top of page


በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ 3,461 ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ኢሰመኮ ተናገረ፡፡
መጋቢት 4/2018 በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ 3,461 ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች እና ማሳዎችን ጨምሮ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢሰመኮ አረጋግጫለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ ጋጮ ባባ፣ ቦንኬ፣ ካምባ ዙሪያ እና ምዕራብ አባያ ወረዳዎች በሚገኙ 6የተለያዩ ቀበሌዎች የተከሰቱ የመሬት መንሸራተት፣ የናዳ እና የጎርፍ አደጋዎችን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን እየተከታተለ አንደሆነ አስረድቷል። ኮሚሽኑ መግለጫውን ዛሬ እስካወጣበት ቀን ድረስ በድምሩ የ65 ሰዎች ሕይወ
1 day ago1 min read


547 - ስለ ህገወጥ የስራ ስምሪት እና ጉዳቶቹ በተግባር ካለፉበት በላይ ማን ሊያወራ ይችላል?
ስለ ህገወጥ የስራ ስምሪት እና ጉዳቶቹ በተግባር ካለፉበት በላይ ማን ሊያወራ ይችላል? ሙሉ ዝግጅቱን ያድምጡ…… አዘጋጅ የኔነህ ሲሳይ
2 days ago1 min read


በጋሞ ዞን ሰሞኑን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 64 መድረሱ ተነገረ።
መጋቢት 3/2018 በጋሞ ዞን ሰሞኑን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 64 መድረሱ ተነገረ። የተጎዱትን በህይወት የማትረፉ ስራ ከዚህ በውሃላ ብዙም ተስፋ የለውም፣ቀሪ የአስከሬን ፍለጋ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው ተብሏል። የሟቾቹ ቁጥር 52 ስለመድረሱ አስቀድመን ነግረናችሁ የነበረ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የተጨማሪ ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ተናግሯል። እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘ የሟቾች ቁጥርም 64 ደርሷል ብሏል። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በአካባቢው ነዋሪ የነበሩና በአደጋው የጠፉ ሰዎች ቁጥር 128 መሆኑን ተናግሯል። እስካሁን ባለው መረጃ ከዚህ ውስጥ የ64ቱ ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሀም ቡሔ ተናግረዋል። ኢንስፔክተሩ በሶስት ወረዳዎች አደጋ ተመዝጋቧል ያሉ ሲሆን ከሁሉም
2 days ago1 min read


የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ ፣ የፓርኮች መራቆት፣ ግጭት እና የፋይናንስ እጥረት የዱር እንስሳትና የፓርኮች ጥበቃ ስራ ፈተና ሆኗል ተባለ።
መጋቢት 3/2018 የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ ፣ የፓርኮች መራቆት፣ ግጭት እና የፋይናንስ እጥረት የዱር እንስሳትና የፓርኮች ጥበቃ ስራ ፈተና ሆኗል ተባለ። ይህ የተባለው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት ዛሬ ሲያከብር ነው። የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታው አቶ ስለሺ ግርማ የኢኮ ቱሪዝምና የብርቅዬ እንስሳት ቱሪዝም ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ መጥቷል ብለዋል። ላለፉት 60 ዓመታት ህገወጥ የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ፣ የፓርኮች መራቆት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የፋይናንስ እጥረት ዘርፉን ሲገጥሙት የነበሩ ችግሮች ናቸው ተብሏል። የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በኢትዮጵያ 30 ፓርኮች፣ ከ90 በላይ ጥብቅ ስፍራዎች ስለመኖራቸው ተናግረዋል። ከነዚህ ውስጥ የባሌ ብሔርራዊ ፓርክና ሰሜን
2 days ago1 min read
በኢትዮጵያ የንግዱን ማህበረሰብ እየገጠሙ ካሉ ችግሮች 40 በመቶ ያህሉ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው ተባለ ።
መጋቢት 3/2018 በኢትዮጵያ የንግዱን ማህበረሰብ እየገጠሙ ካሉ ችግሮች 40 በመቶ ያህሉ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው ተባለ ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ኢንዱስትሪ ተቋማት እንዳሉ ተነግሯል። የእነዚህ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ኢ-መደበኛ በሆኑ ሌሎች ንግዶች የተሠማሩ ሰዎች በአጠቃላይ የብድር ፍላጎታቸው በአገሪቱ ባሉ ሁሉም ባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ተቆጥቦ ከሚገኘው ገንዘብ ግማሽ ያህሉን ይሆናል ተብሏል። በኢትዮጵያ ባሉ ባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ተቆጥቦ ያለ አጠቃላይ ገንዘብ 3.7 ትሪሊዮን ብር እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በካፒታል ሆቴል እያካሄደው ባለው ውይይት ላይ ሲነገር ሠምተናል። በውይይቱ ላይ የንግዱ ማህበረሰብ ስለሚገጥመው የመስ
2 days ago1 min read


ህገ ወጦች ጤነኛ ህፃናት የአካል ጉዳተኛ እያደረጓቸው ለጎዳና ላይ ልመና እንደሚያሰማሯቸው ጥናት አሳየ።
መጋቢት 2/2018 ህገ ወጦች ጤነኛ ህፃናት እና አቅመ ደካሞችን የአካል ጉዳተኛ እያደረጓቸው ለጎዳና ላይ ልመና እንደሚያሰማሯቸው ጥናት አሳየ። የተሻለ ህይወት ትኖራላችሁ እየተባሉ ከክፍለ ሃገር ወደ ከተማ የሚመጡ ጤነኛ ህፃናት ጭምር ሰዎችን ለማራራት በሚል ዓይነ ስውር እየተደረጉ ለልመና መሰማራታቸውን ጥናቱ ጠቅሷል። ጥናቱን ፖፕሌሽን ካውንስል የተባለና ትኩረቱን በጤና ነክ ምርምሮች ላይ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም የተሰራ ሲሆን በጥናቱ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና መቀሌ መካተታቸው ተነግሯል። ህፃናት እና አቅመ ደካሞችን እየመለመሉ ለልመና የሚያሰማሩ ሰዎች የአካል ጉዳት የሌለባቸውን ጭምር የአካል ጉዳተኛ እንደሚያደርጓቸው የነገሩን የፖፑሌሽን ካውንስል የኢትዮጵያ ተወካይ ጌታቸው ተሾመ(ዶ/ር) ናቸው። ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ከትውልድ ስፍራቸው የሚመ
3 days ago1 min read


በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት ያደረገ ገቢ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል?
መጋቢት 2/2018 በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት ያደረገ ገቢ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል? የአገሪቱ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሲነገር ይሰማል። በዚህም የተነሳ የታክስ አይነቱ በላይ በላዩ ሆኖ ይታያል። የገንዘብ ሚኒስቴር በጠራው በገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ወይይት ላይ የተገኙት የተመሰከረለት የሂሳብ ባለሞያው አቶ አወቀ አስፋው ኢኮኖሚያችንን ብናያው ሲሉ ይመክራሉ፡፡ በለሙያው በአገሪቱ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ አይደለም የሚል ሃሳብ ሁሌ እንደሚነሳ አስታውሰው፤ በቅርብ በተሰሩ እና በወጡ መረጃዎች መሰረት ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት 138 ሚሊዮን በመያዝ ከ233 አገራት 10ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይህም ትልቅ ቁጥር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የጥቅል ዓመታዊ ምር
3 days ago2 min read


ጀነራል አስራት ዴኔሮ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ተክተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡
መጋቢት 2/2018 ጀነራል አስራት ዴኔሮ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ተክተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡ ሹመቱን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ መሰረት ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡
3 days ago1 min read


በጋሞ ዞን የጎርፍ ናዳ 30 ሰዎችን ገደለ።
መጋቢት 1/2018 በጋሞ ዞን የጎርፍ ናዳ 30 ሰዎችን ገደለ። በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት፣ በተለይም በደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ስዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ተናግሯል። የዞኑ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እያደረኩ ነው ብሏል። የ30 ህይወት የቀጠፈው የጎርፍ አደጋ መቼ እንዳጋጠመ ዞኑ ያለው ነገር የለም። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ "በጋሞ ዞን በደጋማ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት ናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖቻችን ህይወት በማለፉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በክልሉ መንግስት ስም እገልጻለሁ"ብለዋል። እንደ አርባ ምንጭ እና ገረሴ ከተሞች ባለፋት ሁለት ቀናት በአ
3 days ago1 min read


መጋቢት 2/2018 - ከፍተኛ ትችት የቀረበባቸው እና የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተካተቱ የህግ ክፍሎች እንዲሻሻሉ ቢጠየቅም አዋጁ ስለጸደቀ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አይቻልም ተባለ።
መጋቢት 2/2018 ከፍተኛ ትችት የቀረበባቸው እና የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተካተቱ የህግ ክፍሎች እንዲሻሻሉ ቢጠየቅም አዋጁ ስለጸደቀ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አይቻልም ተባለ። ይህን ያለው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው። የገንዘብ ሚኒስቴር መጋቢት ትላንት፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ለጸደቅው የግቢ ግብር ማስፈጸሚ ረቂቅ ደንብ ላይ በመስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሞያ፣የስራ እና የድርጅት ተወካይዎች ጋር ከ5 ሰዓት በላይ የፈጀ ወይይት አካሂዷል ። በወይይቱ ላይ ጥያቄ ካቀረቡት ከ20 በላይ ተሳታፊዎች ውስጥ የሚበዙት ተመሳሳይ ጥያቄ እና ሀሳብ ስጥተዋል ። የተጣለው የ2.5 በመቶ የአማራጭ አነስተኛ ግብር እንዲነሳ፣ድርጅቶች ወይንም ተቋማት የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ ያሚያስገድድው የህግ ከፍል እና በየሩብ ዓመት ግብር እንዲሰበሰብ የሚያዘው የህ
3 days ago3 min read


ከውስብስብ የአንጎል አፈጣጠር ችግር ጋር የተወለደች ህፃንን በተሳካ ቀዶ ህክምና ማከም መቻሉ ተነገረ፡፡
መጋቢት 1/2018 ከውስብስብ የአንጎል አፈጣጠር ችግር ጋር የተወለደች ህፃንን በተሳካ ቀዶ ህክምና ማከም መቻሉ ተነገረ፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
4 days ago1 min read


በየሳምንቱ 1 ሚሊዮን ሰዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው ተባለ።
መጋቢት 1/2018 በየሳምንቱ 1 ሚሊዮን ሰዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው ተባለ። በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ የፋይዳ መታወቂያ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 37.5 ሚሊዮን መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርአያስላሴ ተናግረዋል። ዋና ዳሬክተሩ ይህን ያሉት ፅ/ቤታቸው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለግል መገናኛ ብዙኀን ፋይዳ መታወቂያ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ብዛት 90 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ አቶ ዮዳሄ አስረድተዋል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመልካም አስተዳደር፣ ለማህበራዊ እና ደህንነት ጉዳዮች ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በፕሮግራሙ ላይ ሲነገር ሰምተናል።
4 days ago1 min read


ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ ተናገረ።
የካቲት 30/2018 ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ ተናገረ። ቦርዱ ይህን ያለው ባለፈው ቅዳሜ በኢዲስ ኢንትርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያላቸው ድርሻ በሚል ርዕስ በተሰናዳ የወይይት መድረክ ላይ ነው። ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አካታች እና ታዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን እያሰራ ነው? የሚል ጥያቄ በወይይቱ ላይ ለምርጫ ቦርድ ቀርቧል። ቦርዱን ወክለው በውይይቱ ላይ የታደሙት የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ የመራጮች ምዝገባ በአንዳንድ ክልሎች መጀምሩን እና የዕጩዎች መዝገባ መጠናቀቁን ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ ነዋይ ዘንድሮ ቦርዱ እሰራለሁ ያለው ትልቁ ስራ የፖለቲካ ፓ
5 days ago1 min read


ኢትዮዽያ በአለም የሎጅስቲክስ ሜዳ
የካቲት 27/2018 የሎጅስቲክስ ስራ ፍፁም የሰላም መስመር እና እውቀት ይፈልጋል፡፡ ሎጅስቲክስ በኢትዮጵያ እንዲዘምን፣ እንዲቀላጠፍ አሁንም ብርቱ ስራ ይጠይቃል። እቃዎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለማንቀሳቀስ፣ መያዝ፣ ማከማቸት እና ማስተናገድ ፤ በየትኛውም የአለም መሮጫ ኮሪደር እና ባህር ማገላበጥ ፤ በአየር በየብስ ምድር ለመላወስ ጥንቅቅ ያለ የሎጅስቲክስ ስራ ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በየጊዜው በአለም በሚደረጉ ጉባኤዎች እና የሎጅስቲክስ ማህበራት ላይ በኃላፊነት ቦታ መገኘት እንደሚያስፈልግ ይታመናል። በተለይ ከአፍሪካ ብቸኛው የአለም ፍሬይት ፎርዋርደርስ ማህበር ፊያታ የቦርድ አባል እና በ ኢትዮጵያም የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ውብሸት በዚህ ጉዳይ ስጋት እንዳላቸው ነግረውናል። ኢትዮዽያ በአለም የሎጅስቲክስ ሜዳ ፤ በጭነት መርከቦች እና አጠቃላ
Mar 61 min read


ደንበኞች ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት አሰራር በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ተናገረ፡፡
የካቲት 27/2018 ደንበኞች ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት አሰራር በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ተናገረ፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ይረዳኛል ብሏል። የሙከራ ትግበራው ከ16 ሺህ በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ባሉበት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን መጀመሩን የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ነግረውናል ፡፡ ሥራ አስፈፃሚው የዲጂታል አሰራሩ ለደንበኞች በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን፣ የፍጆታ ሂሳብን በወቅቱ ለመፈጸም፣ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ጊዜና ወጪን ለመቆጠብ ያስችላል ብለውናል፡፡ በዚህም ከየካቲት 13 ቀን እስከ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ደንበኞች የፍጆታ ንባባቸውን በቀላሉ በቤታቸው ሆነው ለዚሁ አ
Mar 61 min read


የባቱ - አርሲ ነገሌ 57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎቹ ተጠናቅቀዋል ተባለ።
የካቲት 26/2018 የሞጆ - ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የባቱ - አርሲ ነገሌ 57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎቹ ተጠናቅቀዋል ተባለ። የመንገድ ኮሪደሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች የሚገኙትን የባቱ ከተማን፣ የአዳሚ ቱሉ እና አርሲ ነገሌ ወረዳዎችን ጨምሮ ከ17 በላይ ቀበሌዎችን ያስተሳስራል ተብሏል። የመንገድ ግንባታው የአዲስ አበባ - ሞያሌ - ናይሮቢ - ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል መሆኑ ተነግሯል። ግንባታውን ለማከናወን ከዓለም ባንክ የተገኘ 5.3 ቢሊዮን ብር ወጪ መሆኑ ተነግሯል። 57 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቱ - አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ በ90 ሜትር የመንገድ ወሰን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ የጎን ስፋቱ የመንገድ አካፋይን ጨምሮ 31.6 ሜትር መሆኑን የኢትዮጵያ መን
Mar 52 min read


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተነግሯል።
የካቲት 26/2018 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተነግሯል። ይህም የክልሉን አጠቃላይ 20 በመቶ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ማራቁን የክልሉ ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በሽር አብዱረሂም ተናግረዋል። አሁን ላይ ግን በክልሉ በተሰሩ ስራዎች በአብዛኛው በሚባል ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደታቸው መመለሳቸውን ኃላፊው አንስተዋል። ኃላፊው ይህንን ያሉት ኩሶ ኢንተርናሽናል የተባለ የተራድኦ ተቋም በክልሉ ባለፉት 6 ዓመታት ሴት ተማሪዎችን ለዩንቨርሲቲ የማብቃት ፕሮጀክት (U_Girls project) የማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው። የትምህርት ቢሮ ኃላፊው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመማር ማስተማር ችግሮችን በመፍታት ሂደት ውስጥ የኩሶ ኢንተርናሽናልን
Mar 51 min read


ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ የሚያስችል ሁለተኛ ዙር ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ፡፡
የካቲት 26/2018 በተለያዩ አካባቢዎች ባለ የሰላም እጦት እና የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ የሚያስችል ሁለተኛ ዙር ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ፡፡ በአለም ባንክ የሚደገፈው እና ለ5 ዓመታት ይቆያል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ 2 ዓመታት እንደቀረው ሲነገር ሰምተናል፡፡ በዚህም ሁለተኛው ምዕራፍ እና በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ይተገበራል የተባለው ስራ ወደ ትግበራ መግባቱ ተነግሯል፡፡ በጦርነት ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የጤና ድጋፍ እንዲያገኙ፣ የኢኮኖሚ ምስቅልቅል የገጠማቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮቻቸው ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ ፕሮጀክቱም በ5 ክልሎች የሚተገበር ሲሆን አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ቤኒሻን
Mar 51 min read


ከጎርጎርሳውያኑ ከ2024 ጀምሮ ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተብሏል።
የካቲት 26/2018 ከጎርጎርሳውያኑ ከ2024 ጀምሮ ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከአፍሪካ ሁለተኛ ፤ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተብሏል። በቀጣይ ወር በአዲስ አበባ በሚዘጋጀው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ብቻ ከ2.4 ቢሊየን ዶላር በላይ ግምት ያለው የኢንቨስትመንት ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የገንዘብ ሚኒስቴር ፎረሙን አስመልክተው ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ዘርፎችን የሚደግፉ ከ123 በላይ አዳዲስ ህጎችን ባለፉት ሰባት ዓመታት አውጥታለች ተብሏል። ማሻሻያ የተደረገባቸው ህጎች ከተጨመሩበት ደግሞ ቁጥሩ ከ198 እንደሚልቅ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን ተናግረዋል።
Mar 52 min read


አዋሽ ባንክ ለ7 ግብረ ሰናይ ድርጅቶች 25 ሚሊዮን ብር ሰጠ።
የካቲት 26/2018 አዋሽ ባንክ ለ7 ግብረ ሰናይ ድርጅቶች 25 ሚሊዮን ብር ሰጠ። ባንኩ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ ድጋፉን ያደረገው ያለንበትን የረመዳን ወርን ምክንት በማድረግ ነው። 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶችም ህጻናትን፣ በአረጋዊያንን እና አካል ጉዳተኞችን በመደገፍና በመንከባከብ ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ተጠቅሷል። ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን፣ የስራ ለና የበጎ አድርጎ ድርጅት፣ ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ሰፖርት ኦረጋናይዜሽን፣ ዘ ችልድረንስ ኸርት ፈንድ ኦፍ ኢትዮጵ፣ እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት እና አብደላ ኢብኑ ኡሚ መክቱም ቁራን ማህበር ናቸው ድጋፉ የተደረገላቸው። አዋሽ ባንክ የ1447ኛውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ትናንት ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላ
Mar 51 min read


አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በውስጡ ምን ይዟል?
የካቲት 25/2018 የሚኒስትሮች ምክር ቤት 53ተኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት በቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አድርጎ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ፖሊሲዋን ለመጨረሻ ጊዜ ያሻሻለችው በ2001 ዓ.ም ነበር፡፡ ታዲያ አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በውስጡ ምን ይዟል? ስንል በፖሊሲ ማርቀቁ ላይ የተሳተፉትን አቶ ኤንዲ አሰፋን ጠይቀናቸዋል፡፡ የቱሪዝም ባለሙያው አቶ ኤንዲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ወደ ስራ እንዲገባ የተፈቀደው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በዘርፉ ከዚህ ቀደም ይነሱ ለነበሩ ችግሮች ምላሽ ይዞ መጥቷል ይላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ቱሪዝም መሰረተ ልማትን በተመለከተ በፖሊሲ ደረጃ የተቀመጠ ነገር አልነበረም አዲሱ ፖሊሲ በዚህ ዙሪያ ምላሽ አለው በዘርፉ የተማሩ ባለሙያዎችም እንዴት መሰማራት እንዳለባቸው
Mar 41 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

