ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚካሄደው የግብርና ስራ በየዓመቱ የሚያስፈልገው አጠቃላይ ብድር 2.5 ትሪሊዮን ነው፡፡
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ጥር 18/2018
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚካሄደው የግብርና ስራ በየዓመቱ የሚያስፈልገው አጠቃላይ ብድር 2.5 ትሪሊዮን ነው፡፡
አሁን ላይ በዓመት እየቀረበ ያለው 52 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
ለማዳበርያ ከንግድ ባንክ እየቀረበ ያለውን ብድር ሳይካተት፡፡
ይህም ማለት ግብርናው ከሚፈልገው ብድር አኳያ እየቀረበ ያለው እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ነው፡፡
መንግስት በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሀገር አቀፍ የግብርና ፍኖተ ካርታ ከ4 ዓመት በኋላ ለግብርናው ዘርፍ በየአመቱ መቅረብ የሚገባው ብድር መጠን 880 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል፡፡
በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የዲጂታል ፋይናሻል ሰርቪስ ፕሮግራም ቡድን መሪው አቶ አወት ተኬኤ የፋይናንስ ዘርፉ ለግብርናው በቂ ብድር የማያቀርበው ዘርፉን በቅጡ ባለመረዳት ነው፡፡
በተለይም የግል ፋይናስ ተቋማት ለግብርናው የሚሆን ምርት በሚገባ እያስተዋወቁ አይደለም የሚነሳው የፖሊሲ ክፍተት እንደተጠበቀ ሆኖ ብለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ የግብርና ፍኖተ ካርታው መረጃ መሰረት አነስተኛ ማሳ ያለው አንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ የሚያገኘው ብድር መጠን 10 ሺ ብር ብቻ ነው፡፡
በዚህ ብድር ብቻ ገበሬው እርሻው መከወን አይቻልም ብድሩን በተለያየ አማራጭ ማስፋት አለብን ሲሉም አክለዋል፡፡
መንግስት የግብርና ፋይናንስ ችግርን ለመቅረፍ በማሰብ በተጠናቀቀው 2025 የግብርና ፍኖተ ካርታ ይፋ ማድረግ ዘርፉን ለመለወጥ ያለው ፍላጎት ያሳያል ብለዋል፡፡
ብድር ሲቀርብ ከገበሬው ጀምሮ እስከ ምርት ማቀነባበር ስራ ላይ ለተሰማራው የግብርና ተዋናይ ነው ይበልጡኑ ለገበሬው ሲሉም ነግረውናል፡፡
ከ2017 ዓመት በፊት በነበሩት 3 ተከታታይ አመታት በነበሩት ጊዜያት 591 ቢሊዮን ብር ብድር ከባንኮች መሰራጨቱን የግብርና ሚኒስቴርና ብሄራዊ ባንክ የወጡት መረጃ የሚያሳይ ሲሆን ግብርናው የ122 ቢሊዮን ብር አግኝቷል፡፡
ከዚህ ውስጥ 52 ቢሊዮን ብሩ ብቻ ነው ከማዳበርያ ውጪ ላለው የግብርና ስራ የቀረበው ብድር፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD








