ነሀሴ 30 2017የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፤ የአገልግሎት እና ቁጥጥር ጥራቱን እንዲያሻሽል ይረዳዋል የተባለለት ስምምነት ከኤምኤስአይ ኢትዮጵያ ጋር አደረገ።
- sheger1021fm
- Sep 6
- 1 min read
በዚህ ስምምነት ኤምኤስአይ ኢትዮጵያ (MSI Ethiopia) 5 ሚሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።
በሚደረገው ድጋፍም ባለስልጣኑ የባለሞያዎቹን አቅም ለማሳደግ፤ የተለያዩ ስልጠናና መሰል የአቅም ግንባታ ስራዎች እንደሚሰራበት ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በከተማው ባሉ በ4,000 የጤና ማዕከላት እንዲሁም 44,000 የምግብና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።
ከስራው ሰፊነት አንፃር በመንግስት በጀት ብቻ ጥራት ያለው ስራ ለመስራት እንደሚያስቸግር የተናገሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሙሉእመቤት ታደሰ፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አጋርነት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።
ዛሬ የተደረገው ስምምነት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 2 ሚሊዮን የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በተዘዋዋሪ ተደራሽ እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን እንደየአስፈላጊነቱ ሊራዘም ይችላል ተብሏል።

MSI Ethiopia በእናቶች፣ በወጣቶች እንዲሁም በህፃናት ጤና ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ተቋም ነው።
በዚህም በየዓመቱ በኢትዮጵያ ለ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች በተለያየ መንገድ ተቋሙ ድጋፍ ያደርጋል ያሉን፤ የኤምኤስአይ ካንትሪ ዳይሬክተር አበበ ሽብሩ(ዶ/ር) ናቸው።
ማንያዘዋል ጌታሁን








