top of page

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የተባለ የግማሽ ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ልዩ ጨረታ ሊያካሂድ ነው፡፡

  • sheger1021fm
  • 3 hours ago
  • 1 min read

ጥር 18/2018


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የተባለ የግማሽ ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ልዩ ጨረታ ሊያካሂድ ነው፡፡


ነገ አካሂደዋለሁ ብሎ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር ለባንኮች አቀርባለሁ ብሏል፡፡


የዛሬ ሳምንት ባካሄደው የ70 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ 15 ባንኮች አንድን ዶላር በአማካይ 154.9 ብር በሆነ ዋጋ ገዝተዋል፡፡


በዚህ ጨረታ የባንኮች ፍላጎት 94.7 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት የነበረ ሲሆን በጊዜው ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው 70 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር ከ24 ሚሊዮን ዶላር በላይ ክፍተት እንዳለው ያሳያል፡፡


ይህም በባንኮች ዘንድ ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት መኖሩን ያሳያል፡፡


በጥቁር ገበያው እና በመደበኛው የምንዛሬ ገበያ መካከል ያለው ልዩነትም እንደታሰበው መጥበብ አልቻለም፡፡


የተጠቀሱትን ክፍተቶች ከግምት በማስገባት እና የምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋትም ይመስላል ብሔራዊ ባንክ ነገ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ለባንኮች በጨረታ አቀርባለሁ ብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገበያውን ለማረጋጋት ያለበትን ሀላፊነት ለመወጣት የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ማካሄድ ከጀመረ ወዲህ በልዩ ጨረታ ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ሲያቀርብ የነገው ሁለተኛው ነው፡፡


ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በወጣው የ150 ሚልዮን ዶላር ጨረታ ብር ከዶላር አንጻር በስሱም ቢሆን በ40 ሳንቲም የመጠንከር አዝማሚያ አሳይቶ እንደነበር አይዘነጋም፡፡


ለነገ የተሰናዳው ሁለተኛው ልዩ ጨረታ ከታህሳሱ በ350 ሚልዮን ዶላር ከፍ ያለ ነው፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..


X : https://x.com/shegerfm?s=2

Website፡ https://www.shegerfm.com/

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page