭምር በውጪ ምንዛሪ ያስገባሉ ተብሏል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በኢንዱስትሪ ፖርኮች ዙሪያ ያካሄደውን ጥናት ዛሬ የሚመለከታቸውን ጠርቶ በካፒታል ሆቴል ይፋ አድርጓል።
በዚሁ ወቅት ሲነገር እንደሰማነው በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ቦታ ወስደው የሚሰሩ ባለሃብቶች 95 በመቶውን ግብዐት የሚያስመጡት ከውጪ ነው።
በፓርኮቹ ከሚሰሩ ባለሃብቶች አብዛኞቹ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርት ላይ የተሰማሩ እንደሆኑ የጠቀሰው ጥናቱ የሀገር ውስጥ ጥጥ በግብዓትነት ሲጠቀሙ ግን እይታም ብሏል፡፡
ለዚህ የሚያቀርቡት ምክንያት ጥራት ያለው እና ደረጃውን የጠበቀ ግብዐት ከሀገር ውስጥ አናገኝም የሚል እንደሆነ ተነግሯል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከፍተኛ የሠራተኞች በፍልሰት እንደሚታይም ጥናቱ ጠቁሟል።
ጥናቱን ካካሄዱ ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ሢሣይ ስንታየሁ ሲናገሩ እንደሠማነው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ ከጀመሩ አንስቶ እስከ አሁን ለስራው 350,000 ሰዎች ሰልጥነዋል።
አሁን ላይ እየሰሩ ያሉት ግን 70 ሺህ ገደማ መሆናቸው ተጠቅሷል።
የደመወዝ ማነስ ለፍልሰቱ እንደ አንድ ምክንያት ቀርቧል።
በፓርኮቹ የሚሰሩ ባለሃብቶች ከኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ጋር ሽርክና ፈጥረው ሲሰሩ እንደማይታም ተነግሯል።
አንድ የውጪ ባለሀብት ከሌላ የውጪ ባለሀብት ጋር በሽርክና መስራትን ይመርጣል ነው የተባለው።
ይህ ደግሞ እንደ ፀጥታ ያሉ ችግሮች ሲፈጠሩ ባለሃብቶቹ በቀላሉ ጥለው እንዲሄዱ እያደረገ ስለመሆኑ ተጠቅሷል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1












Comments